የወልቃይት ፖለቲካና ተቃዉሞ በዳባት አካባቢ – ግርማ ካሳ
የወልቃይት ፖለቲካና ተቃዉሞ በዳባት አካባቢ – ግርማ ካሳ
የኢሕአዴግ መንግስት ላይ እየቀረበ ያለው ተቃዉሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። በስሜን ጎንደር ዳባት ከተማና አካባቢ ተቃዉሞ እንደተነሳም እየሰማን ነው። ተቃዉሞው ወደ ወረዳዉና የቀበሌ መንደሮች እየተዛመተ እንደሆነ ነው ዘገባዎች የሚጠቁሙት። ዳባት ከጎንደር ከተማ በስተ ሰሜን፣ ወደ ትግራይ በሚወስደው መንገድ ላይ ያለች ከተማ ናት። በደባርቅና በአምባ ጊዮርጊስ መካከል። መረጃዎች እንደሚገልጹት ከጎንደር ወደ መቀሌ የሚወስደው መንገድ በዳባትና በደባር መካከል ተዘግቶም ነበር። በዳባት ያሉ ባለስልጣናት መካከልም ከፍተኛ መከፋፈል እንደተፈጠረ ነው። የአካባቢው ብዙ ታጣቂዎች የሕዝቡን እንቅስቃሴ በሃይል ለመጨፍለቅ ፍቃደኝነት አናሳይም እያሉም ነው። በዳባት የተጀመረው ሰላማዊ የእምቢተኝነት ተቃዉሞ በቀላሉ ወደሌሎች የጎንደር አካባቢዎች ሊዛመትም እንደሚችል የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም።
በኦሮሚያ የነበረው ተቃዉሞ፣ በአዲስ አበባ የተጀመረው የታክሲዎች የሥራ ማቆም አድማ ላይ በዳባትና ደባርቅ የተጨመረው ተቃዉሞ ሲታከልበት በርግጥም የሕወሃት አገዛዝ በሁሉም አቅጣጫዎች እየተወጠረ እንደሆነ አመላካች ነው።
የዳባት ሕዝብ ጥያቄዎች በዋናነት በመሰረታዊ የመብት ጥያቄ ላይ ያነጣጠሩ ሲሆን ወልቃይት ጠገዴና ጸለምት ቀድሞ ወደነበሩበት ክልል ወይም ክፍለ ሃገር፣ በጌምድር፣ እንዲመለሱ የሚጠይቅ ነው።
የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች የወልቃት ጠገዴ ሕዝብ “ትግሬ ነው” ብለው ይከራከራሉ። ሰልፍ ቢጤም አይተናል። ሆኖም ራስ መንገሻ ስዩም፣ የቀድሞ የሕወሃት መስራች አቶ አረጋዊ በርሄ ጨምሮ የአካባቢዉን ታሪክ የሚያውቁ ብዙዎች ከተከዜ በስተምእራብ ያለው የወልቃይት ጠገዴ ግዛት፣ ሕወሃት በኃይል ወደ ትግራይ እስከጠቀለለበት ጊዜ ድረስ፣ በትግራይ ሥር ሆኖ እንደማያወቅ ነው የሚናገሩት። የወልቃይት ጠገዴ መሬት ለትግራይ ቅርብ ስለሆነ ለአስተዳደር እንዲያመች ነው ወደ ትግራይ የተቀላቀለው የሚል መከራከሪያ ቢያቀርቡ አንድ ነገር ነው: ግን ወልቃይት ድሮም የትግራይ ነበር ብሎ መከራከር ግን የሚያስተዛዝብ ከመሆኑንን በተጨማሪ የትም አያደርስም።
የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የሚወክላቸውን የወልቃይት ኮሚቴ አባላት በማሰማራት፣ ጥያቄዎችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት፣ ጉዳዩ በፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲታይ ማመልከቻ ያስገባ ሲሆን፣ የአቶ አባይ ወልዱ የሕወህት አመራር ግን ሕግን አክብረው በሰላም እየተንቀሳቀሱ ያሉ የኮሚቴ አባላትን እያሰሩና እያዋከቡ ነው የሚገኙት። አልፎም በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ ንቀት ያዘለ ማስጠንቀቂያና ዛቻም ሲሰነዝሩ ይሰማሉ።
በወልቃት ጠገዴ ግዛት ብዙ ትግሬዎች ይኖራሉ። ትግሬዎች በወልቃይት ጠገዴ ብቻ ሳይሆን በተቀረዉ ጎንደር ሆነ በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች ለዘመናት በፍቅር፣ በሰላም የኖሩ ናቸው። በወልቃይት ጠገዴ የሚኖረው ህዝብ ሲፈልግ ጎንደር ከተማ፣ ሲፈለግ ሽሬ እየሄደ የሚነግድ ነው። ሕዝቡ አማርኛም ይናገራል፤ ትግሪኛም ይናገራል። የቋንቋ ችግር የለበትም። ቋንቋ የልዩነትና የጸብ ምክንያት ሆኖ አያውቅም። እዉነት እንነጋገር ከተባለ ጎንደሬዉና ትግሬው በጣም የተዋለደ ነው። የተዛመደ ነው።
ሆኖም ሕወሃት፣ ያልነበረ መርዛማ ዘረኝነትን ረጭቶ ለዘመናት የኖረን ሕዝብ ማቃቃር ጀመረ። “እኔ አማራ ነኝ፤ እኔ ትግሬ ነኝ” ሳይባባል በኢትዮጵያዊነቱና፣ በስብዓናው ተከባብሮ ሕዝቡ እንዳልኖረ፣ አሁን “ወልቃይቶች ትግሬ ናቸው፣ ወልቃይቶች አማራ ናቸው” እየተባለ እስከ መወዛገብ ደረጃ ተደርሷል።
የ”ማንነት፡ ፖለቲካ ብዙ አይመቸኝም። ወልቃይቶች “አማራ” ነን ሲሉ አይመቸኝም። ወልቃይቶች እኔ የማያቸው እንደ ጎንደሬ እንጂ “አማራ” አይደለም። “አማራ” የሚባል ማንነት ነበረ ብዬ አላምንም። የተወሰኑ ወገኖች “አማራ” በሚል ጆንያ ዉስጥ በሕወሃት ስለታጨቁ “አማራ” መባል ተጀመረ። ያልነበረ የ”አማራ” ማንነት ማደግ ጀመረ። የአማራ ብሄረተኝነት !!!! ወልቃይት ጠገዴዎችም “ትግሬ ናችሁ” ሲባሉ ያንን ተቃወሙ። “አማራ” ነን አሉ፡ ፖለቲካው የዘር ነዉና እነርሱም የዘር ካርድ መጫወት ጀመሩ። ወያኔዎች እ እርሱ ዘረኛ ሆነው፣ ዘረኛ ፖሊሲ በማራመዳቸው ሌላውን ሳይወድ በግዱ ወደ ዘረኝነት እንዲሄድ ገፋፉት።
“አማራ” ተኮነ፣ “ትግሬ” ተኮነ ምን የሚፈይደው ነገር አለ። “አማራ ነህ”፣ “ትግሬ ነህ” የሚለው ፖለቲክ መርዛማ ቁማርን ጨዋታ እንደ ሕዝብ ወደ ኋላ ቀርንት ከመጎተትና እርስ በርስ እንድንጠራጠር፣ እንድንፈራራ፣ እንድንጠላላ ከማድረግ ዉጭ ምን የሚቀይረው ነገር አለ ? ምንን ችግር ነበረው ትግሬ ፣ አማራ ከምንባባል በቃ ወልቃይቴ ነን በሚል በወልቃይት ነዋሪነታችን፣ ዘር ሳንመለከት እንደ ቀድሞ በፍቅር ብንኖር ?
እንግዲህ ኢትዮጵያዉያን ትግሬ እንሆን ጎንደሬ መንቃት አለብን። ወልቃይት ጠገዴ ትግራይ ዉስጥ ሆነች፣ ጎንደር ዉስጥ ተጠቃለለች ቁም ነገሩ ያ አይደለም። ቁም ነገር ሕዝቡ መብቱ ተከብሮ ይኖራል ወይ የሚለው ነው። ጥያቄው የዘር ወይንም የማንነት አይደለም፤ ጥያቄው የመብት ጥያቄ ነው።
ወልቃይት “የማንነት” ጥያቄ ያነሱት ሰብአዊ መብታቸው ስለተነፈገ ነው። የትግራይ አስተዳደር መልካም፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያው አስተዳደር ቢሆን ኖሮ፣ በኃይል ትግሪኛን በመጫን የትግሪኛ ብቻ ፖሊሲ ባይኖር ኖሮ፣ አማርኛም ከትግሪኛ ጋር የክልሉ የሥራ ቋንቋ ቢሆን ኖሮ፣ አማርኛ ልጆቻችሁን ማስተማር አትችሉም ባይባሉ ኖሮ፣ ስልጣን ከመቀሌ ወደ ዞኖች ቢወርድ ኖሮ፣ የልማት እንቅስቃሴዎች በተወሰኑ ቦታዎች ብቻ ሳይሆን በሁሉም ቦታዎች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ቢከናወኑ ኖሮ፣ ወልቃይት ጠገዴዎች ወደ ጎንደር እንቀላቀል አይሉም ነበር።
እንግዲህ ያለው ትልቁ ችግር አሁን አገዛዙ ላይ ነው። የአገዝዙ ዘረኛ ፖለቲካ ላይ ነው። በዜጎች መካከል ያለውን ታሪካዊ አንድነትና ትስስር ከማጉላት ይልቅ ዜጎችን ለመከፋፈልና ለመለያየት የሚደረገው የኋላ ቀር ፖለቲክ ነው ትልቁ ችግራችን።
ሕወሃቶች በጣም ግትሮች ናቸው። እነ አባይ ወልዱ አሁንም ያኔ ጫካ ዉስጥ የነበሩ ጊዜ እንደሚያስቡት ነው እያሰቡ ያሉት። እነርሱ መቀሌ ሆነ እየፈጸሙ ባሉትም ዘረኛ ተግባራት ሰላማዊ የትግራይ ህዝብ በሌላው እንዲጠላ ለማድረግ እየሞከሩ ነው። እነርሱ ዘረኛ ሆነው ሌላው ዘረኛ እንዲሆን፣ ሌላው እልህ ውስጥ እንዲገባ፣ እንደ እነርሱ ጠባብ እንዲሆን ነው ለማድረግ እየሞከሩ ያሉት። ነገር ግን እኛ በጎንደር ያለንም ሆነ በትግራይ ወደ ቀድሞ ታሪካችን መመለስ ነው ያለብን። ወደ ፍቅርና መቀባበል ነው መመለስ ያለብን።
አንርሳ. ጎንደሬው እና ትግሬው ለዘመናት አብሮ ተፋቅሮ የኖረ ነው። የተዋለደ ነው። ጥቂት ዘረኛ ሰይጣኖች ሕዝቡን እንዲያምሱት እና እንዲያቃቅሩት ሊፈቀድላቸው አይገባም። ህወሃት፣ ይሀ መሬት የትሬ፣ ያ መሬት የኦሮሞ፣ እዚያ ማዳ ያለው የጉራጌ ይሉናል።ጨለምተኛና የኋላ ቀር አመለካከት። ወልቃይት ጠገዴ የጎንደሬው አገር ነው። ወልቃይት ጠገዴ የትግሬም አገር ነው። ወልቃይት ጠገዴ የኦሮሞዉም አገር ነው። ወልቃይት ጠገዴ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን አገር ነው። ሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው።አራት ነጥብ።


Welqait-Tegedie, Telemt yesmien gonder kfle hager akal nachew.
Woyanie baschekuay stetun serzo, beselam welqait-Tegedien ena Telemtn lesmien gonder masrekeb alebet.
Be ebrit ena tbit be hgewoT yelielawn habt nbret meriet mewrer be 21ñaw kfle zemem ayseram, Tornet yasketlal, kekisaraw behualam worariwn kebad yewonjeleña qTat yameTabetal.
Mamn hzb merietun leworari balenbet zemen ayseTm.
Worariw tgrai woyanie medemses alebet.
Le 41 amet tewerenal, ahun demo worariwn tgrai woyanien tewagten medemses alebn.
The so called Girma Kassa are you trying to preach us Welkait Tsgede tslemte is ok if it stay with tigray region? What a nonsense propaganda is this? So, please keep away your poisoned message from our peoples Begemder:
All your articles have a bad smell, that does not give sence.
Girma Kassa please be honest for you consience if you are not working for woyane
First of all TPLF, they don’t have any mind. They are pieces of devil. They don’t believe in God. So why we are expecting good things from devil. The only means to win woyana , we Ethiopians who believe in God we have to stand together without any discrimination among us. If we are united together, we can win TPLF.
ከቡልቻ የተሰጠ የተመቸኝ አስተያዬት
———————
ከድሮ ቀረርቶዎች አንዱን ልንገራችሁ።
አገራችን ጎንደር ወንዛችን ተከዜ
ማን ይነካናል እምቢ ባልን ጊዜ
ይባል ነበር።
ለማንኛውም የወልቃይቴ የትግራይን ክልል አልቀበልም ማለት የወያኔን የቋንቋ ክልል ምሰሶ ከስር መሰረቱ የሚያናጋው ነው። ወልቃይት ትግርኛ ተናጋሪ ቢሆንም የቋንቋን ክልል አልቀበልም ልማታዊና ስነ ልቦናዊ ክልል ነው የሚያስፈልገኝ ማለቱ ለሌሎቹ ያለአግባብ በቋንቋ መስፈርት ብቻ የተከለሉ አካባቢዎች ጥያቄያቸውን እንደሚያነሱ ያደፋፍራቸዋል። ለምሳሌ የደብረ ብርሃን ወይም የደሴ ሰዎች ወደ ጎጃም ክፍለ ሀገር ባህርዳር መዳበላቸው ቋንቋን እንጅ መሰረታዊ የእድገትና ስነልቦና መስፈርትን ያዛመደ አይደለም። በተመሳሳይ ሁኔታ የሀረርጌ ቆቱ ከሸዋ ወይም ከወለጋ ጋር ምንም የሚያስተሳስረው ነገር የለም (ከቋንቋ በስተቀር)። ስለዚህ ይህንን የመሰለ ውስብስ ችግር ለመፍታት ቀላሉ መንገድ ሀገራችን በ 96ቱ አውራጃ ደረጃ ብትከለልና እነኝህ አውራጃዎች የፈለጉትን ቋንቋ መርጠው ቢጠቀሙ የቋንቋን ችግር መቶ በመቶ ከመፍታቱም በላይ የልማትና ስነ ልቦና ጥያቄዎችንም በተሻለ መንገድ የሚፈታ ሲሆን ጠባብ ብሄርተኝነትንም ለአንዴና መጨረሻ ጊዜ ያስወግዳል። የመንግስት ስልጣንም በሚገባ ወደታች ወርዶ የሚያገለግለውን ህብረተሰብ ሊያረካ ይችላል። እኔም የነቀምቴ ልጅ ስለሆንኩ በአዳማ ስር መገዛቴን እቃወመዋለሁ። ወለጋን የሚያክል ትልቅ ክፍለሀገር ለምን ለአዳማ ገባሪ እንደሆንን ሊገባኝ አይችልም። አዳማ የነቀምትን ያህል ደረጃ እንኳን ያልነበራት የአውራጃ ከተማ ነው የነበረችው። ከወልቃይት ቀጥሎ እኛም ማመጻችን አይቀሬ ነው።
ግርማ ካሳ: -ወልቃይቶች “አማራ” ነን ሲሉ አይመቸኝም። It is not because Mr. Germa wanted it or not, but because the situation created by the fascist TPLF forced them to be Amharas. And that is what they are. And it is their right to be what they are. They are Amharas and the millions of Amharas stand behind the Wolkait Amharas. This is only the beginning of the iceberg. It is a long way until all Amharas regain their territories and pride that was abused by these Banda Tigres. Mr. Germa what I would like to tell you is that it is not the WOLKAIT AMHARAS who brought all this mess to this country, but it is the BANDA TIGRES. Unless we get rid of these banda Tigres from our country we will continue to suffer for a long time.
Please destroy the word “ክልል” it is as ugly as woyane. ክልል is a poisonous gift from that demonic sick man called”መለስ” just to make us ሆድና ጀርባ። Can we burry this word with him ? ? ? Please ! ! ! ! በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ከብቶች እያገድኩ ሳድግ፥”ክልል” የሚባለው ከብቶች በተወሰነች ታጥራ በተቀመጠች ትንሽ የትልቁ እርሻ ክፍል የሆነች በሮች እስከሚጠመዱ ድረስ ሳር የሚግጡበት የታጠረ የእርሻው ክፍል ነው።እኛ ከብቶች አይደለነም። ክፍለ ከተማ እንደምንለው ሁሉ ለምን ክፍለ ሃገር አንልም።
Dear Girma you said there is no Amhara?
አቶ ግርማ ክሳ በመርዝ የተቀላቀለ ጨጨብሳ ሲያቀርብልን እንደነበረ እኔ ገና ድሮ ነበር ያወቅሁት ግን የመጀምሪያ ተናጋሪ ሰው ለመሆን ድፍረቱን ፈርቸ ነው እንጅ።ጽሁፎቹን ሁሉ ብታጣጥሙት ጥረቱ ሁሉ ወያኔን ከጠጠያቂነት እጅግ በረቀቀ መንገድ ለማዳን ነው። Thank you my Ethiopian heros for detecting this virus ! ! !
Girma ante Ahiya
Ante beagerachin
LE shekim yemitfelgew qurema.
wolkait is state of Gonder, so TPLF like it or not wolkait will stay with a Gonder. other ways TPLF will pay the price.
የዳግም አደዎ ዘመቻ ቁጥር 3 መመሪያ
ለህዝቡ የሚሰራጭ።
በ25 አመት ውስጥ በየአመቱ ከ $3 ቢሊዬን በላይ እርዳታ እና ብድር ከውጭ ሲፈልቅ ቆይቷል ለኢሕአዴግ ። የአንዱ አመት ብቻ ኢትዮጵያን ለማልማት የበቃል፣ ግን ሌላው ቀሪው የ24 አመቱ የገንዘብ ጎርፍ የ1000 የአደዎ ኢሕአዴግችን ኪስ አለማ በልማት መልክ። ይህን የኢትዮጵያን ህዝብ ማታለል አይቻልም።እነዚህን ናቸው የታሪክ ነቀርሳዎች በትግራይ ህዝብ ስም በኤፍርት ስም የነገዱትን ከእነ ሂሳቡ $50 ቢሊዬን ጋር እን ፈለጋቸወለን??? ይህንን ጥሪ እናረጋለን ከኢሕአዴጎቹ አስከ ይካቲት 30, 2008 ድረስ ለጠንከራ አገር ወዳድ ተቀዎሚዎች መርጠው በሰላማዊ መንገድ ሥልጣናቸውን ማስረከብ አለባቸው። ይህ ካልሆነ ይድረስ እርምጃ ለመውስድ ይድረስ ባሉበት ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊያን።
መመሪያ ቁጥር 1: እናት አና አባቶች በኢሕአዴግ ስራዊት ውስጥ የተሰለፉትን አስቸኳይ ጥሪ አርጉ በሚገባቸው ቋንቋ እና ድህረ ገፅ ላይ ከዛሬ ጅምሮ ማንኛውም ኢትዮጵያዊም የሁን ወንድም ሆነ ኤርትራዊያን በሰራዊት ውስጥ ለመቀጠል እንድ ጥይት እንዳትተኩስ! እምቢ ብሎ የተኮስ ካለ አጠገቡ ያለህው ስራዊት ቀድመህ እንድትመታው ታዘሀል። ማንኛውንም ለኢህአዴግ ጦር ውስጥ አለቅላቂ ካለ በአገኘህው አጋጣሚ እርምጃ እንድትወሰድ ተዘሀል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ የሚያከብርህን የኢሕአዴግ ጦር ወይም ፓሊስ አክብር፣ በአንጻሩ ለገድልህ ከአሁን በኋላ የሚመጣብህ ካለ ባላህ መሣሪያ ቅደመው። በማንኛውም ቆረጣ ወገያ ላይ በለህበት ቦታ ተሳተፉ።
2ኛ የአዲስ አበባ ነዎሪዎች በሙሉ፣ የኢሕአዴግ ካድሬዎች ቤታቸውን ቶሎ ለመሽጥ የስውር ዘመቻ ላይ ስለሆኑ እንዳይገዙ። በቅርብ ቀን የመሬት ከርታ ስብስበው ደግም ህዝቡን በአዲስ አበባ ላይ ላማስለቀስ ዘመቻ ጀምረዎል። በጉልበት ቦታህን ሊነጥቅህ የመጣ ሁሉ ላይ እርምጃ እንድትወስድ ታዘሀል። የመሬት ይዞታ በቋሚ መንግስት አዋጅ ይወጣል። የኢሕአዴግን ሕግ ሁሉ ይሸራል።
3ኛ በቆረጣ ወግያ ጥሪ ላይ ማንኛውም አገር ወዳድ መሳተፈ አለበት።
ነፃነት ወይም ባርነት፣ ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር!!!
ተራማጅ የኦሮሞ ማህበር ከ አምቦ ጫካ ጽ/ት እና ይድረስ ለመሪዎቻን ከአስመራ ደ/ር ብርሐኑ ነጋ አና የ ጦር አስተባባሪ አዛዥ ጄነራል ከማል ገልቹ።
Some of you are working for TPLF because you just simply make a hate speech. You don’t have tangible evidence to argue but insulting. I’m so sorry to say it.
Ato Girma has said what he has felt is good for us. If you don’t agree on his idea, bring what is yours and challenge him. Otherwise, it’s nothing other than showing your stupidity.
Let’s feel free and say something genuinely and which is good for our country.
Dedebit you are so desperate what’s going on I am not talking about Adawa.
Yenesber ager yene demelash.
woyanien ygela kagru sayshesh.
Bebrit tewoTro yetgrie woyanie.
Meriet worere kanbesaw gonderie
tbit yewoTerew woyanie aleqelet. Madaberia yhon legonderie meriet ayT motn st-sha.
Zela tashetalech yedmet tksha. glemenun
Yenesber ager yene demelash.
woyanien ygela kagru sayshesh.
Bebrit tewoTro yetgrie woyanie.
Meriet worere kanbesaw gonderie
tbit yewoTerew woyanie aleqelet. Madaberia yhon legonderie meriet ayT motn st-sha.
Zela tashetalech yedmet tksha. Asarun ybla yayetgrie qoshasha. Glebew Tbesew ahunun.
Wleta aTfto beltualna ermun. Kahadi aymarm yenaqe newrun.