ጠቢቡ ሰለሞን፣ ጥበበ የሱስን ተመስሎ መጣ እንዴ? – ገላነው ክራር
“ስለ አማርኛ ቋንቋ ቃላት በማንሳት መከራከር … ከኔ ይራቅ… ስለ ሃይማኖት ያነሳሃውን ግን በግዴለሽነት፣ በማናለብኝነት፣ …ባለፈው…” ከሚል ቀረርቶ ጋር ጥበበ የሱስ የሰብቁብኝ ጦር… ጭቃ የማይወጋ…ቄጠማ ኖሯል።
በከበደ ሚካኤል ግጥም እንጀምር። ፍቺው እርስዎ እንዳሉት፣ ያ መሆኑን (በኮሚኒዝም ስም ያለቀው፣ ሃይማኖት የለሾችን ሃይማኖትቴን ክጃለሁ ብላችሁ…” ለሚሉት ምንጭዎትን ባይጠቅሱልኝም1 እርስዎ ባሉት መንገድ ሊፈታ እንደማይችል እንዲህ አስረዳለሁ።
“ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም” በሚለው መንቶ ውስጥ፣ ሁለት መልእክቶች ናቸው ያሉት—ቢኖርም’ እና ‘ባይኖርም’ በሚሉት ቃላት ውስጥ።