ወታደራዊው ክፍል የኢሕአዴግን ቀውስ አስታኮ ለስልጣን አሰፍስፏል።
ወታደራዊው ክፍል የኢሕአዴግን ቀውስ አስታኮ ለስልጣን አሰፍስፏል።
#Ethiopia #EPRDF #EthiopianArmy #TPLFCadets #Miniliksalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) “ፖለቲካዊ አመራሩ እንጂ ወታደራዊ ክፍሉ ጤነኛ ነው” እሚል መልእክት አደገኛ አካሄድ ነው:: በዝርፊያ በኢኮኖሚ ራሳቸው ያደላደሉ እና የፈረጠሙ ወታደራዊ መኮንኖችን ያቀፈው በሳሞራ የኑስ የሚመራው ወታደሩ ክፍል በሁለት መንገድ የኢሕአዴግን ቀውስ ተከትሎ ስልጣን ሊይዝ ይችላል የሚሉ ፍንጮች አየታዩ ነው። ከዚህ ቀደም የተለቀቁ መረጃዎችን (https://web.facebook.com/photo.php?fbid=1722881581316371&set=pb.100007836377373.-2207520000.1465128610.&type=3&theater ) –
( https://web.facebook.com/photo.php?fbid=1723183201286209&set=pb.100007836377373.-2207520000.1465128610.&type=3&theater ) የሚያጠናክሩ ጽሁፎች መነበብ ጀምረዋል።
ለኢሕአዴግ ቅርብ የሆኑትና የቀድሞ የሕወሓት ታጋይ የነበሩት ጆቤ(ሜጄ አበበ ተክለሃይማኖት) በኢትዮጵያ ደርግነት እያቆጠቆጠ – ዴሞክራሲው እየጨላለመ ነው – ህዝቦች ጠንቀቅ በሉ በማለት ሕዝብን ማስጠንቀቅ ጀምረዋል።ጄኔራሉ በዚህ ጽሁፋቸው ማጣቀሻ በማለት የተጠቀሙት የሳሞራ የኑስን ንግር ሲሆን ወታደራዊው ክፍል በበላይነት ሲቭሉን ስልጣን በቀጥጥሩ ስር ኣድርጎ ሊነዳው አንደሚፈልግ ኣሳይቷል ሲሉ ጽፈዋል፥ ኣያይዘዉም የዴሞክራሲ እጥረት ወይም ምህዳር መጥበብ ማለት ደርግነት መንገስ ማለት ነው፤ ሱፍም ወታደራዊ ልብስም ሊለብስ ይችላል። ብለዋል።

በሃገሪቱ የተከሰተውን ግልጽ የፖለቲካ ቀውስ በሃይል የመፍታት ኣዝማሚያ በስፋት አየታየ አየተተገበረ እንደሆነ የሚጠቁመው ጽሁፍ በከፍተኛ አመራሮቹ እየታየ ያለው ነገር አንዳንድ ስጋቶችን እየጫረ ይገኛል።በማለት የመቀሌውን የግንቦት ሃያ ፓናል አንደማጣቀሻ በማስቀመጥ ኢታማዦር ሹሙ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ያነስዋቸው ሃሳቦችና እና የተናገርዋቸው ነገሮች በጣም እሚያሳዝኑና ሕገ መንግስቱን ገድል ግባ ያሉበት መድረክ ነበር። ከ ሀ እስከ ፐ ስለ ሲቪል አስተዳደሩ ድክመት፣ ልፍስፍስነት፣ ስለ ወታደራዊ ክፍሉ የመተካካት ልዩ ችሎታና ስለ ሰራዊቱ የአሁንና የወደፊት ጥንካሬ ሲያወሩ ላየ ጄኔራሉ ምን እያለ እንደሆነ ይገባዋል ወይ፧ የሚል ጥያቄ ያጭራል። “ፖለቲካዊ አመራሩ እንጂ ወታደራዊ ክፍሉ ጤነኛ ነው” እሚል መልእክት አደገኛ አካሄድ ነው፤ እኔ ልምራ አይነት አንደምታ ያለው ንጝር ነው። የሲቪል መንግስት በወታደራዊ ክፍሉ የሚገመገምበት አሰራርም ሆነ ሕገ መንግስታዊ መርህ ወይም ድንጋጌ የለም። ሲቪል አስተዳደሩ ወታደሩን ሊቆጣጠር ሲገባው በተገላቢጦሽ ወታደራዊ ክፍሉ ሲቪሉን አትረባም፣ ሞተሃል፣ አመራር አታዉቅም እያለው ነው፥ ከኣቶ ኣባይ ጸሃይ በተቃራኒ ሃሳባቸውን የገለጹት ሳሞራ የኑስ ታገልኩለት የሚሉትን ሕገ መንግስት በኣደባባይ ኣፍርሰውታል ብለዋል።
ጄኔራል አበበ(ጆቤ)ደርግነት በሁለት ኢ፡ሕገ መንግስታዊና ስርዓት፡የለሽ በሆነ መንገድ ሊከሰት ይችላል።አንደኛው በግላጭ መፈንቅለ መንግስት ማድረግ ነው። ሁለተኛው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ብሎም የኢህአዴግ ምክር ቤት ወይም ፈፃሚዉን መመርያ በመስጠትና በማስፈራራት “እከሌ ሊቀ፡መንበር እንዲሆን እከሌን አዉርዱት” ወዘተ በማለት ሊሆን ይችላል። በድርጅቱ ባለው ሁኔታ ይህ አይቻልም ማለት የዋህነት ነው። የግንቦት ሃያ በዓል አስመልክቶ የተደረገው ፓነል ይህን ለማስረገጥ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብን። ኢህአዴግ ዉስጥ ያለው ችግር ባልተመሰቃቀለና ሕገ መንግስታዊ በሆነ መልኩ ከህዝቦች እና ሌሎች ፓርቲዎች ተሁኖ መፈታት ያለበት ጉዳይ ነው፤ ያለ ምንም የወታደር ጣልቃ ገብነት። በማለት በጽሁፋቸው መደምደሚያ ኣስቀምጠዋል፥፥#ምንሊክሳልሳዊ ሙሉ ጽሁፉን ከዚህ ሊንክ ላይ ያንብቡት። http://www.mereja.com/amharic/499972
sewyew and hamun new yekerew eko kkkkkkkkkkkkkkk
Hey Minilik
Mefenkile mengistun yimokrut yihen?
Yigermal gobez tgrie woyanie be tgrie woyanie liqeyer yichlal blo mesegatu!
Bihonma nuro sergunn tezkar tiyiwalesh neber.
Eyetebale yalew tgrie woyaniewoch liqeyerubn new, eda meTabn new.
Ajeb
nothing is better than weyanes please get rid off them who ever you are
Long live the true General un like the derg generals,General Samora Mahammed Yonus.
I can’t see the difference between them.
በወንድሞቻችን በአባይና በሳሞራ መካከል ምን ልዩነት አለ!? እውነት…የማን ፊት ያምራል? በሚል ካላበላለጥናቸው በስተቀር ሴም ቦቆሎ ናቸው።
yes !!! 40/60 be kenu keseten wedeza yinekakilachew. Hodam like Abate and Mekuriya gedel yigibu!!!!
አሁንስ የሚመራው ማን ሆነና?
Who is civil or who is military? They are all Tegadaly Woyane who came to central Ethiopia wearing plastic sandal shoes and short trousers with long & dirty hairs infested with lice.
Now with no shame you refer your long time friends in Tigray desert who are wearing smart Englad/Italian suits a civil and the rest who took up military uniforms without having formal military course a military. You are funny.
“if wishes were horses beggers would ride it”.Which millitary force would take the power? You mean Samora and some few fake generals?
it is hard situation i can’t believe it i don’t want
to my country
jebe you have betrayed betri haki betri weyanne. beka bihanti zereba koynu adi zigilbet. ata hawna zitewagaekayo dergi diw tefiuka mis hiji tewedadiro zeleka. entay yibihal mesiluka “korbet dorho zeyikon lekota afey ember hilinayis meyta” ayetemelkan zelo. tom tselaetina eyom zerebaka zegawihiwo zelewu. timali dergin kab nisu zeyihishun yilom keyahitin tselemtin ahatka zimeketiwom. nab libina dea.
የሚፈልጉትን አያውቁምና…ተብሏል።
እኛ ኢትዮጵያውያን ግን እርግማን አለብን መሰለኝ እንጅ፣ አንዱ ያነሳውን ሃሳብ ገና አውጥተንና አውርደን ከመገምገማችንና አንድ መቋጫ እስክንደርስ ድረስ ጊዜ ሳንሰጥ፣ በችኮላ ሰውዬውን መዘርጠጥና ያለና የሌለ ስድብና እርግማን ማውረድ ባህላችን እየሆነ ከመጣ ሰነባብቷል።
ምናለ በትግስትና መከባበር ሃሳባችንን ብናቀርብ? በተለይማ፣ በየድረ ገጹ ጀርባ ተከልለን የምንጽፍ ሰዎች፣ ስለወገኖቻችን ጉዳት ተቃዉሞአችንን ለመግለጽ ሰልፍ እንውጣ በሚባልበት ጊዜ፣ ጥላችሁም አይገኝም። በዕውነት ስለ ኢትዮጵያ አገራችን የምናስብና ለሁላችንም የምንፈልጋት አገር እንድትኖረን ፍላጎት ካለን፣ በንጹህ ልቦናና መከባበር ሃሳቦቻችንን መግለጽ ያስፈልጋል።
በሁሉም ነገሮች ላይ ላንስማማ እንችላለን፣ ነገር ግን ቀሪውን ህዝቡ እንዲወስን ዕድል በመስጠት ልዩነታችን ላይ ሳይሆን አንድነታችን ላይ እየበረታን መሄድ ተገቢ ነው።
አደራችሁን፣ ባህላችን ያልሆነውን ስድብና ማዋረድን ብናስወግድ መልካም ነው እላለሁ።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ።
Zem bele,washelam.
Here is what they did. When they found that the military may overturn against them, they brought the top military officials to ward corruption, the top military officials became millions, and when this was not enough they symbolized Samora Yunis as “professor”
እኔ ምለው ሰዉየው የሚቀጥለው ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ካለቀረ ጥርሳቸውን ቶሎ ቢያሰሩ ደግሞም አቻምና
ከእንግሊዝ በፖስታ የተላከላቸውን ዲግሪ ግድግዳ ላይ መለጣጠፍ ቢጀምሩ መልካም ነበር