በሱልልታ እና በጅማ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ቀጥሏል።

በሱልልታ እና በጅማ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ቀጥሏል።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Sululta‬ ‪#‎Jimma‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎AddisAbaba‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የኣዲስ ኣበባ መግቢያ በሆነው የሱልልታ ከተማ እና በጅማ ዩንቨርስቲ ውስጥ ከፍተኛ የተማሪዎች የተቃውሞ ድምጾች መሰማታቸው ታወቀ፥የወያኔው ኣገዛዝ በኦሮሞ ወጣቶች ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እስር እና ኣፈና ቀጥሎ በሚገኝበት በዚህ ወቅት በይቅርታ ሽፋን የሚሰሩ መንግስታዊ ሽብሮች በርትተዋል።ተቃውሞው ኣሁንም የወያኔ ኣስተዳደሮች ሊመልሱት ያልቻሉ ሲሆን በሃይል ተጠቅመው ወጣቶቹን መደብደብ ማሰር ተያይዘዋል።

በዚህም መሰረት ከባድ መሳሪያ የታጠቁ የኣግዓዚ የሕወሓት ሰራዊት ኣባሎች የጅማ ዩንቨርስቲ ገብተው ተማሪዎችን በመደብደብ ከባድ ጉዳት ኣድርሰዋል፥በፎቶው ላይ የሚታየው ሕክምና አየተሰጠው የሚገኘው የጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪ ነው፥ እንዲሁም በሱልልታ በርካታ ወታቶች የተደበደቡ ሲሆን ሰባት ተማሪዎች በወታደሮች ተይዘዋል ኣምስት ወንዶች አና ሁለት ሴቶች ሲሆኑ ወታደሮቹ ተማሪዎችን ሲያንገላቱ አና ሲያዋክቡ ተስተውሏል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

12 Comments on “በሱልልታ እና በጅማ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ቀጥሏል።”

  1. ከባድ መሣርያ የታጠቁ?
    ከባድ መሣርያ እኮ እነ መድፍ፦ ዙ23፦ ቢ ኤም እና ዘመኑ የፈጠረው ተምዘግዛጊ ሚሣይል (ሮኬት) ወዘተ
    . ናቸው። እንዴት ለተማሪዎች ከባድ መሣርያ? የክላሽን ጥይት አለቀ እንዴ? ወይስ ከባድ ብላችሁ ልታካብዱ?

  2. do you know why weyane is coming belive me to destoryed Ethiopian unity! always they are narrow minded!

  3. Negussu Motoma says:

    April 5, 2016 at 8:13 pm

    የዳግም አደዎ ዘመቻ
    ቁጥር 8 አሰቸኳይ መመሪያ
    +-+++++++++++++++
    ኢሐድግዬ(1000 ምርጥ ዘር አደዎዎች) እና ሆዳቸውን የመለኩ በቺሎቹ እስከ አሁን ሕዝባችንን በጭካኔ መግደሉን እና ስልጣኑን ላለመልቀቅ እንደ አበደች ውሻ ሆነዎል። ኢትዮጵያን ምን አይነት አገር እንደሆነች ሳያቋት፣ በሱዳን 17 አስማተኞች አህያዎች ይዘው በጎርፍ ጋኔን ቤተ መንግስት ተሳካላቸው፣ ሕዝባችንንም በዘር ፓለቲካ እንደ አህያ እንዲያስብ አረጉት። ኢትዮጵያ 41 ጊዜ በላይ በመፃፍ ቅዲስ የከበረች እና ሂዱ እዛ ኑሩ የኣላ ሰላም አገር ነች ብለው ነብዩ መሐመድ ያከበራት አገር ነች። አበው እንደሚሉት ይቺን የመከራ ጊዜ ካለፈን ኢትዬጰያዊ መሆን እንደ ሎተሪ የሚታይበት ቀን በቅርቡ ይደርሳል። የአገር ውስጥ ኦርሞዎች የዘር ፓለቲካ ነቃንብሸ ኢሐዲግዬ ብለውታል። የተደራጅው ንኡስ ኮር በወልቃይት፣ በትግራይ፣ በሐረ ር ፣ በአምቦ እና በመተከል ኮሩን ዘርግቶ በየአንዳንዱ ከተማ ሠራዊታችን ገብቷል። ሕዝባችን አየሞተ ነው በኢሕአዴግ አጋዚ እና በረሐብ እርዳታ የሚሰጠው ቅድሚያ ለሆዳሞች ብቻ ከዚያ በሚድያቸው ረዥሙን ይሉኝታ የሌለውን ምላስ ይለቁብናል። የሚከተለውን ተጨማሪ መምሪያ ሕዝባችን ተግባራዊ እንዲያረግ እንገልፃለን።
    1ኛ፣ እኛ የኢሕአዴግ ስላዬቸ እና ከታች ያለውን አብዛኛውን ፈሸካው ሲነፈ የአገር ግዴታ የሚሰሩትን አዘጋጅተን ጨርሰናል። ለምሳሌ በመተማ የሰፈረውን ጦር እንደቋንቋው መረጃውን አግኝቶ ከወገኔ ጋር ብሎ ኢትዬጰያዊነቱን አስቀድሞ በተጠንቀቅ ይጠብቃል። የጦር መሪዎች ስንት የሰረቁት ዶላር አስቀምጠው ጦር ሜዳአይሞክሩትም።
    2ኛ፣ ሕዝባችን በዚህ ጊዜ ያለውን ከአርበኞች ግንባር፣ ኢሳት፣ የአቶ ኦባንግን ድርጅት አንገብጋቢ ወቅት ላይ ስለሆን መርዳት አለበት። አቶ ኦባንግ ሰሞኑን ከዘር ነፃ የሆነ ተራማጅ አትዬጰያን የሚያሰቀድም በሙሁራኖች የተጨመቀ ሰለለውጡ ካርታ እንዴት አውራ ሸግግር መሪ እንደሚጓዝ እና በቋሚ ስርአት ለውጥ መረጃ ይሰጣሉ።
    እኛ አሁን ለወሬ እና ለዘር ፓለቲካ ጊዜ የለንም የፈለገ መሪ በቋሚ ሰርአትን ተከትሉ እኩል ማስተዳደር የሚችል ብቻ ነው የምንፈልገው ከዚህ ውጭ የሆናችሁ የራሳችሁን ሙያ ቀጥሉ እንጂ የማይሁን ቃላት አቁሙ እና ተራማጅ የለውጥ ሐዋሪያዎችን እንድትደግፍ እናሳስባለን።
    3ኛ፣ ሕዝባችን እንዲሁም የ አክሱም ትግራይ ጭቁን ወገኖቻችን፣ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አክብሮ የሰጣትን የሙሴ ፅላት አቡነ ማትያስ ሌሎችን ጳጳሳት ጉባኤ በማግለል ከገንዘብ አፍቃሪ ተሐድሶዎች ጋር በመሆን የውሸት ተቦት አስቀምጠው፣ ትክክለኛውን ለመሸጥ ውሉን ጨርሰዎል ከዚህ ቀን ጀምሮ አቡነ ማቲያስ እንቅልፍ የላቸውም፣ የሚሰሩትን ምንም አያቁም። የግፍ ወንበር በተራው እንደዚህ ያረጋል።

    4ኛ አቡነ መርቆርዮስ በሕገ ወንበር ላይ ስላሉ፣ የአባቶቻችን ድጐማ ና ቀኖና አንዲት ሳት ቀይር ለህዝባችን አንድነት ቡራኬ እና ጥሪ እንዲያደርጉልን በማክበር እንጠይቃለን። ይህንን ስንል የአቡነ ጴጥሮስ መስቀል እና ደም ከፊቶት ቆሟል ማለታችን ነው!!!
    የትግሉ መሪ እስከ ሽግግር ድረስ የተግባር ጀግኖቹ ዲ/ር ብርሀነ ነጋ እና የጦር አስተባባሪ አዛዥ ጀነራል ከማል ገልቹ። ለህዝባችነው መረጃውን አስተላልፍ በተዋረድ ትእዛዝ ተቀብላችሁ በፍቅር እንወጠዋለን። የኢሕአዴግን ስርአት እርቃናው ላይ አድርሰናል በመርᎊ ትንሽ መንካት ነው የቀረን። ትግሉ ወዲያውኑ ሲጀመር የአገር ውስጥ መገናኛ ስለምንቆጣጠር ከህዝብ ጋር የሆነ ትግል ቢበዛ 30 ቀናት ብቻ ነው ።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር!!! ንጉሡ ሞቱማ አምቦ ኮር

    [Reply]

    Reply

  4. ቆስሎ ሆስፒታል የተኛው ልጅ ከተወጊ ሄሊኮፕተር በተተኮሰው ሮኬት ተመቶ ነው? በቃ ወሬ ጠፋ?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*