የፈጠራ ዉንጀላ ማካሄድና ሠላማዊ ዜጎችን ማፈንና መግደል ይቁም !! ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ የተሰጠ መግለጫ

የፈጠራ ዉንጀላ ማካሄድና ሠላማዊ ዜጎችን ማፈንና መግደል ይቁም
ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ የተሰጠ መግለጫ
=======================================

ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንም ሆነ የኦሮሚያ ከተሞች አዲሱ አወቃቀር በገጠመዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ምክንያት ሳይተገበር እንዲቆይ በኦህዴድ/ኢህአዴግ የተወሰነ ቢሆንም፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተቀጣጠለዉ ሕዝባዊ ንቅናቄ የመጠንና የዓይነት ለዉጥ እያስከተለ ቀጥሏል፡፡ ገዥዉ ፓርቲም የችግሩ መንስኤ የኦሮሚያ ክልል አካሉ ኦህዴድ መሆኑን በሕዝብ ዜና ማሰራጫዎች ቢገልጽም፤ ነገር ግን ለጥፋቱ ይቅርታ እንደመጠየቅ ፋንታ ባለፉት አራት ወራት ዉስጥ ዉስጥ ብቻ ከ270 በላይ የኦሮሞ ዜጎች ተገድለዋል፤ የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎችን ጨምሮ ንፁሐን ዜጎች ታስረዋል፤ ከመኖሪያ ቀዬያቸዉ እንዲሰደዱ ተደርገዋል፡፡ ይባስ ብሎም፣ ጅራፍ እራሱ ገርፎ ለራሱ ይጮሃል እንዲሉ መንግስት ሠላማዊ የመብት ጥያቄ በአቀረቡ ዜጎች ላይ ያላንዳች ርህራሄ የጭካኔ እርምጃ መዉሰዱን እንዲያቆም ደጋግመን በመጠየቃችንና የሕዝብን ሠላማዊ የመብት ጥያቄ ደግፈን በመቆማችን የአህአዴግ መንግስት ባለሥልጣናት ድርጅታችንና አባሎቻችንን መክሰስ ገፍተዉበታል፡፡


ኦፌኮ በሠላማዊ አግባብ ታግሎ ዲሞክራሲያዊ የሕዝብ መንግስትን ለመመስረት የሚታገል ፓርቲ እንጂ በሽብር ፈጠራ ሥልጣን ለመያዝ ዓላማና ዕቅድ የለዉም፡፡ ከዚህ መሠረታዊ ዓላማችን የተነሳም በአጠቃላይ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ፣ በተለይ ደግሞ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት በማግኘታችን ሁሉንም ዜጎች ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ የመንግስት ሥርአትን ዕዉን ለማድረግ የሄድንበት ርቀት የድሉ ጊዜ ሩቅ እንዳልሆነ አመላካች ነዉ፡፡ ዲሞክራሲያዊ የመንግስት አስተዳደር ዕዉን ከሆነ ደግሞ ሙሰኛነት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ የመልካም አስተዳደር ዕጦት እና ከሕገ መንግስታዊ አግባብ ዉጭ ሥልጣን መያዝ ብቻ ሳይሆን ከሕገ መንግስታዊ አግባብ ዉጭ ሥልጣን ላይ መቆየትም የማይታለም ይሆናል፡፡ በፖለቲካ ልዩነት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን መወንጀልም በበኢህአዴግ አገዛዝ ላይ ያበቃል፡፡


የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብታቸዉን ለማስከበር የሚያደርጉትን መነሳሳት ከሕገ መንግስታዊ አግባብ ዉጭ ሥልጣን የያዙም ሆነ ሥልጣን ላይ የቆዩት ኃይሎች ግን፤ ኦፌኮን የመሳሰሉ ሐቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሕዝብን ዓላማ ደግፈዉ ሲሰለፉ የገዥዉ መንግስት አባላት የአሸባሪነት ታፔላ ይለጥፉባቸዋል፡፡ ከፖለቲካ ጨዋታ ዉጭም ለማድረግ የማይሰጡት መግለጫ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ዉስጥም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የሚነሳሱ የሕዝብ ጥያቄዎች ሠላማዊ በመሆናቸዉ መንግስት ሕጋዊና ተገቢ መልስ መስጠት ኃላፊነቱና ግዴታዉ እንደሆነ ኦፌኮ ዛሬም ያምናል፡፡ ሠላማዊ ሰልፍ በወጡና የመብት ጥያቄ በሚያቀርቡ ዜጎች ላይ የሚተኩስ መንግስት ለሕዝብ መብት መከበር ደንታ እንደሌለዉ ከዚህ የበለጠ ተጨማሪ ማስረጃ የማያስፈልግና ፓርቲያችንና አባላቱ የሕዝብን ጥያቄ ደግፈዉ የተሰለፉ እንጂ የአሸባሪነት ታፔላ ሊለጠፍባቸዉ እንደማይገባ ሚሊዮኖች የሚመሰክሩት ጉዳይ ነዉ፡፡ የሕዝብን ሠላማዊ ጥያቄ ደግፌንና ዜጎች መገደላቸዉ፣ መታሰራቸዉ፣ መሰደዳቸዉ፣ መቁሰላቸዉ፣ መደፈራቸዉ፣ መንገላታታቸዉ፣ ወዘተ እንደማይገባ መቃወማችን በምንም ዓይነት መስፈርት አሸባሪ የሚያስብል አይደለም፡፡


አሸባሪነት በፓርቲያችንም ላይ ሆነ በአባሎቻችንን ላይ መለጠፍን አጥብቀን እንቃወማለን፡፡ በሠላማዊ አግባብ ዲሞክራሲያዊ መንግስት እንዲቋቋም የመፈለጋችን ያህል የዜጎች ሕይወት በመንግስት ሠራዊት መቀጠፉን እናወግዛለን፡፡ በተለይ እስካሁን ከሁለት መቶ ሰባ በላይ ለተገደሉ ዜጎች የኢህአዴግ መንግስት ሙሉ ኃላፊነት መዉሰድ አለበት ብለን እናምናለን፡፡


ስለሆነም፤ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ አባላትና ደጋፊዎች ሕዝባዊ ዓላማን አንግቤን የሕዝባችንን ሠላማዊ ጥያቄ እየደገፍን፤ አንደኛ ሠላማዊ የመብት ጥያቄ ባቀረቡ ሕዝቦች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ሕፃናትና አዛዉንቶች ላይ በጦር መሳሪያ የታገዘ እርምጃ መዉሰድን እናወግዛለን፡፡ ሁለተኛ በኢህአዴግ ባለሥልጣናት ክስ ሳንሸማቀቅ ትግላችንን እንደምንቀጥል ቃል እንገባለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለምናራምደዉ የተቀደሰ ዓላማ መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦችና ዓለም አቀፍ ሕብረተሰብ ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ለኦሮሞ ሕዝብ የመብት ትግል መልሱ የጠመንጃ አፌሙዝ መሆን የለበትም!
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
መጋቢት 2 ቀን 2008
ፊንፊኔ

6 Comments on “የፈጠራ ዉንጀላ ማካሄድና ሠላማዊ ዜጎችን ማፈንና መግደል ይቁም !! ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ የተሰጠ መግለጫ”

  1. መቼም አገሪቱ በዚህ ቀውጢ ወቅት በምትገኝበት ሰዓት፣ መሃል ገብቶ የሚያረጋጋ ሰው ተፈላጊ እንደሆነ ግልጽ ይመስለኛል። ስለዚህ እነዚህ ግለሰቦች ደግሞ ላገሩ በሬ ባገሩ ሰርዶ እንደሚባለው፤ ከነርሱ የተሻለና የቀረበ ሰው አለ ብዬ አላምንም። ያቀረቡት ሃሳብም ትክክለኛ ነው ብዬ እገምታለሁ ምክንያቱም ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ፻ ፐርሰንት አሸንፌያለሁ ብሎ ያላሸነፈበትን ምርጫ ባጠቃለለበት ሁናቴ እና (ለይስሙላ እንኳን የተወሰኑ ወንበሮችን ይሰጥ ይሆናል በተገመተበት ግዜ ማለት ነው)፤ አልመረጥናች ሁም ውረዱ ብሎ ድምጹን እያሰማ (በሰላማዊ መንገድ) እያለ የጥይት ናዳ ማዝነብና ይህን ያህል ግፍ ሲወርድ ልክ እያደረግክ አይደለህም ብለው በመናገራቸው የ አባሪነት ስም መለጠፉ አግባብ ያለው አይመስለኝም።
    ይልቅስ ኢህአዴግ አሁን የባጥ የቆጡን ከሚቀባጥር፣ ካቢኔውን አፍርሶ ሌላ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ቢያካሂድ ነገሮች ሰላም ይሆናሉ ብዬ እገምታለሁ። የሕዝቡን እምቢተኝነት በሃይል እደፈጥጠዋለሁ ብሎ አስቦ ከሆነ ግን ወደ እማይወጣበት ችግር ውስጥ አገሪቱን እየከተታት መሆኑን በውል መገንዘብ አለበት። ለሚደርሰው ጥፋትም ዋና ተጠያቂ እንደሆነ ሊረዳው ይገባል።

  2. ትዬጵያ እነሆ በወታደራዊ አገዛዝ ሥር ከገባች 17+25 አመታትን አሥቆጠረች እንዲያውም ዜጎች ሀገራዊ ሥሜት ባልተላበሰው ወታደራዊ የዘራፊ ቡድን ወያኔ ሥብሥብ ቁጥሩ ከፍተኛ ይፕሆነ ህዝብ በግድያና በእሥር በሥደት ላይ ያለን ህዝቦች አድርጎናል የሀገሪቱን ሀብት በመዝረፍ ለታላቋ ትግራይ ለሚሏት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬን በውጭ ባንኮች አከማችተዋል ህዝቡን ልማታዊ ነን እያሉ ትውልዱ ከፍሎ የማይጨርሰው ብድር ለቻይና በጃዙር ተሽጠናል እንዲሁም ይህ የአፋኝ ሥርአት ለአለም ሚዲያ ሀገሪቱን እዳ ውሥጥ ከቶ በምግብ ራሣችንን ችለናል ኢኮኖሚው በሁለት አሀዝ ጨምሯል ….ወዘተ እያለ ዛሬ ህዝባችንን በአግባቡ ያልመገበን መሬት ሄክታሩን በአንድ ዶላር ገበሬውን በማፈናቀል ለ100 አመት እንዲያርሱ ለሳውዲ ለህንድ ለቱርክ…እየሸጠን ይገኛል ሌላው የማጨናበሪያ ሥልቱ የተፈጥሮ ሀብት በሌለበት ሀገሪቱ ወደ በረሀነት የለወጧትን ዘራፊ ድርጅት ወያኔ ጥብቅ ደኖችን በሙሥና በማሥጨፍጨፍ ይህን ለማየት ሩቅ ጫካ መግባትም አያሥፈልግም በየኬላው የሚያልፋትን የአይሱዙና የኤፌሥ አርን ተሽከርካሪዎች ባላቸው ጥብቅ ቁርኝት መሀል አገር ላሉ ፋብሪኮች ሲያሥረክቡ ማየት ያልተሰወረ ድርጊትም ነው ዛሬ ሀገሪቱ ወደ በረሀነት ተለውጣለች ጆሮ ያለው ይሥማ ሁለተኛው ሥልቱ የሰላም አሥከባሪነት ሸፋን ከፍተኛ የዶላር ጥማቱን የሚያሥገኝለትን የወታደሩን ደም በመሸጥ ለሀጉሩ አሥተዋፅኦ ላይ ነን ይላሉ ቀጥሎም የአፍሪካ ህብረት ጦር እኛ እንበቃለን በማለት የተመደበውን የሎጂሥቲክ ካፒታል በንፁ የህዝብ ደም ለውጠውታል ዛሬ ትልቁ የኢትዬጵያ ጦር ካምፕ ሶማሌ ይገኛል ይህንንም በተጨማሪ የአሜሪካ መንግሥት ፋይናንሥ ያረገዋል ይህ ሲሆን የህ ገልቱ ወታደር የቆመለትን አላማ ባለማወቅ በዶላር ይከፈልሀል በሚል ተታሎ የአሞራ እራት ሆኗል በነዚህ በመሳሰሉት የማጭበርበሪያ ሥልቶች በመጠቀም ሥልጣኑን በጠበንጃ ሀይል በመታገዝ ዛሬ በፊንፊኔ ባሉት ክፍለ ከተማ ወረዳና ቀበሌዎች ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሻለቃ ህዝቡ ተወሮ ይገኛ ከተማው ክፕምርጫ 97 በሃላ የምድር ጦር ካምፕ መሥላለች ህዝባችን በከፍተኛ የሥነልቦና ጫና ውሥጥ ይገኛል ይህ የወታደር አገዛዝ ቡድን ለደፈሩት የኦሮሞና ከፊል የአማራ ታጋዬች የከፈሉት መሥዋትነት ሊመሰገኑ ይገባል ወታደራዊ መግሥቱም ያለምንም ማወላወል ህዝባዊ መንግሥት እንዲመሰረት የከፋ እልቂት ሳያሥከትል ከወዲሁ ሊዘጋጅ ሊወያይ ይገባል።

    ሞት ለወያኔ

    ቶኪቹማ ቢሊሱማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*