ታግዶ የነበረው የማህበረ-ቅዱሳን ዐውደ ርእዩ እንዲታይ ተፈቀደ

ዐውደ ርእዩ እንዲታይ ተፈቀደ – በዲ/ን አባይነህ ካሴ
 
ታግዶ የነበረው ዐውደ ርእይ እንዲታይ መፈቀዱ ተሰማ፡፡ የእገዳ ትእዛዙ የተሰጠው ከማን እንደኾነ በተደጋጋሚ ለማወቅ የተደረገው ጥረት በመጨረሻ ተሳክቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የማኅበሩ አመራር ባደረገው ውይይት መፈቀዱ ዐቢይ የደስታ ዜና ነው፡፡ ከደኅንነት ስጋት ጋር በተያያዘ እንደታገደ ይገመታል፡፡ ለጊዜው ያገድሁት እኔ ነኝ ብሎ የሚቀርብ አካል አለመኖሩ ግራ አጋብቶ የነበረ ቢኾንም ይመለከታቸዋል ተብለው ከተገመቱት የመንግሥት አካላት ጋር የተደረጉ ውይይቶች መፍትሔውን ወልደውታል፡፡
 
በእርግጥ አሁን መፈቀዱ ብቻውን የት፣ እንዴት እና መቼ ይታያል? የሚለውን አይመልሱ ይኾናል፡፡ ምክንያቱም የዐውደ ርእይ ማዕከሉ ቀደም ሲል በተያዙ የትንሣኤ ዋዜማ የግብይት መርሐ ግብሮች እንደተጨናነቀ ስለሚታወቅ፡፡ ይሁን እንጂ የዝግጅት ልዑካኑ እስከመጨረሻው ያሉትን አማራጮች ለማየት እና ሙከራ ለማድረግ ወዲያ ወዲህ ተፍ ተፍ እያሉ ይገኛሉ፡፡ ከተሳካላቸው በወርኀ ጾሙ ጊዜ ውስጥ ለማሳየት የሚቻልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ይህ ካልኾነ ግን በበዓለ ሃምሳ እንዲታይ ለማድረግ ይታሰባል፡፡
 
ረድኤተ እግዚአብሔር ታክሎበት ማዕከሉን ቀደም ብለው ከያዙት አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ጥቂት ቀናት ተገኝተው አሁን ቢታይ እንዴት ደስታችን ሙሉ በኾነ፡፡ ይኽም ባይኾን ግን መፈቀዱ ብቻውን የሚሰጠው ትርጉም እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡ የእገዳው መነሣት የሚሰጠው የትርጉም ጓዝ ከማስደሰትም ባለፈ መልእክትም አለው፡፡
ከሁሉ በላይ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ዓላማ እና ምኞት እጅግ ከፍተኛ ኪሣራ ውስጥ መግባቱ ስንመለከት እና ጨብጠነዋል ብለውት የነበረው ጉዳይ ድሮውንም ቢኾን በእጃቸው እንዳልነበረ ማስመስከሩ፣ እነዚህ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን (የሩቆችን ትትን የቅርቦች መኾናቸውን ሳንዘነጋ) ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚያንገበግባቸውን የማኅበሩን ውድቀት ሊመለከቱ ቀርቶ ተቃራኒው ሲኾን ለማየት ሲገደዱ ወድደን ብቻ ሳይኾን ፍቅሩ አገብሮን እግዚአብሔርን እንድናመሰግነው ያደርገናል፡፡
ከአሁን አሁን ገፋነው ሄደልን ወጣልን ብለው ሲመኙ እግዚአብሔር የበለጠ እግሮቹን በጽኑ ዓለት ላይ ሲያቆማቸው እያዩ፣ ጨብጠነዋል ሲሉ እያመለጣቸው፣ አበቃለት ከሰመ ሲሉ እየፈካባቸው ታላቅ የራስ ምታት ኾኖባቸዋል፡፡ በተለይም በሐራጥቃ አሰላለፍ የሠለጠኑ እና እንደ ቅድሚያ የትግል አማራጭ አድርገው የቀየሱት የማኅበሩን ጥፋት ማየት እንደ ግብ ይዘውት ይልፉ እንጂ ጠብ አላለላቸውምና፡፡ አልገባቸውም እንጂ እየታገሉ ያሉት ከአንድ ማኅበር ጋር አይደለም፡፡ ትግላቸው ስንት የመከራ እና የግፍ ዘመናትን አልፋ በእሳት እየተፈተነች ለእሳቱም እሳት የኾነችውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ እርሷ ደግሞ ከምድር እስከ ሰማይ የተዘረጋ የማይነቀነቅ መዋቅር ያላት ናትና በአልፎ ሂያጆች አትበገርም፡፡
ሐራጥቃዎች ሺህ ጊዜ ጨበጥነው ሲሉ እልፍ ጊዜ የሚያመልጣቸውን ትግል በመጀመራቸው ጸጸታቸው እየበረታ ኪሳራዎቻቸውን በመቁጠር ላይ እንዲጠመዱ አድርጋቸዋለች፡፡ ሰልፉ የእግዚአብሔር ነውና!
ሁለተኞቹ የቅርብ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን አዝማደ ሙሰኞች ሲኾኑ የእነርሱም ጥረት ሌላ ነበረ፡፡ ጊዜ የሰጠው ቅል እንዲሉ ድንጋይ ለመስበር ወቅታዊ የሥልጣን ቁመናቸውን በመጠቀም ዐውደ ርእዩ እንዲታገድ የአቋም መግለጫ እስከማውጣት ደርሰው ነበረ፡፡ ሰልፉ የእግዚአብሔር ነበረና አመከነባቸው እንጂ! አሳገድነው እያሉ ጥቂት ሳያማስኑበት በአጭሩ አስቀረባቸው፡፡ በገንዘብ ምርኮ ከሚያበዙት ይልቅ እግዚአብሔር በእንባ የሚማርኩትን መረጠ፡፡ ሣር ነጭታ እንደጠገበች ዕዋል ባናፉበት አንደበታቸው ይናገሩት ዘንድ አሳጣቸው፡፡ በእነዚህ ሁለት አካላት ላይ ተፈቀደ የሚለው ዜና እንደ መብረቅ አናት የሚሰነጥቅ፣ እንደ እሳት የሚፋጅ፣ እንደ ንዳድ ብርክ ብርክ የሚያስብል የቁም መቅሰፍት ነው፡፡
በእርግጥ የዐውደ ርእዩ ዓላማ ከተሳካ ቆየ፡፡ ለመድረክ ሳይበቃ ዓላማውን ቀድሞ ያሳካ ዐውደ ርእይ ተብሎ ይመዘገብ ዘንድ ይገባዋል፡፡ ምናልባትም ብቸኛው ባለታሪክ ሊኾን እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ ግን ሁለተኛ ግቡ ሳይዘገይ ቶሎ በመታየቱ እግዚአብሔርን ከልባችን እናመሰግነዋለን፡፡ ሁል ጊዜም ቀድመህ የምትዋጋልን ጌታችን ሆይ ለዘለዓለሙ እናመሰግንሃለን እያልን ሥራችንን እንቀጥላለን፡፡ መፈቀዱ ባይታይም እንኳ ዐቢይ ድምጽ አለው፡፡ ፍጹም የሚኾነው ደግሞ ሲታይ ነውና እርሱ እንዲሳካ እንጸልያለን፡፡
በዲ/ን አባይነህ ካሴ

8 Comments on “ታግዶ የነበረው የማህበረ-ቅዱሳን ዐውደ ርእዩ እንዲታይ ተፈቀደ”

  1.  30, 2016 at 8:05 pm

    እውነቱ ይርደው says:

    March 29, 2016 at 8:18 pm

    እግዚኦ ማለት የለብን ጊዜ ላይ ነን ከመሪ የራሳችን ዜጎች አረመኔ ጋኔን እና ዲያቢሎስ ሆነው ይገሉናል። በሐይማኖትም ያልታደልን ሆን ታጋይ አባ ጳውሎስ ሲሄዱ ታጋይ ማትያስ በመለስ ሰም እየማሉ ይገኛሉ ሐይማኖቱን ከተሐድሶ ሰዎች ጋር አመሰት፣ እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ የለህም እንዳልል የ365 ቀናት ፓውዛህ መብራት ኢትዮጵያ ላይ በቃልህ ስታበራ አይተናል፣ ግን አምላክዬ ትግስትህ በዛ አንድ በል በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ይብቃህ ዝምታ? በሥልጣን ላይ በህይወት ያሉትን አቡነ መርቆርዩስ አልናገርም እሳቸው ለ ቡራኬ እንኳን ዝም ብለዎል፣ አንተ አንደበታቸውን ክፈትልን!!! እሳቸው ዝም በማለታቸው ሐይማኖቱን እናድስው ብለው ኦርጋን ና የግዜውን ፍልስፍና ጨምረው፣አጅበው ከሐይማኖቱ ታሪክ ጋር ያልተለመደ ጉዞ እነ አባ መልከ ፀደቅ፣ አባ ወ/ትንሣኤ ፣ አባ መላኩ፣ ልኡለቃል ሕዝቡን በተሐድሶ መንገድ ኢትዮጵያዊውን ጋራ እያጋቡ ነው። ተው ተብለው ሲመክሩ ያለመታደል ከእኔ በላይ ከፈጣሪ የቀረበ የለም ይሉናል። ብዞዎቹ በጎንደርነት ያከብሯቸዎል ማክበር ጥሩ ነው ሲሰታቱ ከለነገራቹ ግን እነሱን ገደለ ውስጥ ከታችሁ ማለት ነው። አባቶቻችን ያስረከቡንን ዶግማ እና ቀኖና አንዲት ነገር ሳትቀየር፣ ስርአቱን ጠብቀው ህዝብን በአንዲት ቤተክርስቲያን መሰብሰብ አልቻሉም እባካችሁ ስህተት ጎዳና ላይ ናቹ ተመለሱ። እባካችሁ የአገራችን ፈተና ለይ ነች፣ ይቅርታ ህዝቡን ጠይቃችሁ፣ ህዝቡን እንደገና አሰባስቡ፣ የጥላቻ ቤተክርስቲያን በዛ ፍቅር ከሌለ በመሀከላችሁ እግዚያብሔር የለም ማለት ነው ባዶ ባዶ ባዶ ከደመና በታች ስጋን ለማስደስት ይሆንባቸዎል!!! እርስ በእርስ በሁለቱም ጎራ ዲየቢሎስ በረሱ መንገድ እየመራችሁ፣ እያረሰረባችሁ ነው ቆም ብላችሁ ሁለቴ በአሰቸኳይ ዛሬ አስቡ ነገ ፈራጅ ይመጣል። ስሙኝ እኔን ዛሬ የወደቁ ሐጥያተኛውን እኔ እንደ እናንተ አልሆንም ኤኔን ሐጥያተኛውን ስማኝ አምላኬ ብዬ እፀልይላቸዎለሁ። እባካቹ የማህበሩ ቅዱሳን ተግባር አትኮኑኑ ፈራጅ ያያል በአንፃሩ አንዳንዱቹ ከኔ በላይ ክርስትያን የለም ብለው የሚታበዩ አሉ እነሱን ቀጥታ ለይቶ ማስተማር እና ወደ ስርአቱ መመለስ ይበጃል ደካማው ወገኔ ብዙ ደም የተከፈለበት ነው።

    [Reply]

  2. amen haleluya

    temesgen

    ye Memhir Girma tera mech yehon ?

    ke Milyon belay temerewoch yaluwachew memhirGirma

    zare degafeyachew debzaw yet tefa ?

  3. Senu,
    Abune Mathias is modern and he don’t care if millions suffering with bad sprit. It is proved that those people who had bad sprit is opposing Memhere Girma. It is a blessing to apprecate God for he giving us such blessed to save us & to glorify his work.

  4. seytan yenegse bante laie new. merze tenesenesalh lemehonu ant yefugnet tije maneh Abun Meleksadiken yemetinager.kirsetna batemekuh kirsetenan besetuh beabatoch liay afhen atekefet. yeminageruten ayawukemena yekere belachew.

  5. Abajalew,,

    Please learn your mistake and come back under one united Orthodox. Ethiopian people needs always the real Orthodox ceremony. Youbare in civilized world to learn domething else not to blend your founder relgion. We love you come back and please think twice today not tomorrow bring your people under one Orthodox Umberela. No Club music organ in church, No blending our founder law. We love u and critisize u today.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*