ሻሸመኔ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው:: አዶላ የአግኣዚ ጦር መሰብሰቢያ በእሳት ነደደ::


በምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ እና አዋሳኝ ከተሞች ውጥረቱ የቀጠለ ሲሆን በየሕዝቡ ተቃውሞ ለአምስት ተከታታይ ቀናት እየተሰማ ከመሆኑም በተጨማሪ በዛሬው እለት ወደ ከተማው የሚያስገቡ እና ወደ መሃል አህገር የሚያሻግሩ መንገዶች ተዘጋግተው የከተማው ወጣቶች ከአግኣዚ ወታደሮች ጋር እየተፋለሙ መሆኑ ታውቋል::
ለሻሸመኔ አጎራባች አዶላ ከተማ የአግኣዚ ወታደሮች ጊዜያዊ ካምፕ የሆነ የቀበሌ ጽህፈት ቤትን ለተቃውሞ በወጡ ሕዝቦች በእሳት የነደደ ሲሆን የቢሮ ጠረጰዛ እና ወንበሮችን አውጥተው ሰባብረው ከመንገድ ዳር ጥለውታል::በትናላትና ቀን እስር ቤት ከፍተው 125ይ እስረኞችን ማስለቀቃቸውን ሲታወስበዛሬው ተቃውሞ ደግሞ የአዶላ ቀበሌን አጋይተውታል::

