የትግራዩ ገዢ ጉጅሌ በኢትዮጵያ ያወጀው የዋጋ ተመን የዘር ትስስር ያላቸውን ነጋዴዎች እንደማይነካ ተነገረ
መለስ ዜናዊ የሰሜን አፍሪካው ህዝባዊ አመጽ እሱም ጋር እንዳይደርስ በመስጋት በችኮላ ያወጀው የዋጋ ተመን አንዳንድ ነጋዴዎችን እንደማይመለከት ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።
የግንቦት 7 ሪፖርተር ከአዲስ አበባ ባስተላለፈው ሪፖርት፥ ሌሎች ነጋዴዎች የዋጋ ተመኑን በስራ ላይ አላዋላችሁም በሚል እየታሰሩ፤ ከአገዛዙ ባለስልጣናት ጋር የዘር ትስስር ያላቸው ነጋዴዎች ግን ሸቀጣሸቀጦቻቸውን ባሻቸው ዋጋ እንዲሸጡ ተፈቅዶላቸዋል። ከሁለት ሳምንታት በፊት ተመኑ በታወጀ ማግስት ከ100 በላይ ነጋዴዎች አዋጁን በስራ አልተረጎማችሁም በሚል መታሰራቸው ይታወሳል።
ለምሳሌ ያህል፥ ሃሊውድ የተባለ እና በ22 መገናኛ አካባቢ የሚገኝ መጠጥ ቤት፤ በቢራ ላይ የተጣለውን ተመን ወደ ጎን በመተው ለአንድ ቢራ የቀድሞውን 15 ብር እንደሚያስከፍል ዘጋቢያችን የላካቸው ተጠቃሚዎች መስክረዋል። ሌሎችም በርካታ ከአገዛዙ ጋር ትስስር ያላቸው ሰዎች መጠጥ ቤቶች እና አገልግሎት ሰጪዎች የዋጋ ተመኑን እንደማይከተሉ ዘገባው አመልክቷል።
የወያኔ አገዛዝ በተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጨቋኝ እርምጃዎችን በወሰደ ቁጥር፤ ለራሱ እና ቅርብ ለሆኑት ነጋዴዎች ግን የንግድ እድል የመፍጠር አሰራር እንዳለው ይታወቃል። ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ በአስር ሺሆች የሚቆጠሩ ንጹሃን በግፍ ሲታሰሩ፤ የወያኔ ባለስልጣናት ንብረት የሆነው ትራንስ ኢትዮጵያ እስረኞችን የማጓጓዝ ኮንትራት ተሰጦት ከፍተኛ መጠን ያለው ክፍያ ከህዝብ ካዝና እንደተከፈለው ይታወቃል።