የወጣቶች ዓለም፦ ለሃያ ሠዓታት አልጋ ላይ

የዛሬ አስራ አምስት ቀን ባስተላለፍነው የወጣቶች ዓለም ዝግጅታችን «እርግዝና እና ህመም የነፃነት መንገዶች» በሚል ርዕስ ማልታ በእስር ላይ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አንድ ጥንቅር ማቅረባችን ይታወሳል። ወጣቶቹ ከበርካታ ወራት የእስር ቆይታ በኋላ ነፃ የወጡት በህመም አለያም በእርግዝና ሰበብ እንደነበረ፣ አሁንም ድረስ በከፍተኛ ህመም የሚሰቃዩ በርካታ ወጣቶች በእስር ላይ እንደሚገኙ ገልፀውልን ነበር። እኛም እስር ቤት የሚገኙትን ወጣቶች እንዳገኘን ልናገጋግራቸው ቃል በገባነው መሰረት የተወሰኑትን ወጣቶች አነጋግረናል። ያዳምጡ