በወጣት ምሁራን የተቋቋመዉ የብርሃን ለአንድነት ለዲሞክራሲ ፓርቲ የአንድነት ፓርቲን ሊቀላቀል ነዉ !

አቡጊዳ – ነሐሴ 18 ቀን 2002 ዓ.ም

ብርሃን ለአንድነትና ለዲሞክራሲ የተሰኘዉ የፖለቲካ ድርጅት በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከሚመራዉ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ ማመልከቻ እንዳሰገባ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል።

በወጣት ምሁራን የተቋቋመዉ ብርሃን ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የያዘዉ የፖለቲካ ፕሮግራም፣ የቅንጅት ወራሽ ተብሎ ከሚነገርለት ከአንድነት ፓርቲ ጋር ተመሳሳይነት ያለዉ ሲሆን፣ ለመዋሃድ ያቀረበዉ ማመልከቻም በአንድነት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ በከፍተኛ አዎንታዊነት ተቀባይነት ያገኘ እንደሆነ ምንጮቻችን ይዘግባሉ።

የአንድነት ፓርቲ ከብርሃን ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጋር እንዲነጋገሩ ከፍተኛ የአመራር አባላትን መወከሉንም የደረሰን ዜና ያመለክታል።

የአንድነት ፓርቲ መድረክን በተቀላቀለ ጊዜ የከንባታ ሕዝብ ኮንግረስ የሚባለዉ ድርጅት እራሱን አፍርሶ አባላቱ በሙሉ የአንድነት ፓርቲን መቀላቀላቸዉ ይታወቃል። የብርሃን ፓርቲ የአንድነት ፓርቲን የመቀላቀል ሂደት ከተጠናቀቀ፣ የአንድነት ፓርቲ የተቀላቀለ ሁለተኛ ድርጅት ይሆናል።

በተያያዘ ዜና የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ማእከላዊ ኮሚቴ፣ ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጋር አብሮ የመስራትን ጥቅም አስምሮበት፣ ከአንድነት ጋር አብሮ መሥራት፣ አልፎም መዋሃድ የሚቻልበትን ሁኔታ እንዲነጋገሩ ሶስት ከፍተኛ የአመራር አባላቱን መመደቡን ከድርጅቱ አካባቢ ያሉ የታመኑ ምንጮቻችን ገለጹ።

ከአንድነት ፓርቲ ጋር እንዲነጋገሩ አቶ ማሙሸት አማረ፣ ዶር በዛብህ ደምሴና አቶ መሃተመ በኩረ የተመደቡ ሲሆን የአንድነት ፓርቲም የመኢአድ ማእከላዊ ኮሚቴ ለወሰነዉ ዉሳኔ አዎንታዊ ምላሽ በአስቸኳይ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በየቀበሌና በየወረዳዉ በአገሪቷ ክልሎች በሙሉ የመኢአድና የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች በአንድ ላይ እንደሚታሰሩ፣ እንደሚዋከቡና እንግልት እንደሚደርስባቸዉ የጠቆሙት ያነጋገርናቸዉ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ «ለአንድ ዓላማ በእሥር ቤት እየታሰሩና መከራ እየተቀበሉ፣ ተመሳሳይ የፖለቲካ ፕሮግራም እያላቸዉ መኢአድና አንድነት ከዚህ በፊትም ተለያይተዉ መቆማቸዉ ተገቢ አልነበረም» ሲሉ የመኢአድና የአንድነት መቀራረብ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የአንድነት ፓርቲ ከመድረኩ ዉጭ ካሉ ድርጅቶች ጋር አብሮ የመሥራት እንቅስቃሴዉ እንደተጠበቀ፣ በመድረክ ሥር አብረዉት ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋርም ያለዉን ግንኙትና መተሳሰር የበለጠ ይተናከር ዘንድ መድረኩ ከቅንጅትነት ወደ ግንባር የሚሸጋገርበት ሁኔታ ላይ አጥብቆ