በኦሮሚያ ክልል ሕዝባዊ የተቃውሞ ድምጽ ሌሎችንም ብሄሮች እንዳካተተ ተቀጣጥሎ ቀጥሏል::

በኦሮሚያ ክልል ሕዝባዊ የተቃውሞ ድምጽ ሌሎችንም ብሄሮች እንዳካተተ ተቀጣጥሎ ቀጥሏል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል የተቀጣጠለው ሕዝባዊ የተቃውሞ ድምጽ በዛሬው እለት በወለጋ በሃረርጌ በሸዋ በኢሊባቦር እና በተለያዩ አከባቢዎች ሕዝቡ ከባድ ተቃውሞ ሲያሰማ ውሏል::በማለዳው በቦረና ያቤሎ ከተማ የጀመረው ተቃውሞ ሕዝቡ በነቀስ ወጥቶ ተቃውሞውን ያሰማ ሲሆን ደምየጠማቸው ሰው በላዎቹ አግኣዚዎች የሶሩዱ የቢሮ ሃላፊን አቶ ከድር አብዶን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ ጉዳት አድርሰዋል::

Minilik Salsawi's photo.

በወለጋ ቀለም ጊዳሜ ወረዳ ወሪ ቀበሌ የአንባገነኑ መንግስት 5 ሰዎችን መግደሉን እና በርካቶች ማቁሰሉ ተሰምቷል::በምዕራብ ወለጋ ዩብዶ ወረዳ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እየተደረገ ሲሆን ወረዳዋ ከፍተኛ የሆነ የተፈጥሮ ሃብት ቢኖራትም የአካባቢው ህብረተሰብ የሀብቱ ተጠቃሚ አለመሆኑና በችግር ላይ የሚገኝ መሆኑ እንዲሁም የሀብቱ ተጠቃሚ አንድ ባለሃብት ብቻ መሆኑ የታወቀ ሲሆን በዛሬው እለት እየተደረገ ያለው ተቃውሞም የመጀመሪያው አለመሆኑ ታውቋል ። በምዕራብ ወለጋ አይራ ከተማ ከፍተኛ የሆነ ታቃውሞ የአካባቢው ነዋሪዎች በማድረግ ላይ መሆናቸው ታወቀ ።የአካባቢው ነዋሪዎች ትግሉ ከተጀመረ ጀምሮ በተቃውሞው ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን የተለያዩ እርምጃዎች ቢወሰድባቸውም ትግሉን አፋፍመው ከመቀጠል ወደኃላ አለመላታቸው ታውቋል ።

 

ምእራብ ሃረርጌ ጋዲሎ ተቃውሞ የተሰማ ሲሆን በበደኖ ሶስት ቀን መንገድ ተዘግቶበት የነበረው የአግኣዚ ጦር በሰባት ካሚዮኖች ተጭኖ ወደ ከተማው ገብቷል:: በምዕራብ ሃረርጌ የዳሩ ለቡ ወረዳ ነዋሪዎች: ትጨርሱናላችሁ እንጂ በፍፁም አትገዙንም በማለት በወረዳው ውስጥ በሚገኙ መቻ ፣ ሚጨታ ፣ ቢልቃዔ ፣ ጋዱሎ ፣ በሚባሉ ከተሞች ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ በቀን በለሊት እያደረጉ መሆናቸው ታወቀ ።ተቃውሞውን አቀጣጥለው የቀጠሉት ታጋዮቹ የዳሩ ለቡ ወረዳ ነዋሪዎች :በጎሎልቻ ፣ ሃብሮ እና አንቻር : አካባቢ ያሉ ወገኖችም እንደተለመደው ከጎናቸው በመቆም ትግሉን እንዲያፋፍሙ ጥሪ አቅርበዋል ።በመጀራ ከሁለት ቀን በፊት አስራ አራት ሰዎች በአጋዚ ወታደሮች መገደላቸውም የሚታወስ ነው ።በሸዋ ቤላሚ ከተማ በኢሊባቦር በበደሌ ከተማ ኢሉ አባቦራ ዞን ተማሪዎች ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን የበደሌ ቢራ ፋብሪካ መኪና ላይም ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል::
‪

በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ ያለው እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ የቆመ ሲሆን የወያኔ መንግስት በቦታው የነበሩ ፖሊሶችን ትጥቃቸውን በማስፈታት ባዶ እጃቸውን እንዳስቀራቸውና በአካባቢውም የአጋዚ ጦርንና ከሱማሌ ክልል የሆኑ ወታደሮችን ማስፈሩ ታውቋል ።

በተያያዘ ዜናም ሞሉ ሃለኬ የተባለውን ተማሪ ጢሌ ቀበሌ ላይ በዛሬው እለት የቀበሌው አስተዳዳሪ የሆነው ከነዮ ዋሪዮ የሚባለው አንተ አሸባሪ የኦነግ አባል ነህ ካለው በኃላ ለወያኔ ወታደሮች በመናገሩ ወታደሮችም አፍነው ከወሰዱት በኃላ ከባድ ማስጠንቀቂያ ከሰጡት በኃላ እንደለቀቁት ታውቋል ።

#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

15 Comments on “በኦሮሚያ ክልል ሕዝባዊ የተቃውሞ ድምጽ ሌሎችንም ብሄሮች እንዳካተተ ተቀጣጥሎ ቀጥሏል::”

  1. lelaw behereseb OLF OROMON
    endeyasgenetil yefelgal ?

    LELAW Hizb Oromeya yemitbal Hager yefelgal ?

    lein ye OLFn tigil lelaw yeqelaqel ?

    YE andinet hailoch begara weyanen enabariralen !!

    and Ethiopia,,, and Senqeq,,, and Hizb !!!!!!

  2. lelaw behereseb OLF OROMON
    endeyasgenetil yefelgal ?

    LELAW Hizb Oromeya yemitbal Hager yefelgal ?

    lein ye OLFn tigil lelaw yeqelaqel ?

    YE andinet hailoch begara weyanen enabariralen !!

    ye tegentay tigil aldegifim

  3. YALEW

    manew Gind? manew kirinchaf ?? KKKK

    KE oROMO BEFIT EKO BEZACH hager Gamo nebere !! welayta nebere,, Amara nebere Gurage nebere ,, Afar ,, Sumale nebere!

    manew anten Gind yaregeh ??? kkkkkkkkkkk

  4. እናንተ ኦነጎች እባካችሁ ኣስቡ፤ ኢትዮጵያ ለማደፍረስ ብላችሁ ኣይናችሁ እያየ ገደል ልትገቡ ነው ። kkkkk

  5. ኦህዳድ ኦነግ ነው ሥንፍቀው አላችሁ ኦሮሞ በቃኝ ሲል ኦነግ አላችሁት አማራው ሲጀምር ደግሞ ቅማንትና ወልቃይት የኢትዬጵያ ሣይሆኑ የትግራይ ሪፐብሊክ ናቸው አላችሁ ቤንሻንጉልን ደግሞ አይ የደቡብ ሱዳን ናቸው ሥርያቸው ኢትዬጵያውያን አይደሉም ይሸጡ አላችሁ ይህ በታትነህ ከፋፍለህ ግዛ የብሄር ፖለቲካን ለማጥፋት ሁሉም ባንዳ ያልሆነ ኢትዬጵያዊ ሊዋጋው ከወዲሁ ይገባልና በርቱ።

  6. መንጋ አህያ ሁሉ ! ! ! ስለኦሮሞ መገንጠል ውይም አለመገንጠል አሁን አፋችሁን ከምትክፍቱ ለምን ስለ ዘርኛው እና ከፋፋዩ ወያኔ መወገድ አትጨነቁም ? ? ? ? Who is bleeding Ethiopia for the last 25 years ? ? ? ዳውድ ኢብሳ who is simply hiding in asmara or sibihat nega ? ? ? ? ኦሮሞው ልክ እንደ አማራው ሁሉ በስተሳሰብ እና በአመለካከቱ የተከፋፈለ ነው።በአንድ ላይ አድሞ አግሪቱን እያጠፋት ያለው ትግሬ ወያኔ ነው።በዚህ አጋጣሚ ለሞረሽ ወግኔ ሊቀመንበር የተከበሩ አቶ ተክሌ የሻው ሰሞኑን በለቀቁት olf በማራው ሕዝብ ላይ ስለተፈጸመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ይከንን ጊዜ መርጠው ይከንን ጊዜ መርጠው ይከንን ጽሁፍ መልቀቃጨው ያልተገባ መሆኑንና የወያኔን እድሜ እንደማራዘም መሆኑን ላስገነዝባቸው እወዳለሁ።ሕግና ስርአት ሲሰፍን ነፃነት ሲከበር ሕጉ ራሱ ውንጀለኞቹን እያደነ ይለቅማቸዋል። At this moment let us join forces with the oromo uprising.Lets listen to professor Getachew Begashaw and make this call a national call.

  7. ለክፉም ለደጉም ውይይቱ ይቀጥላል ለሀሳብ ግልፆነት ለተግባር ትግልና ስራ

  8. እናሥትውል ዝም ብለን ሀገር ሊበታትን ህዝብን ለሥደትና ለስቃይ አናጋልጥ የትናንት አውሬ ዛሬም አውሬ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*