ኢትዮጵያውያን ከያካባቢው ለተቃውሞ ሰልፍ ወደ ንዮርክ እያመሩ ነው።

ከህገሪቱ መዲና ዋና ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ በአሁኑ ወቅት በደረስን ዘገባ መሰረት 3 አውቶቡስ ሰልፈኛውን ጭነው እንደተንቀሳቀሱና ሌላ ተጨማሪ አውቶቡስ ተሳፋሪውን እየጫነ መሆኑ ተረጋግጦል።

እንዲሁም ከቦስተን ከተማ አንድ መለስተኛ አውቶቡስ ሰልፈኛውን ጭኖ የለቀቀ ሲሆን እንዲሁም መጠናቸው 15 ሰው የሚይዝ ሚኒባሶች ውደ ኒዮርክ እያመሩ ሲሆን በግል ተሽከርካሪ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ሰልፈኞች ተንቀሳቅሰዋል።አቦጊዳ ድህረገጽም በምስል በማስደገፍ ወቅታዊ ዘገባ እንደሚያቀርብ እናሳውቃለን።