ጅቡቲ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳያርፍ ከለከለች
አቡጊዳ — የጅቡቲ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጅቡቲ እንዳያርፍ መከልከሉን አዲስ ፎርቱን የተሰኘዉ በኢትዮጵያ የሚታተም የእንግሊዘኛ ጋዜጠ ዘገበ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐምሌ 27 (ኦገስት 1) ጀምሮ በርራዉን በጅቡቲ ያቀመ እንደሆነ የዘገበዉ አዲስ ፎርቱን በኢትዮጵያና በጅቡቲ መካከል ድርድሮች እየተደረጉ መሆኑንም ዘግቧል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ እስኪያጅ አቶ ግርማ ዋቆ «እንዲሟላ(ጅቡቲዎችን ማለታቸዉ ነዉ) የሚፈልጉት ነገር አለ። የበረራዉ መቋረጥ አንድ አይነት ስምምነት እስኪደረስ ነዉ» በማለት የተፈጠረዉን መጠነኛ ቀዉስ እንደ ትልቅ ችግር መታየት እንደሌለበት ለመጠቆም ሞክረዋል።
የጅቡቲ ኢኮኖሚ ሙሉ ለሙሉ የሚደገፈዉ ኢትዮጵያ ወደቧን በመጠቀሟ መሆኑ እየታወቀም፣ ጅቡቲ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳያርፍ ማገዷ፣ የሚያሳየዉ «ሌላ ወደብ የላቸዉም ፣ ከኛ ዉጭ የትም አይሄዱም። ምን ሊያደርጉ አይችሉም» የሚል አስተሳሰብ እንዳላቸዉ፣ መሆኑን የገለጹት በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡን የፖለቲካ ተንታኝ « ሰማኒያ ሚሊዮን በላይ የሆነ ሕዝብ አንድ ሚሊዮን በማይሞላ ሕዝብ ጥገኛ ሲሆን ማየትን የመሰለ የሚያሳዝ ነገር የለም» ሲሉም ለኢትዮጵያ ወደብ የማስፈለጉ ጉዳይ ትልቅ የአገር ደህንነት ጉዳይ እንደሆነ አስረድተዋል።