በብኣዴንና በኦሕዴድ ካድሬዎች ላይ የሕወሓት የበላይነት በስልጠና ሽፋን የሚቀጥለው እስከመቼ ነው?
በብኣዴንና በኦሕዴድ ካድሬዎች ላይ የሕወሓት የበላይነት በስልጠና ሽፋን የሚቀጥለው እስከመቼ ነው?
#Ethiopia #EPRDF #TPLF #ANDM #OPDO #MinilikSalsawi #Change
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ጸሃይ የሚሞቅ ውሻ ሁሉ ሞኝ የሚመስላቸው ሕወሓቶች ካለፉት ሳምንታት ጀምረው ለሶስት ወራት የሚቆይ የኢህአዲግ ከፍተኛና መካከለኛ የአመራሮች ስልጣናን ግምገማ በመቀሌ አስጀምረው የሕወሓትን የበላይነት በሃይል ለመጫን እና ለማሳመን ካድሬዉም ሄዶ ሕዝቡን እንዲያሳምን ለማድረግ በስልጣና ሽፋን እየተውተረተሩ ይገኛሉ::ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከኦሕድድ የተወጣቱ ካድሬዎች በተወሰኑ የብኣዴን እና ሕወሓት ካድሬዎች ታጅበው ስልጠና እና ግምገማ ላይ ሲሆኑ ዋናው አላማ በኦሮሞ ክልል የተነሳውን ሕዝብዊ እንቅስቃሴ ዳግም እንዳይከሰት ታዛዥ እና ሕዝብን የሚያኮላሹ ካድሬዎችን በመፍጠር ለሕወሓት ተገዢ የሆነ ትውልድ ማፍራት ነው::
ኦሕደዽ እና ብአዴን አለቃቸው ሕወሓት ያዘዘውን በመፈጸም የሚረኩ ጥርቅሞች ናቸው።ከተለያዩ ክልሎች ተወጣጥተው የሚሰለጥኑ ካድሬዎች ቢኖሩም አንደኛው ቡድን በባህር ዳር በግምገማ እና ስልጣና ስም እየታሸ ይገኛል::ዋና አላማው በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የሚነሱ ተልእኮዎችን በማኮላሸት በሕወሓት ቁጥር ስር ለማዋል እንዲሁም ሕወሓት ደርግን በመደምሰስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለውለታ እንደሆነ በማሳየት ለሕወሓት የበላይነት ስኬት የታቀደ ስልጣና እና ግምገማ ነው::

የቀድሞውን ወታደራዊ ስርኣት ለመጣል የአሁኑን የሽምቅ ሽብራዊ መንግስት ለማንገስ በበረሃ ትግል የተሳተፉት የኢሕኣዴግ ድርጅቶች በሃገሪቱ የትግል ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው::በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስራትን ለማስፈን እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ታግለን ህዝባዊ ነጻነትን እናረጋግጣለን በማለት ጫካ የተደባለቁት ድርጅቶች የትግራይን ህዝብ ነጻ በማውጣት ታላቋን ትግራይን እፈጥራለሁ ያለውን ሕወሓት የትግሉ ስኬት ሲከሽፍበት ኢሕዴንን እና ኦሆዴድን በመንተራስ ተረማምዶ ለስልጣን ከበቃ 25 ድፍን አመታትን አስቆጠረ::ከዘላለም ባርነት የአንድ ቀን ነጻነት አግኝቶ መሞት እንዴት የተሻለ መሆንን መገንዘብ ብስለት ሲሆን ለሌሎችን ከባርነት የማላቀቅ አንዱ መፍትሄ ነው::
የኢሕዴንን እና የኦሕዴድን የትግል አስታውጾ ላማኮላሸት እና ከታሪክ ሂደት መስመር ለማሳት የተጠቀመባቸው ዘዴዎች እና ወታደራዊውን እና የደህንነቱን ተቋም በአንድ ብሄር በማጠር አባል ድርጅቶቹ እና አባላቱ መላወሻ እንዲያጡ ሲሰራ በአደባባይ ታይቷል::ከአቶ ታምራት ላይኔ የፖለቲካ ጠለፋ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ቁጥራቸው ይህ ነው የማይባሉ የኢሕዴን ታጋዮች እና ካድሬዎች በተለያዩ የወንጀል ልጣፎች ከያሉበት ተጠልፈው ወደ ሞት እስር እና ስደት ተግዘዋል:: የኦህዼድ አባላትንም እንዲሁ በመጥለፍ በፖለቲካዊ የኦነግ ታርጋ በማሰር በመግደል እና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች በማሸት አንደበታቸውን አሽጎታል:: ይህ የሕወሓት ስራ ማንም የሚያውቀው እና ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው:: የአማራውና የኦሮሞው ህዝብ ኢሕዴን/ብኣዴንን አይተው ኦሕዴድን አይተው እንጂ ለሕወሓት ሲሉ የእትዮጵያን መሬት በመምራት አልተባበሩም ስለዚህ የብኣዴን እና የኦሕዴድ አመራሮች እና ካድሬዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ ትግሉ ሕወሓት ብቻ የመራው ያደራጀው ያሸነፈው አለመሆን እና የድርጅቶቹም ድርሻ እኩል መሆኑን ነው:: #ምንሊክሳልሳዊ
“የብኣዴን እና የኦሕዴድ አመራሮች እና ካድሬዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ ትግሉ ሕወሓት ብቻ የመራው ያደራጀው ያሸነፈው አለመሆን እና የድርጅቶቹም ድርሻ እኩል መሆኑን ነው” ትክክል።
Yehulum ethiopian ETHIOPIAWINET netsanetna equlnet siregaget
Eneko yemigermegn. OPDO ena ANDM yalut sewoch chinkelat yelachewm enate gin alachihu. Yenesu mekari yehonachehut enante enbeltalen bayoch selehonachihu new aydel?
መከራዋ የበዛ ሃገር ስንት አመት ትድማ (በጦርነት፣በድርቅ፣በርሃብ፣ በድህነት፣ በስደት፣በአፈና በጭቆና )ሂሳብ እያወራረደ ያለችና ሃገርና ሕዝብ ምን ይሆን ጥፋታችን ? ለመሆኑ ብአዴንና ኦሕዴድ የሚባል በወያኔ የተጠፈጠፋ ቅጥረ ነፍሰ ገዳዩች ናቸው፡፡
ዘሩ
የቀድሞው የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚ/ር ቶኒ ቢሌር አዲስ አበባ ፓያሳ መታየት በየት ገቡ ለሚለው በአስመራ በኩል አድረገው በአድግራት በመቀሌ፣በዴሰ አዲስ አበባ ገቡ፡፡
ይህ ሰው ለመሆኑ ምን ጉዳይ ኑሮት ይሆን መጠርጠር ተገቢ ነው የኢትዮጵያ ጉዳይ ለአውሮፓውያን እስከ አሁን እንደማይተኝና ተንኮላቸውን በምስራቅ አፍሪካ ላይ ያሰቡት ነገር አይጠፋምና እስቲ ለምን መጡ ሰውዩው እኮ ቀድመው ፓያሳ መተየታቸው የሃገሪቱን ደህነት መድፈር ነው! አዎ ደፍርናል የእንግሊዞች የስለላ ድርጅት ፍተሻ ማድረጉ መታወቅ አለበት እንጅ ለበጎ አድራጎት ስራ አለመምጣታቸው የምዕራባዊያን ድብቅ አጀንዳ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ መሆን አለበት በ1997 ዓ.ም ምርጫ ይህ ሰው ምን እንደሰራ እስከ አሁን እንቆቅልሹ ስንት ገንዘብ ይዞ እንደመጣ የሚያውቁት
1- ወያኔ
2- አሜሪካን
3- እስራኤሎች
4- ግብጾች
5- ታማኝ የሆኑት ብአድን ሌሎችም መሆናቸው አንድ ኢትዮጵያዊ በትክክል አስረድቶናል
ይህ ሰው ለምን ኢትዮጵያ መጣ?
ሳተናው አሊ