መስመራችን ያስመዘገባቸውን አንፀባራቂ ድሎች ያቆሸሹ በሚል ኦሕዴድ በተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው የሚታወቁ አመራሮቹን ማባረሩን ቀጥሏል
መስመራችን ያስመዘገባቸውን አንፀባራቂ ድሎች ያቆሸሹ በሚል ኦሕዴድ በተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው የሚታወቁ አመራሮቹን ማባረሩን ቀጥሏል::የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) በኦሮሚያ በርካታ አካባቢዎች የተፈጠረውን ችግር ለማጥራት ሰሞኑን ባካሄደው የማዕከላዊ ኮሚቴ ጉባዔ፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩትን የክልሉን የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘለዓለም ጀማነህን እስከ ቀጣዩ የድርጅቱ ጉባዔ ድረስ ከማዕከላዊ ኮሚቴው አገደ፡፡
ሪፖርተር በየካቲት 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ዕትሙ ከኦሕዴድ አመራርነትና ከክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊነት በብቃት ማነስ ሳቢያ፣ የኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌና የክልሉ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኩቹ መነሳታቸውን መዘገቡ ይታወሳል፡፡ማዕከላዊ ኮሚቴው ለአምስት ቀናት ያካሄደውን አስቸኳይ ጉባዔ የካቲት 27 ቀን 2008 ዓ.ም. ባጠናቀቀበት ወቅት ባወጣው መግለጫ ደግሞ፣ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ዘለዓለም ጀማነህ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው እስከ ቀጣዩ የድርጅቱ ጉባዔ ማገዱን አስታውቋል፡፡
ፓርቲው ውሳኔውን ያሳለፈው ‹‹ከሁሉም በፊት መስመራችን ያስመዘገባቸውን አንፀባራቂ ድሎች ያቆሸሹ የግለኝነትና ጥገኝነት፣ እንዲሁም የጎራ መደበላለቅን በጥልቀት በመመርመር ከሥራ አስፈጻሚና ከማዕከላዊ ኮሚቴ ጀምሮ በከፍተኛ አመራሮች ላይ ያለምንም ርህራሔ ዕርምጃ ተወስዷል፤›› በማለት ነው፡፡አቶ ዘለዓለም ጀማነህ በኦሕዴድ ውስጥ በተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው የሚታወቁ ሲሆን፣ ለረጅም ዓመታትም የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ሠርተዋል፡፡በፓርቲው የአምስት ቀናት ውይይት ወቅት ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል፣ በፌዴራል ፓርላማ ውስጥ የኦሕዴድ መሠረታዊ ድርጅት አባላት ለማዕከላዊ ኮሚቴው ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ይገኙበታል፡፡
ከእነዚህም መካከል የሰው ሕይወትና ንብረት ከመጥፋቱ በፊት ኦሕዴድ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት ለምን ተቸገረ? የአዲስ አበባና የኦሮሚያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን የቆመው በ2006 ዓ.ም. ነው በማለት መረጃ ሲሰጥ ከቆየ በኋላ፣ በድጋሚ በ2008 ዓ.ም. የተቀናጀ ማስተር ፕላኑ ውድቅ ተደርጓል ብሎ ለምን የተጋጨ መግለጫ ሰጠ? በ2006 ዓ.ም. ቆሞ ከነበረስ በወቅቱ ለሕዝብ ለምን ይፋ አልተደረገም ነበር? የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ያላት ልዩ ጥቅም የማግኘት መብት በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፋ ይሆናል መባሉ ተገቢ ነው ወይ? መቼ ተጠንቶ እንዴት በአጭር ጊዜ ይፋ ሊሆን ይችላል? ማግኘት የሚገባበት ጥቅም ወደኋላ ተመልሶ የ21 ዓመታት ጥቅምን ያስገኛል የሚሉ ጥያቄዎች ተመልሰዋል ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችም በውይይቱ ተነስተዋል፡፡
በዚህ ውይይት ላይ የተሳተፉት የማዕከላዊ ኮሚቴው አባልና የፓርላማው አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ‹‹ዋናው ችግር ያለው የፓርቲው አመራር ላይ ነው፡፡ ራሳችንን እንፈትሽ፤›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
‹‹የተፈጠረው ችግር የራሳችን የሙስና ችግር ነው፡፡ ችግሮችን በፍጥነት መፍታት ካልቻልን አንዱ በአንዱ ላይ እየተደራረበ አገር ይፈርሳል፤›› ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ‹‹ትልቁ ውድቀት የሕዝብ ጥያቄን መመለስ ሳንችል ስንቀር ነው፡፡ ስለዚህም ራሳችንን እንፈትሽ፤›› ያሉት አፈ ጉባዔው፣ ‹‹ይኼን ጊዜ እዚሁ ቁጭ ብለው መረጃ የሚልኩ ይኖራሉ፡፡ የድርጅታችን ችግር እኛ ውስጥ ነው ያለው፤›› ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ የአቶ አባዱላ አባባል ጉባዔውን ያሳቀ ሲሆን፣ እንዳሉትም የጉባዔው የድምፅ መረጃ አፈትልኮ ወጥቷል፡፡
ኦሕዴድ ጉባዔውን አጠናቆ በደረሰበት መደምደሚያ ላይ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ደስተኛ አለመሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም ጉባዔው እንዳለቀ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በአዳማ ከተማ ከኦሕዴድ ከፍተኛ አመራሮች ጋር እየመከሩ መሆኑ ታውቋል፡፡
አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከኦሮሚያ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊነት የተነሱት አቶ ሰለሞን ኩቹ፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት አማካሪ ሆነው መሾማቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
Source Reporter amharic

የነፃነት ትግሉን መልካም አሥተዳደር አንፀባራቂ ግድያ ተለውጦ ይገኛል ይህን የሰብአዊ መብት ረገጣን ምን ልንለው እንችላለን ድል? ዋ!
ወያኔንና አህዬቹን ለማሥለቀቅ የሚደረገው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል ለባንዳ አንገዛም።
ወያኔ ሀቱ ሀጠራው!
ማነህ ባለ ተራ ሲባል አልሰማች ሁም፣ ኢህ አዴግ በየ አስር ዓመቱ ሰውን ካላባረረ በጤና የሚሄድ ያለ መስሎ አይታዬዉም። በመሆኑም በረሃ ውስጥ የነበረበትን ጊዜ አውጥተን፣ መንግስት መስርተናል ካሉበት ጊዜ ያለውን እንኳን ብናሰላው በየ አስር ዓመቱ የተሰናበተውን ( በግምገማ ስም የተባረረውን) ማወቅ እንችላለን።
ስለዚህ አቶ ታምራት ላይኔ ራሳቸው ከመባረራቸው በፊት ጓዶቻቸውን እንዲያሰናብቱ ካደረጉበት አንስቶ፣ ራሳቸውን እስከጣሉበት ድረስ፤ ከዚያም ኢትዮጵያዊ ሽታ የነበራቸውን የሕውሃት አመራሮችን መለስ ዜናዊ ከመቀደማቸው በፊት ያስወገዱበት (የሕወሓት መሰንጠቅ)፣ እግረ መንገዱንም ከነርሱ ጋር አብረው የውጡትን የኦህዴድና የደቡብ ህዝቦች አመራሮችን እንደ አባተ ኪሾ የመሰሉትን፤
ያኔ እንግዲህ ብአዴን ለመለስ ዜናዊ ቡድን ህልውና መቆም ቁልፍ ሚና በመጫወቱና የሕወሓት በዚያ መልኩ መሰንጠቅም ለህልዉናችን አመቺ ነው ብለው ብአዴኖች ስላመኑበት ይመስለኛል ውሽንፍሩ እነርሱን ሳይነካቸው እንዳለፈ ይታወቃል። መቼም ብ አዴን ላደረገው ውለታ ብዙ ደረጃዎችን ቢያስገኝለትም ህዝባዊነቱን ግን እንደሸረሸረው ራሱም ቢሆን ቆይቶም ቢሆን የተገነዘበው ይመስለኛል።
ከዚህኛው በኋላ በከፍተኛው አመራር ላይ ባያተኩርም በዝቅተኛው ዕርከን የሚገኙትን ጨረፍ አድርገው እንዳለፉ የምንስተው አይደለም። ቀጣዩ አስር ዓመት ዋናው ሰው ራሳቸው በግምገማ ይሁን በ አስገዳጅ ጥሪ ስለተወገዱ የኢህ አዴግ ግምግማ ግራ ተጋብቶበት ራሱን በማሰማመር ላይ ከርሞ፣ የልማዱን ለመፈጸም እንሆ ወደ ኦህዴድ አቅጣጫውን አዙሯል ቀጣዩ ደግሞ ብአዴን ለመሆኑ የኣታሞው ድለቃ እየነገረን ነው። ታዲያ አሁን የርሱ ተራ ሲሆን አደራ እርሱ ከድቶን ነበር ብላችሁ እሰየው እንኳን የጃች ሁን ሰጣችሁ እንዳትሏቸው።
እንግዲህ እንደዚህ እያደረጉ እየቆራረጡ ከሚጥሏችሁ፣ ተደራጅታችሁ እነርሱን ብትጥሉ አይሻልምን?
ቸር ይግጠመን
Weyane lebaw, thug and thief creating problem in communities during a day light when it was supposed to be busy handling public administration. Does weyane have elderly cohort who could say ‘immature babies what you are doing is not right’.
Ke’ij ayshal doma!