የመለስ ዜናዊ አሽከሮች ስብሰባ በአትላንታ ከሸፈ
ቅዳሜ ኖቬምበር 27 ቀን 2010 እ ኤ አ በአትላንታ ጆርጅያ በአቶ ዳዊት ቸኮል የተጠራው ስብሰባ ሳይጀመር ተጨናግፏል።
አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የስብሰባ ጥሪ መኖሩን ሲሰሙ፤ ስብሰባው ምንን አስመልክቶ እንደሆነና፤ የስብሰባው ጠሪወች እነማን እንደሆኑ ጠንቅቀው ካወቁ በኋላ በተጀመረው ወያኔ/ኢሕአዴግንና ተባባሪ ደጋፊወቹን በያሉበት መታገል አስፈላጊነት በሚለው መርሕ ተነሳስተው የአትላንታ አገር ወዳድና የፖለቲካ ድርጅት ደጋፍኢወች ይህን የበርከት ስምኦንን ድርጅት ጥሪ የአድርባዮች ስብስብ መሆኑን ለማጋለጽ ወደአዳራሽ ገቡ። በእርግጥም ስብሰባው የተጥራው በበአዴን የአካባቢው ቻፕተር ሲሆን የስብሰባው አላማ ድርጅቱ ተመሰረተ የሚሉትን 30ኛ አመት ለማክበር እንደሆነ እዚያ ከተደረሰ በኋላ ለማወቅ ተችሏል። ሌላው ኢንቨስትመንትና እድገትን አስመልክቶ የተያዘ አጀንድአም እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
በአለፈው ሙሉ ሳምንቱን የኑልን ጥሪ የተደረገለቱ ስብሰባ በእርግጥም ስብሰባ ሳይሆን የቪዲዮ ዝግጅት እንደነበር የአገዛዙ ደጋፊወችና ተቃዋሚወች ወደስብሰባው አዳራሽ ከገቡ በኋላ ተረድተዋል።
የዚህ የእንኳን አደረሰን ጥሪና አያይዞም የበአዴን የድል ውጤት ያሉትን ሁሉ ከአዲስ አበባ በነበረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰና የአድርባዩ ክንፍ መሪወች የላኩትን የቪዲዮ ፕሮፓጋንዳ የተጠራው እንዲመለከት ድምጽ ከፍ ተደርጎ የሚጫወት የቪዲዮ ምስሎችን ሲጋብዙ። ጉዳዩ ያስገረማቸው ወገኖች በስነስራት ጠይቀው አስቁመዋል።
አንዱና ዋነኛው የስብሰባው መልእክት፤ የዛሬ 30 አመት ዛሬ በሕወሐት ተጠፍጥፎ የተሰራው የበረከት ስመኦን የአማራ ድርጅት ተብየው ከኢሕአፓ ሰራዊት አምልጠውና አፈርሰው ጠፍተው በሄዱ ግለሰቦች ኢሕዴን የተባለ ስም ተሰጦት የሕወሐት ሰርዊት በተንቀሳቀሰበት አብሮ ሲንከራትት የነበር የትቂት ግለሰቦች ስብስብ ሲሆን። እነዚህ ግለሰቦች ለአንድ የዘር ድርጅት የሚያበቃም እንኳን መስፈርት ሊያሟሉ የማይችሉ ሆነው ሳለ፡ ወያኔ የትግራይን ትግል አስፍቶ ወደወሎና ጎንደር መንቀሳቀስ ሲጀምር እነ ታደሰ ጥንቅሹን፣ እንወይ ገ/መድሕንን እና ሌሎች ተመሳሳይ ግለሰቦችን በማስቀደም ከኢሕዴንነት ወደ በአዴንነት ቀይሮ የአማራ ድርጅት ነን ብለው ላለፉት 30 አመታት የወያኔ ጋሻጃግሬ በመሆን እንዲያገለግሉት አድርጓል። በእርግጥም እነዚህ ግለሰቦች አገር ከማስገንጠል ጀምሮ በአርባ ጉጉና በበደኖ እንዲሁም በአሰቦት ገዳምና በጎንደር እየሱስ ለተካሄደው ፍጅት ፊታውራሪ ሆነውም ሰርተዋል። በአማራ ስም ተደራጀሁ ያለው የበረከት፣ አዲሱ፣ ተፈራ፣ ሕላዊ፣ ታደሰና ታምራት ላይኔ ድርጅት፤ ወያኔ የሰጠውን ተልእኮ በሚገባ አከናውኗል። የዚህ ኮ….. ድርጅት መሪወች ከአገር አገር እየዞሩ ሰላማዊ ዜጎችን ነፍጠኛና ትምክህተኛ በማለት አስረዋል ገለዋል። በተለየም ከኢትዮ/ኤርትርያ ጦርነት ማግስት ጀምሮ መለስና የሕወሐት ተከታዮቹ ብቻቸውን በቀሩበት ወቅት አቢይ ሚና ይዘው የመለስን መንግስት ያተረፉ እነዚህ ጉዶች እነደነበሩ የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመጀመሪያ መብቱን በትግሉ ተጠቅሞና ሆብሎ ወጥቶ ያሳየውን የምርጫ 1997 ዓ.ም ገድል ከአጋዚ ጦር ጋር ሆነው እንዲጨናገፍ ያደረጉና የአያሌ ዜጎችን ሕይወት ያመሰቃቀሉ እነዚሁ የበአዴን ጀሌወች እንደነበሩ በሐዘን እናስታውሳለን። ይህን በበቂ የሚያውቀው አገር ወዳድ የአትላንታ ወገንና የተቃዋሚ ድርጅቶች ደጋፊወች በአንድ በመሆንና በመተባበር በዛሬው ቀን የአትላንታ የበአዴን 30 አመት ብለው በጠሩት ስብሰባ በመገኘት ስብሰባውን እነሱ በፈለጉት መልክ ሳይሆን በዚህ ዘረኛ መንግስት ለተጨፈጨፉ ሰማእታት ጸሎት በማድረግ እንዲጀመር በማድረግ፤ ያሰቡት የበአዴን/እሕዴን የተለጣፊነት ቀንን አስተጓጉለውታል። ለሰማእታቱ ከተደረገው ጸሎት በኋላ ምንም አይነት ስብሰባ ማድረግ ስላልቻሉ ቀናችውም ስለተበላሸ ያለምንም ማንገራገር አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል።
አገርወዳዱና ተቃዋሚውም በድጋሜ በዳላስ፣ በለንደን የታየውን ወያኔን በየሄደበት መከላከል አላማ ዳግም በአትላንታ በማድረግ፤ ለዴሞክራሲው ትግል የበኩላችንን አስተዋጸኦ በማረግና በጭቆና ስር ላለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎኑ መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ አስመዝግበናል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ከአትላንታ አገር ወዳድ ኢትዮጵያያንና የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊወች