የአንዱዓለም አራጌና የሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች ግፍና መከራ

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረ ማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

በቀድሞው ሶቭየት ሕብረት ስርአት ውስጥ የሰብአዊ መበት ተሟጋቾችንና ተቃዋሚ ፕርቲዎችን እያጎረ በስቃይ ይጠብሳቸው የነበረበት የስርአቱ ገሃነም‹‹ጉላግ›› ወህኒ ቤት ነበር፡፡እነዚህ ‹‹ገሃነሞች›› ጉላጎች ተግባራቸው፤ በሶቭየት ሕብረት ያሉትን ተቃዋሚዎች በአጠቃላይ ለማጥፋትና ዳጋም እንዳያቆጠቁጡ ማደረግ ነበር፡፡የሶቭየት የሽብርና የመከራ ቁጥቋጦዎች ሆነው ያደጉና የሃገሪቱና የህዝቦቿ ቀንደኛ ጠላቶች ነበሩ፡፡በተላበሱት የጭካኔና ኢሰብአዊነት ጎሬነታቸው ‹‹የሥጋ መፍጪያዎች›› በሚል ይታወቁ ነበር፡፡