ክቡር ሚንስትር : ወጥ ጨላፊያችን ልትወልድ ሆስፒታል ገብታለች – እሷን የሚያዋልድ ግብረ ኃይል መቋቋም አለበት፡፡
በሃገር ላይ እንዲህ ይቀለዳል: ጉድ እኮ ነው::
[የክቡር ሚኒስትሩ ሾፌር መኪና ውስጥ ዘፈን ከፍቷል]

- ምን ዓይነት ሙዚቃ ነው አንተ?
- ወደዱት ክቡር ሚኒስትር?
- ያልተጠየከውን ምን ያስቀባጥርሃል? አማርኛ ዘፈን ነው ለመሆኑ?
- አዎ ክቡር ሚኒስትር ራፕ ነው፡፡
- ምንድነው ራፕ?
- ዘመናዊ ሙዚቃ ነው፡፡
- ይሰማሃል የሚለው ግን?
- በሚገባ ክቡር ሚኒስትር፣ እርስዎ አይሰማዎትም?
- ኧረ ምንም አይሰማኝም፡፡
- ስለለመደብዎት ይሆናላ፡፡
- ምኑ ነው የለመደብኝ?
- አለማዳመጡ!
[የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ቢሯቸው ገቡ]
- ፕሮፖዛሉ አልቋል ክቡር ሚኒስትር፡፡
- የትኛው ፕሮፖዛል?
- የትልቁ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል፡፡
- ስለዚህ ቀጣዩ ሥራ ምንድን ነው?
- ያው ፕሮጀክቱን ማን ይገንባው የሚለው መወሰን አለበት፡፡
- እሱማ ተወስኗል፡፡
- ጨረታ እንዲወጣ ማለትዎ ነው?
- የምን ጨረታ ነው የምትለው?
- ማለቴ ይህንን ትልቅ ፕሮጀክት ሊገነባ የሚችል ተቋም ለማግኘት ነዋ፡፡
- እኮ ምን ዓይነት ጨረታ?
- ዓለም አቀፍ ጨረታ ነዋ፡፡
- የኒዮሊብራሊስቶች ድርጅት መጥቶ ሊገነባ?
- የአገር ውስጥ ጨረታም ማውጣት እንችላለን፡፡
- እኮ የማንም ኪራይ ሰብሳቢ ድርጅት መጥቶ እንዲገነባው?
- ታዲያ ማን ይገንባው ክቡር ሚኒስትር?
- እኛው ያቋቋምነው ድርጅት ነዋ፡፡
- ያለምንም ጨረታ?
- ፕሮጀክቱ እኮ የመንግሥት ነው፡፡
- ቢሆንስ ክቡር ሚኒስትር?
- የመንግሥት ፕሮጀክት በመንግሥት ተቋም ነው መገንባት ያለበት፡፡
- ከመቼ ጀምሮ?
- አንተ ለመሆኑ ማን ነው ተቆጣጣሪ ያደረገህ?
- እንዳያስጠይቀን ብዬ ነው፡፡
- ስለእሱ አታስብ፡፡
- እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
- ጠያቂውም መንግሥት ነው፤ መላሹም መንግሥት ነው፡፡
- ሕዝቡስ?
- ለሕዝቡማ ከባድ የቤት ሥራ ሰጥተነዋል፡፡
- ምን ዓይነት የቤት ሥራ?
- የኑሮ ውድነት የሚሉት፡፡
- ግን ክቡር ሚኒስትር…
- የምን ግን?
- አሁን ይኼ ተቋም ይህን ትልቅ ፕሮጀክት ለመገንባት ከዚህ በፊት ምን ሠርቷል?
- ምን ዓይነት ጥያቄ ነው?
- ማለቴ ልምድ አለው ወይ?
- እንዲህ ዓይነት ሥራ እየሠራ ልምድ ካልያዘ፣ እንዴት ልምድ ሊኖረው ይችላል?
- ያው ይኼ ከባድ ሥራ ነው ብዬ ነው፡፡
- ተቋሙ ከባድ የሚባል ነገር አያውቅም፤ ብረት ነው ስልህ፡፡
- እንደ ተረቱ እንዳይሆን ብዬ ነው፡፡
- ምንድን ነው ተረቱ?
- መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ፡፡
- እና እነሱ እንደስማቸው ብረት አይደሉም እያልከኝ ነው?
- ሥጋት ስላለኝ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ምኑ ነው የሚያሠጋህ?
- አቅማቸው!
[ከክቡር ሚኒስትሩ ጋ የቦርድ አባል የሆኑ ሌላ ሚኒስትር ደወሉላቸው]
- ክቡር ሚኒስትር ምነው ከቦርድ ስብሰባው ቀሩ?
- በጣም አፋጣኝ ሥራ ገጥሞኝ ነው፡፡
- ያው አዲሱ ትልቅ ፕሮጀክት ወደ ሥራ እንዲገባ ተወስኗል፡፡
- ማን ይሥራው ተባለ?
- እሱ ገና አልተወሰነም፣ ግን በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡
- ምኑ ነው የሚያሳስበው?
- ያው ፕሮጀክቱ ትልቅ ስለሆነ ማን ይገንባው የሚለው ነዋ፡፡
- ምን ችግር አለው? የእኛው ድርጅት ይገነባዋላ፡፡
- የትኛው ድርጅት?
- ትልቁ ድርጅት ነዋ፡፡
- እሱማ ሕፃን ነው እኮ፡፡
- እኮ ሕፃን ልጅ እንዲያድግ ሥጋውንም፣ ወተቱንም፣ ፋፋውንም መመገብ አለብህ፡፡
- እሱማ ልክ ነው፡፡
- ስለዚህ ይኼ ድርጅት እንዲያድግ ባቡሩንም፣ ግድቡንም፣ ፋብሪካውንም መመገብ አለብን፡፡
- ክቡር ሚኒስትር በቃ አከበርኩዎት፡፡
- ለዛ እኮ ነው ክቡር ሚኒስትር የሚሉኝ፡፡
- እኔማ ለእርስዎ አንድ ቃል ነው ያለኝ፡፡
- ምን የሚል ቃል?
- ብልህ!
[ክቡር ሚኒስትሩ ፕሮጀክቶቹን የሚገነባው ድርጅት ኃላፊ ጋ ደወሉ]
- እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
- ጠፋህ እኮ ወዳጄ፡፡
- ያው በርካታ ፕሮጀክቶች እኮ ተቀብለን ደፋ ቀና እያልን ነው፡፡
- ሥራ በዛባችሁ አይደል?
- ይኸው አገሪቷን እኮ በጫንቃችን ላይ ተሸክመናት ነው የምንዞረው፡፡
- ይገባኛል እኛም ጫንቃችሁ እንዲጠነክር እኮ ነው በላይ በላይ የምናጐርሳችሁ፡፡
- ሌላ የሚጐረስ ተገኘ እንዴ?
- የሚጐረስማ በየጊዜው ነው ያለው፡፡
- ዛሬ ምን ይዘው መጡ ታዲያ?
- ትልቅ ፕሮጀክት እንዲሰጣችሁ አስደርጌያለሁ፡፡
- ውለታዎትን በምን እንመልስ ታዲያ?
- ያው ጀርባዬን ማከክማ እንዳትረሱ፡፡
- ክቡር ሚኒስትር እዚህ የደረስነው እየታከክን አይደል እንዴ?
- ለዛ ነው እኔም ጀርባዬን ማከክ አትርሱ ያልኩት፡፡
- ክቡር ሚኒስትር አሁንማ ጀርባዎትን በእጄ አይደለም የማክልዎት፡፡
- ታዲያ በምን ልታከው ነው?
- በኤክስካቫተር!
- እንዲህ ከሆነማ ሌላም ፕሮጀክት በቅርቡ አጐርሳችኋለሁ፡፡
- ክቡር ሚኒስትር ጉርሻው ላይ ግን ጥንቃቄ መውሰድ አለብን፡፡
- ምን ዓይነት ጥንቃቄ?
- ብዙ አጉርሳችሁን በኋላ…
- በኋላ ምን?
- እንዳታስተፉን!
[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ ቢሯቸው ገባች]
- ሰሙ ክቡር ሚኒስትር?
- ምኑን?
- የክበባችን ወጥ ጨላፊ እኮ ሆስፒታል ገባች፡፡
- ምን ሆና? አደጋ ደረሰባት እንዴ?
- የለም የለም፣ እርጉዝ ስለሆነች ልትወልድ ነው፡፡
- ውይ በጣም ደስ የሚል ዜና ነው የነገርሽኝ፡፡
- ምን እናድርግላት ታዲያ?
- በአስቸኳይ አማካሪዬን ጥሪልኝ፡፡
- ለምን ክቡር ሚኒስትር?
- ግብረ ኃይል መቋቋም አለበት፡፡
- የምን ግብረ ኃይል?
- ወጥ ጨላፊያችንን የሚያዋልድ ግብረ ኃይል!
[የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ተጠርቶ ቢሯቸው ገባ]
- ፈለጉኝ ክቡር ሚኒስትር?
- ስለፕሮጀክቱ እንድናወራ ብዬ ነው፡፡
- ስለቅድሙ ፕሮጀክት ነው?
- አይደለም፣ አዲስ ፕሮጀክት መጥቶልናል፡፡
- የምን አዲስ ፕሮጀክት?
- ወጥ ጨላፊያችን ልትወልድ ሆስፒታል ገብታለች፡፡
- እሺ፡፡
- ስለዚህ እሷን የሚያዋልድ ግብረ ኃይል መቋቋም አለበት፡፡
- እየቀለዱ ነው ክቡር ሚኒስትር?
- የምን ቀልድ ነው? ስማ የእሷን ጉዳይ የሚከታተል ኮሚቴ መቋቋም አለበት፡፡
- አወላለዷን የሚከታተል ኮሚቴ እያሉኝ ነው?
- እህሳ፣ አንደኛው የመልካም አስተዳደር ችግር እኮ ይህ ነው፡፡
- ምን እያሉ ነው ክቡር ሚኒስትር?
- ይኸው ኮሚቴ እንዴት ይቋቋማል እያልከኝ ነዋ?
- ገርሞኝ ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ስማ አንድም እናት በወሊድ መሞት የለባትም እያልን አሁን ለምን ኮሚቴ ይቋቋማል ትላለህ?
- እሺ ምን ዓይነት ኮሚቴ ነው የሚቋቋመው?
- ሦስት ኮሚቴ መቋቋም አለበት፡፡
- ይንገሩኝ እስቲ፡፡
- አንደኛ የገንፎ አስገንፊ ኮሚቴ፡፡
- እ…
- ሁለተኛ የአጥሚት ዝግጅት ኮሚቴ፡፡
- እ…
- ሦስተኛ የዳይፐርና ዋይፐር አፈላላጊና ገዢ ኮሚቴ፡፡
[የገንፎ አስገንፊ ኮሚቴው ኃላፊ ክቡር ሚኒስትር ቢሮ ገባ]
- ለመሆኑ ይኼን ኮሚቴ ለመምራት ምን ብቃት አለህ?
- ክቡር ሚኒስትር ቁርስ፣ ምሳ፣ እራቴን ከገንፎ ውጪ አልበላም፡፡
- ለነገሩ ፊትህ ራሱ እንደገንፎ የተነፋ ነው፡፡
- ክቡር ሚኒስትር የተሰጠኝን ኃላፊነት ለመወጣት ከተማ ውስጥ አሉ የተባሉ የገንፎ እህሎችን ከነዋጋቸው አጣርቻለሁ፡፡
- በጣም ደስ ይላል፡፡
- እና በኤክስፖርት ስታንዳርድ ያለ የገንፎ እህል አግኝቻለሁ፡፡
- ስማ ሥራህን እንዲህ በትጋት የምትሠራ ከሆነ ይኼን ኮሚቴ አሳድገዋለሁ፡፡
- ወደ ምንድን ነው የምታሳድጉት ክቡር ሚኒስትር?
- ወደ ገንፎ አስገንፊ ኮርፖሬሽን!
[የአጥሚት ዝግጅት ኮሚቴ ኃላፊዋ ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ገባች]
- በአማካሪዬ በጣም ተደስቻለሁ፡፡
- እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
- የፆታን ተዋፅኦ ከግምት ውስጥ ያስገባ ኮሚቴ ነው ያቋቋመው፡፡
- ያው ክቡር ሚኒስትር እኔ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ነው ያለኝ፡፡
- ትንሽ ብታብራሪልኝ?
- በአፌ ጁስ የሚባል ቀምሼ አላውቅም፡፡
- ምንድን ነው የምትጠጪው ታዲያ?
- አጥሚት ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- እና ምን ይዘሽ መጥተሻል?
- ያው ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሁሉ የሚበቃ የአጥሚት እህል ተዘጋጅቷል፡፡
- በዚህ ትጋትሽ ከቀጠልሽ ኮሚቴውን አሳድገዋለሁ፡፡
- ወደ ምንድን ነው የሚያሳድጉት?
- ወደ አጥሚት ዝግጅት ዳይሬክቶሬት!
[የዳይፐርና ዋይፐር አፈላላጊና ገዢ ኮሚቴ ኃላፊው ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ገባ]
- ይህን ኮሚቴ ለመምራት ምን ብቃት አለህ?
- ክቡር ሚኒስትር አያስታውሱም እንዴ ግምገማ ላይ ምን ያህል ጊዜ ሽንት ቤት እንደምመላለስ?
- ሽንታም ነኝ እያልከኝ ነው?
- ከሙስናዬ ብዛት በግምገማ ወቅት በሽንት ብቻ መገላገሌ ዕድለኛ ነኝ፡፡
- ስለዚህ ምን አስበሃል?
- ዳይፐርና ዋይፐር ከውጭ ለማምጣት የውጭ ምንዛሪ ስለሚጠይቀን ሌላ ሐሳብ አለኝ፡፡
- ምንድን ነው ሐሳብህ?
- ያ ትልቁ ድርጅት ለምን ዳይፐርና ዋይፐር እዚሁ አገር ውስጥ አያመርትም?
- የሚገርም ሐሳብ ነው ያመጣኸው እባክህ?
- እዚህ ብናመርተው የውጭ ምንዛሪ ማትረፍ እንችላለን ብዬ ነው፡፡
- አሁኑኑ ወደ ምርት መገባት አለበት፡፡
- ሐሳቤን ስለተቀበሉኝ አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ከዛሬ ጀምሮ አንተም የእኔ ልዩ አማካሪ ሆነሃል፡፡
- በምን ጉዳይ ክቡር ሚኒስትር?
- በዳይፐርና ዋይፐር!
Ende be Gebrehayl new yasregezat?kezenam diaper fit
Gedeffa Wako says:
May 17, 2016 at 8:24 pm
ንጉሡ ሞቱማ says:
May 14, 2016 at 6:31 pm
የዳግም አደዎ ዘመቻ
ቁጥር 13 አሰቸኳይ መመሪያ
+-+++++++++++++++
ኢሐድግዬ(1000 ምርጥ ዘር አደዎዎች) ኢትዮጵያን ምን አይነት አገር እንደሆነች ሳያቋት፣ በአልበሽር ጠንቋዮች 17 አህያዎቹን ይዘው በጎርፍ ጋኔን ቤተ መንግስት ተሳካላቸው፣ ሕዝባችንንም በዘር ፓለቲካ እንደ አህያ እንዲያስብ አረጉት። ባንዲራችን ላይ በጋኔኑ አስገዳጅነት ለአለም የመጀመሪያው የጋኔን ምልክት ለውጥ በባንዲራ ላይ አርገው ሕዝባችንን የብሔር እኩልነት ብለው እንደ አህያ እንዶያስብ አረጉን። ኢትዮጵያ ከአለም በፊት 41 ጊዜ በላይ በመፃፍ ቅዲስ የከበረች እና ሂዱ እዛ ኑሩ የኣላ ሰላም አገር ብለው ነብዩ መሐመድ ያከበሯትን አላወቁ የሆን??? የአገራችን ህዝቦች አገራችን በየአቅጣጫው በረሀብ መከራ፣በስደት፣ተዋርደናል፣ታርደናል። ሰለዚህ እስከ መቼ ይህንን ሰቆቃ እየሰማን፣ እየደማን፣ እየተገደልን፣ እየተገለልን፣ ባህር እየወስደን፣ መሪር ሐዘን መቼ ነው በኦሮሚያ፣ በአማራ፣በትግራይ ፣ በሱማሌ፣በደቡብ፣ በጋምቤላ የሚቆመው ??? በመጀመሪያ ለሀያሉ አምላክ ሁሉም እንደእምነቱ ከልብ አምርረን ማልቀስ ያለንበት ወቅት ላይ ነን??? በችግር ለይ ችግር አሁን ብዙ ሺ ሕዝባችን በየቤቱ በጠኔ እያለቀብን ነው። ነገ ደግሞ በሚሊዮንዎች በረሐብ ሊያልቁብን ነው። ቀጥሎ በኃላፊነት ምን ለአገራቹ ስራቹ ተበሎ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚንጠየቅበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። አዎ ከኢትዮጵያ አፈር ላይ መወለድ ፣ ኢሕአዴግ በዘር ከፋፍሎ የጨረሰን ለማከም በመተማመን ተራማጅ የአገር ውስጥ አሮሞ ኢትዮጵያዊያን የጋራ ጠላታችን ጋኔኗ ኢሕአዴግ ብቻ ነች ብለን ከሌሎች ወድ ኢትዮጵያዊያን ጋር የዱሮ ፈቅራችንን መልሰን በጋራ በማንዴላን ራዕይ የዘርን ፓለቲካ እጥፈተን እንድ ኢትዮጵያ ብለን ወደ ዋናው መንገድ ለመሰዋትነት ተዘጋጅተናል። አንዳንድ ሆዳም ኦሮሞዎች በተለያዩ ጊዜያት የራሳችንን ህዝብ አሰፈጅተዎል። በአንፃሩም እንዲሁም በአማራ፣ትግራይ ወዘተ አስፈጅተውናል። 1000 አደዎዎቹ አፉን አፍነው ሌላውን የትግራይ ህዝብ የከፋ የመረረ በደል አድርሰውበታል። አሁን ደግሞ ጥላሽት የተቀባውን የመጨረሻውን ግንቦት 20 ሊያከብሩት ነው። ጠ/ሚሩ ህዝቡ ነቅቷል በቃ ይህንን አንብበው እያላቹ ሳቅ እያፈነኝ ነው፣ አናንተ እየሰማችሁ “ስጥ” እንግዴ ትሉኛላቹ እናንተ ምን ቸገራችሁ ቆዳዬን ይጭነቀው እንጂ አሉ። በ25 አመት ውስጥ ከ10ኘ ክፍል ተስፋ ቢስ አርጎ ያባረራቸው ወጣቶች ፈክሻውን እየጠበቁ ነው።
1ኛ፣ የኢሕአዴግ ስላዬቸ እና ጦሩን አብዛኛውን ሰለ ስራ አስመስለው ለወገኖቻችው እና ለአገራቸው ሲሉ እንዲስሩ ታዘዎል።
2ኛ የኢህአዲግ አባላት ዝርዝር ፣ የኤፈርት በአለም ዙሪያ የለው ዝርዝር በእጃችን ገብቷል። በእስር ቤት ውስጥ ወገንን እያሰቃዬ ያሉት ስም ዝርዝር ደርሶናል። አፈቀላጤ ጌታቸው ረዳ መሽገህ ኢሳትን የምትሰማበት ቦታ ላይ ከጀርባህ ከች እንላለን።
3ኛ ሕዝባችን ማንኛውም ንብረት ጊዜ ውል እንዳይገባ። ባንኮች ተገዳጁ የምታረጉትን መረጃ ያዙ ዘራፊዎችን ከገቡበት ገብተን ነገ ኢትዮጵያዊ ለፍርድ ያቀርባችኃል። የኢትዮጵያ እዳ በጤፍ ቁጥር ነው።
4ኛ ኢትዮጵያ የምትፈልገው በእኩል የሚያስዳድር መሪ ብቻ ነው። ሕዝባችን ለሽግግር ለውጥ ተዘጋጁ ተራማጅ መረዎቻችን ደ/ር ብርሀኑ፣ ጄ/ር ከማል እንዲሁም አቶ ኦባንግ ለህዝባችን የቅድመ ሸግግር ሥርአት መረጃውን በኢሳት ላይ አገሪቷን ወዲያውኑ የሚረከበው ሃይል አስቸኳይ መረጃ ለህዝባችን ይተላለፈል።ጉዞ ወደ ፈት ከተረማጆች ኢትዮጵያዊያን ጋር።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር። ንጉሡ ሞቱማ ኦ.ማ.
[Reply]
Reply
Geday Hagos says:
May 14, 2016 at 6:34 pm
We proud of u connected all Ethiopians together. We are united now more than anytime.
Viva Negussu.
All trash Adowas play game on
Tigrians.
[Reply]
Reply
Bertukan says:
May 14, 2016 at 6:43 pm
We need such progressive united view on 21st century.
Thank you Negussu for you come in from Oromoia such great impressive connection under one Ethiopian. Great man and Great postive mind.
[Reply]
Reply
Sammy P says:
May 15, 2016 at 12:31 am
Ethiopia is the “least” reported country in
Africa compare to south Africa , Nigeria , Kenya ,
Egypt , Angola , Zambia , Burkna Faso , Uganda and
Ivory cost . Its not a bad record in respect .
[Reply]
Reply
G,Michael H says:
May 15, 2016 at 12:38 am
My brother Sammy thank you for your comment
you are absolutely right Ethiopia’s rank is
much better than any country in the world .
Ours is very insignificant .
[Reply]
Reply
መርጋ ኃይሌ says:
May 15, 2016 at 1:17 am
ሆዳምቹ በግለሰብ ኪስ ሲምላ ዝም በሉ ኢትዮጵያ እየለማች አየአደገች ነው ይላሉ ግን በየአመቱ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን በእርዳታ እና በብድር ወደ አገር ይገባል። የአንድ አመት ብቻ መንገድ ሰርቶ አባይን ገድቦ ይጨርሳል። የ24አመቱ ሆዳምቹ ኪስ ይገባል እንደተባለው ማስረጃው ተገኝቷል ሂሳቡ ይሰራል በነፃነት ቀን ላይ ሩቅ አይደለም።
ያንን ሁሉ የቻይና እንደ ጤፍ ያለውን እዳ ማነው የሚከፈለው?????????
[Reply]
Reply
siraj says:
May 15, 2016 at 3:33 am
@ngusu motuma you are not ngusu motuma you are the ortodox yetenkay zer.oromia is for oromo.yedebtera zer.viva oromia.
[Reply]
Reply
Gedeffa Wako says:
May 15, 2016 at 4:34 am
Great Negussu bright mind works for all except 1000 Adowas.
[Reply]
Reply
Tolla says:
May 15, 2016 at 9:00 am
oROMO BILO POLITICA AWRI .
DENGAY IRASOCH . iNANTE INA
WAHBBIST YEMETAWKUT SEAT MEBDAT
BICH NEAW . AFER BILU
[Reply]
Reply
Alo shokie says:
May 15, 2016 at 9:27 am
Siraj is tefa gmat gebreb ke eritrea
yih luTi abatu gebreb orthodox new.
Kdo woim selmo new orthodox misadeb.
Lenegeru be qiTu sibeda hulemenaw zurobet new
[Reply]
Reply
ገላን ወርዶፋ says:
May 15, 2016 at 12:31 pm
አሮሞ ማለት ምን አይነት ቀጥተኛ ትውልድ የሆነ ካመረረ የማይመለስ ፍቅርን ሰጥቶ መቀበል የሚችል ነው። ከላይ ቶላ እና ሲራጅ የሚባሉ የሚፅፍት ነገር ምን የህል ከገማ ጭንቅላት እና ሆዳምነት የወጣ ነው። ዳሩ ግን ሊታረድ መጨረሻ ሰአት ላይ የደረሰ
ዶሮ ብዙ ይጮሃል ይባላል። ጉድ ነው ዘንደሮ የኦሮሞ ልጆች ከሌሎቹ ውድ ኢትዮጵያአዊ ጋር እትብታችን ይፈረደን። ከፈፈሎ በዘር መግዛት አበቃ። ሁላችንም ኢትዮጵያዊ ህብራችን ነው አስከ መጨረሻው ትውልድ ደረስ። ከእናንተ ጭንቅላት የላቀ ምላጭ የሆኑ በየአቅጣጫው በተጠንቀቅ በየከፍለሀገሩ ይገኛሉ። ጎበዝ ጀግና የአምቦ ውድ ኮራችን በኢትዮጵያውያን የሚኮራ አደረጃጀት ተከትሎ ነው። ወደ ኋላ መየት የለም በጅግኖቹ ወድ መሪዎቻችን ደ/ር ብርሀኑ፣ ጀኔራል ከማል፣ ወድ የትግራይ ነፃ አውጪ ታጋዬች አገር ውስጥ ካለው 30 ሚሊዮን ወጣት ኃይል ጋር ወደፈት ብለናል።
ሞኛቹን ፈልጐ ከፋፍሎ በዘር መግዛት አበቃ፣ አሮም አንዱ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ነው።
[Reply]
Reply
አህመድ መኑር says:
May 15, 2016 at 1:55 pm
መልስ ለሲራጅ
ኦሮቶዶክስ ሐይማኖት ከኢትዮጵያ ታረክ እና ፈደል ባለወረለታነች። ነብዪ መሐመድ እኮ አላ አስመልክቶአቸው እኮ በኦርቶዶክስ ደንብ በሚመሩት ንጉስ ነጋሢ ዘመን ነው። ሂዱ እዛ
ኑሩ ብለው መልእክተኛ የላኩት ና መልክተኞቹም ነብዪ ያሉትን ቃል እውነት መሆኑን አረጋገጡ። ዛሬ ዛሬ ኦርቶዶክሱንም በተሐድሶ ስም እነ ታምራት ላይኔ አመሱት።
ኦርቶዶክስ ሐይማኖት ለኢትዮጵያ እስለምና ተከታዮች ጌጣቸው ነች በሷ የመጣብንን አንምርም እኛም እነሱም በፍቅር አይነ አንድ ነን።
[Reply]
Reply
ፈጤ ከድር says:
May 15, 2016 at 3:24 pm
እንወደሀለን አህመድ ሙስሊሙን ሕዝባችን ለ ኦርቶዶክሱ በመግለፀህ።
[Reply]
Reply
ገብሩ ግርማይ says:
May 15, 2016 at 4:22 pm
ወንድም እና እህት ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ሁላቹንም በፍቅር እንወዳቹሀለን። በኢትዮጵያ ጥላ ስር ነው ያለነው በኢትዮጵያችን ቀልድ የለም። ጋኔኖቹንም እስከ መጨረሻው ጠራርገን እናጥባቸዋለን።
[Reply]
Reply
Abay says:
May 15, 2016 at 6:45 pm
All of woyanes will be under arrest soon because They are thieves, killer and mafias. Do not expect good things from those canibalse.
[Reply]
Reply
ሞላ አስግዶም says:
May 15, 2016 at 8:49 pm
ማፈሪያው ጌታቸው ረዳ ጦርነቱም እና ጎርፉ ከሻቦያ የተላከ ነው አልክ። ሌባ ነህ ሆሌ መሸገህ ኢሳትን የምታዳምጥበትን ሁሉ የነፀ አውጪዎች ጎርፍ ትንሽ ቀን እየጠበቀ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ጉዳን በቅርብ ቀን ይወራችኃል። የኢትዮጵያ ህዝብ አንጥሮ አውቋል የሻዕቢያ መንግስት ከወያኔ ይልቅ በተግባር እንደሚጨነቅ አሰወቋል። 90 ሚሊዬን ኢትዮጵያዊ 1000 አደዋ ሻርሙጦች 100% ይቻላል። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!!!!!!!!!!!
[Reply]
Reply
Eyasu says:
May 15, 2016 at 11:09 pm
Tilik sew!!Endihem aynet sew ale leka… yante aynet zega new tesfaChen yanureh.
[Reply]
Reply
Eyasu says:
May 15, 2016 at 11:16 pm
Ahmed Menur,
Tilik sew!!Endihem aynet sew ale leka… yante aynet zega new tesfaChen yanureh.
[Reply]
Reply
ሳ.አ says:
May 16, 2016 at 2:31 am
ለምን መጡና ነው ዛሬ ታላቆን ኢትዮጵያ ሕልውና አደጋ ላይ ጥለው ገንዘብ፣ሃብት ባሃብት ሆነው ጉበቱ በእጃቸው የድንበር መሬት ለሱዳን ካሳ መስጠታቸው ጎንደርን መሬት የትግራይ ሕዝብ ነው አይደለምን!
[Reply]
[Reply]
Reply
Abay says:
May 17, 2016 at 9:38 pm
Don’t expect good things from devil. TPLF means simply a collection of mad , canibalse , killers and mafia groups. The only solution to avoid this cancer from our motherland Ethiopia , we have to stand together
[Reply]
Reply
kiddi kuddi says:
May 18, 2016 at 2:10 am
zeraf……..zeraf
[Reply]
አማራውን በማፈናቀል ወንጀል የሚፈለጉት የቤንሻንጉል ጉምዝ ርእሰ መስተዳደር አቶ አህመድ ናስር ከዚህ ዓመት በሞት ተለዩ፡፡ ስንት አማራዎች ገደለ፣አስገደለ፣የተፈናቀሉትስ የትና እንደት ይገኛሉ?
አቶ አህመድ ናስር የተወለዱት እናታቸው አርጎባ፣አባታቸው ሱዳናዊ መሆናቸውን ስንት ሰው ያውቅ ይሆን ? ይህ ሰው ስልጣን የተሰጠው አማራን ለማጥፋትና ለመግደል ይመስላል ከመተሃራ አሶሶ ሂዶ ኢትዮጵያዊያንን ከሃገራቸው ያባረረውና ያፈናቀለው፣የገደለው፣ያስደገለው ብቻ ስንት ሰው እንደገደለና እንዳስገደለ ትክክለኛ እንደሆነ መርጃ አስቀምጡልኝ ይህች ሀገር መቼም እንደዚህ ሁና አትቀርም ፈጣሪም ኤርሳትም
በሃያ አምስት አመታትና ከዚያ በፊት ስንት አማራዎች በወያኔና በመሶሎቹ ተገደሉ ዛሬስ ለመገደልስ ያዘጋጅቸው እነማን ናቸው?
አማረውን በማደን፣በማሳደድ፣በማፈናቀል የሚገኘው ውጤት ምን ይሆን? ሂሳቡንስ ማን ያወራርዳል ትላላችሁ? በሚስጥር የተገደሉት አማራዎች ማፈላለግ አለብን መተባበር የግድ ይለናል!
ጌቱ