ኬንያ እንደመኖር ነው ? ? ? – ግርም ካሳ

ኬንያ እንደመኖር ነው ? ? ? – ግርም ካሳ

ጃዋር መሐመድ እኛ እንድናነብው ይመስለኛል በአማርኛ ትንሽ ዘርዘር ያለ ነገር ጽፏል። አንድ መሰረታዊ ነጥብ ላይ ጥቂት ማለት እፈልጋልሁ።

“ ኦሮሚያ የኦሮሞ ነች ስንል ኦሮሚያ የኦሮሞ ህዝብ ሀገር ነች ( Oromia is homeland of the Oromo people) ማለት ነዉ” ይለናል ጃዋር።

ኦሮሚያ የኦሮሞዎች አይደለችም ያለ ሰው ማን ነው ? በሚገባ Oromia is homeland of the Oromo። ሆኖም እነ ጃዋር የማይቀበሉት አንድ ሐቅ አለ። በአዲስ አበባ 90% የሚሆነው ሕዝብ አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ አይደለም። በአዳማ፣ በቢሺፍቱ፣ በሻሸመኔ፣ በጂማ …እንዲሁም በርካታ የኦሮሚያ ከተሞች የሚኖሩት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኦሮሞ ያልሆኑ አሉ። ጃዋር ራሱ ከጥቂት ሳምንታት በፊት እንደተናገረዉም ኦሮሚያ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ናት። ታዲያ ለነዚህ ወገኖች ኦሮሚያ የነርሱም homeland አይደለችምን ? በሚገባ ናት። አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጂማ. ነጆ፣ ጊምቢ …ሁሉም የኦሮሚያ መሬት የሁሉም ኢትዮጵያዉያን homeland ነው። የሁላችንም ነው።

ቤኔሻንጉል ክልል ከ25% በላይ፣ በሃረር ክልል ከ56% ነዋሪዎች ኦሮሞዎች ናቸው።፡በአማራዉ ክልል በከሚሴ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ልዩ ዞን አላቸው። በራያና አዘቦ ኦሮሞዎች በብዛት አሉ። በሶምሌ ክልል ዉስጥ የሚኖሩ ብዙ ኦሮሞዎች አሉ። ታዲያ ከኦሮሚያ ዉጭ ያሉ ቦታዎች የኦሮሞ homeland አይደሉምን ? ሁሉም የኢትዮጵያ መሬት የኦሮሞዎች መሬት ነው።

ስለዚህ ኦሮሚያ የነዋሪዎቿ ናት በሚል ብንስማማ ይሻላል !!!!

“ኦሮሚያ የኦሮሞ ነች ማለት ኬኒያ የኬኒያኖች እንደ ማለት ነው። ይህ ማለት ኬኒያ ወይም ኦሮሚያ ውስጥ ሌላ ሰው መኖር ዜጋ መሆን አይችልም ማለት አይደለም። በሚገባ ይችላሉ” ሲል ጃዋር ነገሮች የበለጠ ይለጥጣቸዋል። አዲስ አበባ በኦሮሚያ ዉስጥ እንደመሆኗ፣ አዲስ አበባን ጨመሮ በኦሮሚያ ዉስጥ የሚኖሩ ኦሮሞ አይደለንም የሚሉ፣ ወይንም ኦሮሞ ሆነው አፋን ኦሮሞ የማይናገሩ፣ የኦሮሞና የሌሎች ብሄረሰቦች ድብልቅ የሆኑ (እንደኔ) ግን “ኦሮሞ” አይደላችሁም የሚባሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉይን ፣ በኦሮሚያ ዉስጥ ሲኖሩ፣ በኬንያ እንዳሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ ነው ጃዋር ለማሳየት የሞከረው። ያን ያህል ለቋል።፡

ሲያጠቃልልም “ኦሮሚያ የኦሮሞ ነች የሚለውን መፈክር ልናፍርበት ሳይሆን በደማችን እውን ለማድረግ እየታገልንለት ያለ ህያው አላማችን ነው። ይህን አላማችንን የሚቃወም ካለ ከኦሮሞ ጋር መስራት አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን ፀረ-ኦሮሞ በመሆኑ አጥብቀን አንታገለዋለን “ ሲል በነርሱ አይምሮ ዉስጥ ያለችዋን የኦሮሞዎች ብቻ የሆነች ኦሮሚያ፣ እዉን ለማድረግ ደም እንደሚፈስም ያስጠነቅቀናል። ይሄ extrem radicalism ነው። የከረረ አክራሪነት !!!!! ይህ አይነት ፖለቲካ እጅግ በጣም አደገኛ ፖለቲካ ነው። ሁላችንም በፍቅር፣ ተከባብረን የምንኖርባት ኢትዮጵያ እንዳትገነባ እንቅፋት የሚሆን ነው። ማንም ኢትዮጵያዊ ሊታገሰው የሚገባ ፖለቲካ አይደለም። በተለይም የኦሮሞ ልሂቃን ሊያወግዙትና ሊመክቱት የሚገባ ፖለቲካ ነው።

ጃዋር ለምን ይህ አይነቱን መርዛማ ፖለቲካ እንደሚረጭ ሊገባኝ አልቻለም። ብዙ ኦሮሞዎች ጠንካራ ተቃዉሞ እንዳቀረቡበት አውቃለሁ። በቁቤ የጻፈውና እነ አበበ ገላው ያስተረጎሙትን ጽሁፍ የጻፈው ከኦሮሞዎች የቀረበበትን ጠንካራ ትችት ለመመከት ነበር። ” While bereaving the sacrificed, rejecting the cause is unacceptable I have realized my reaction towards our adversary has offended some of our people (Oromos)” ሲል ራሱ ጃዋር በኦሮሞውሽ ዘንድ ተቃዉሞ እንደደረሰው ማመኑን እናያለን። ይሄ ተስፋ የሚሰጥ ነው። ሰዉዬ ብዙ ጭፍን ተከታዮችን እንዳሉት የሚቃወሙትም እጅግ በጣም ብዙ ናቸው።

ይሄን ጥቂት ቁልፍ ነጥቦች ላስቀምጥ፡

1. የጃዋር ፖለቲካ ከምንም በላይ የሚጎዳው የኦሮሞ ማህበረሰብ ነው።

2. ጃዋር በኢሳት ላይ ጠንካራ ትችት ያቀርባል። የአኖሌና የጨለንቆ ሃዉልቶች ያሉበት ምስሎች ይቆርጣሉ፣ የኦነግ ባንዲራን አያሳዩም ….ምናምን petit ምክንያቶች ነው ያቀረበው። ግን ዋናው ኢሳት ላይ ያለው ችግር ቦታዬን ሊወስዱብኝ ነው በሚል ነው። ኢሳት የአፋን ኦሮሞ ፕሮግራም ጀምሯል። የኦሮሞ ማህበረሰብ ከኦሮሞ ሜዲያ ኔትዎርክ በተጨማሪ ሌላ አማራጭ አገኝ ማለት ነው። ቢቢሲ በአፋን ኦሮሞ ስርጭት እንዲያቀርብ ዘመቻ ስናደረግ አልነበረመ እንዴ ? ብዙ አማራጮች ለህዝብ ይጠቅማሉ። ጃዋር ግን በባህሪው እኔ ብቻ መሰማት አለብኝ የሚል በመሆኑ የኢሳትን የኦሮምኛ ፕሮግራም አልወደደዉም።

3. ጃዋር በግንቦት ሰባት ላይ ትችት አቅርቧል። ግንቦት ሰባት ለምን ተተቸ አልልም። እኔም የማደርገርው ነው። ሆኖም ጃዋር፣ ችግር ያለው ግንቦት ሰባት ላይ ሳይሆን ከግንቦት ሰባትና ሌሎች ኢትዮጵያዊ ኃይሎች ፣ በጋራ ለመስራት እያተነጋገሩ ያሉ የኦሮሞ ኃይሎች ላይ መሰለኝ። በተዘዋዋሪ መንገድ እነ ሌንጮ ለታን እያስፈራራ መሰለኝ።

የኦሮሞ ማህበረሰብ በአሁኑ ወቅት ወሳኝ ትግል እያደረገ ነው። ብዙዎች እየታሰሩ፣ እየተገደሉ ነው። ላለፉት ሶስት ወራት አገዛዙ ኮስሜቲክና ዉጫዊ ለዉጦች ከማድረግ ዉጭ፣ የለወጠው ምንም ነገር የለም። በተናጥል የተደረገውን የኦሮሞዎች እንቅስቃሴ ለጊዜውም ቢሆን አገዛዙ የተቆጣጠረው ይመስላል። በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ ይሄን ያህልም ግፊት አልታየም። ያ ሁሉ ሰው ሞቶ፣ ያዉ ሁሉ ተደብድቦ በአጭሩ የመጣ ለዉጥ የለም። ሐቁ ይሄ ነው።

ይሄም የሆነበት ምክንያት እንቅስቃሴው በዋናነት በኦሮሚያ ወዳሉ ትላልቅ ከተሞች እንዲሁም በሌሎች ክልሎች ባለመዛመቱ ነው። ከዚህ የተነሳ ሌላው ማህበረሰብ የኦሮሞዎችን እንቅስቅሴ እንዲቀላቀል፣ የትግሉ አጀንዳ በተቻለ መጠን አገራዊና አሰባሳቢ እንዲሆን ማድረጉ አስፈላጊ በመሆኑ፣ የኦሮሞ ኃይሎች ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻቸው ጋር ዉይይቶች ጀምረዋል። እንዴት ትግሉን እናቀናጀው በሚል ። ጃዋር እዚህ ላይ ነው ችግር ያለው።

ጃዋር ይሄንን ለመብት፣ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲ የሚደረግን የጋራ እንቅስቃሴ ለምን ይጠላዋል ? የኦሮሞ ማህበረሰብ እርሱ ከሚመራው የኦሮሞ ሜዲያ ኔትዎርክ ዉጭ ሌላ አማራጭ እንዳይኖረዉስ ለምን ይፈልጋል?

አንድ መልስ ነው ያለው።ሰዉዬው የራሱን ተክለ ሰዉነት ለመገንባትና ሰው ሁሉ ስለርሱ እንዲያወራ የሚፈልግ ሰው በመሆኑ ነው። የሚሰራው ለኦሮሞ ማህበረሰብ ጥቅም ሳይሆን ለራሱ ጥቅም ነው። ይሄንን ሁላችንም በተለይም የኦሮሞ ማህበረሰብ መረዳት አለብን። አንድ ሰው የትብብርን መንፈስ እንዲያደፈርሰ ሊፈቀድለት አይገባም። ዉይይት ጥሩ ነው። ግን ትኩረቱ መሆን ያለበት መሰባሰቡ ላይ ነው። ተስፋ አለኝ እነ ጃዋር የሚያስቀምጡትን መሰናክሎች አልፈን እንደምንሄድ። እነ ጃዋር ወደኋላ ሊጎትቱን ነው። ላለፉት 25 የተከፋፈልነው አይበቃም እንዴ ? አሁን የሚያስፈለገው አንድነት ነው።

20 Comments on “ኬንያ እንደመኖር ነው ? ? ? – ግርም ካሳ”

  1. Thank you. The reason of Oromo struggle could not achieve its goals are because of people like jwahar. This guy used to work with woyanne. In past we heard him say that why other Ethiopians live and work in Addis Ababa and other cities of Oromo region. Also he warned us that violence against others. We should pray and make sure that this kind of individual never come to power. God forbid jawhar and people share his evil idology come to power,they shade blood in large scales.his ambition to kill scare me. We talking about millions of innocent people. He is not struggle for freedom of oromia but to slaughtered non Oromo speaking Ethiopians. The most dangerous person a live is jwahar(little Adolf hittler).

  2. በመጀመሪያ ደረጃ አማራ ሚባለዉ ብሄር ከማንም በላይ በሳል አእምሮ ባለቤት የሆነ ህዝብ ነዉ፡፡ ባለፉት አርባና ሃምሳ አመታት የተደረገዉን በሙሉ ተመልክቷል፤ ገፈት ቀማሽም ሆኗል፡፡ ስለሆነም በአማራ ስም በመነገድ ብዙዎቹ አትርፈዉበታል፡፡ አማራ ነን በሚሉ የስልጣን ጥመኞች ሲጨቆን ኖሯል፤ ከዚህ በኋላ የማንም ፖለቲካ ማስፈጸሚያ አይሆንም፡፡ ካስፈለገ ኢትዮጵያ ትኖራለች፤ የማይሆን ከሆነም መበተን ትችላላችሁ፡፡ ኢትዮጵያዊነት የአማራ ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ አማራም ሃገርና ክልል ጀግና ህዝብ አለዉ!!
    ስለዚህ እባካችሁ አማራን ተዉት!!! ከፈለጋችሁ መገንጠል መብታችሁ ነዉ!! አማራ አልከለከላችሁም!! ‹‹ አህያዉን ፈርቶ ዳዉላዉን›› ነዉ ያለ የሃገሬ ሰዉ!!! ኦሮሞ የተጣላዉ ከህዉሃት ጋር ከሆነ፤ ኦሮሞ የተጣላዉ ከኦህዴድ ጋር ከሆነ አማራ ምን አገባዉ!! እንደጀመራችሁ እናንተዉ ጨርሱት! አማራ ከዚህ በኋላ ለራሱ መብት ብቻ ይቆማል!! ስጋት አይግባችሁ! በቅርቡ በሁለት አመታት ዉስጥ ማን እንደሆነ ታያላችሁ! እድሜ ብቻ ይስጠን፤ አማራ ከሃገራችን ይዉጣ ትላላችሁ! ኦሮሚያ የኦሮሞ ናት ትላላችሁ! ታዲያ አማራን እዝህ ዉስጥ ምን ጥልቅ አደረገዉ! ሁለታችሁ ስትጣሉም አማራን ማጥላላት ስትፋቀሩም አማራን ማጥላላት! አረ ጎበዝ ይደብራል! ከፈለጋችሁ ሁለታችሁም መገንጠል ትችላላችሁ!! በአሁኑ ወቅት እኮ አማራ የሚባል ብሄር በክልሎች በከተሞች ካልሆነ በቀር በገጠሩ ክፍል የለም!! ስለሆነም እንዳትሸወዱ ጎበዝ! ኢትዮጵያዊነት፣ አንድነት የአማራ ጉዳይ ብቻ አይደለም!! አብዛኛዉ የተማረዉ የትግራይ ህዝብ በሁሉም ክልሎች ላይ ተበታትኖ ይገኛል! አብዛኛዉ ነጋዴ የጉራጌ ህዝብ በሁሉም ከተሞች ተበታትኖ ይኖራል! ብዙ የኦሮሞ ህዝብ በአማራ እና በቢኒሻንጉል ክልል ይኖራል! ታዲያ ኢትዮጵያ ለምን በአንድ ጀምበር ብትንትን አትልም! አማራ ከሌለ፤ ኢትዮጵያዊነት የለም!!
    ስለሆነም እደግመዋለሁ እባካችሁ አማራዉን ተዉት!!! ተስማምታችሁ የፈጠራችሁትን የጎሳ ፖለቲካ በማራመድ ‹‹ተስማምታችሁ ዝረፉት››!! ‹‹የጎሳ ፖለቲካ የማር ቀፎ ነዉ›› እንዳለዉ ጸሃፊዉ የለመዳችሁትን ማር በብሄር ሰበብ እየቆረጣችሁ ብሉ!! አማራን ተዉት አቦ!! ሁለታችሁም የ16ኛዉ ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ የያዛችሁ ‹‹ታጥቦ ጭቃ›› ናችሁ!!

  3. Girma:

    Sorry to say but you are addicted to writing garbage – spewing your venom to mask your continuing fear and hate of the oromo. In the past weeks, many have stated that you are a Woyane agent or have made your illiterate mind at the service of the Woyane.

    You are no match to the intelligent and fearless, young oromo leader – Jawar. Take a look at yourself in the mirror – you will see yourself in the text that you wrote;

    ሰዉዬው የራሱን ተክለ ሰዉነት ለመገንባትና ሰው ሁሉ ስለርሱ እንዲያወራ የሚፈልግ ሰው በመሆኑ ነው።

    Just go away and save yourself another embarrassment!

  4. Good observation Mr. Kassa. We have to expect individuals with fascist ideology from all coroners and Jawir is one of them. Our focus and strategy should be to alinate such fascists and consolidate the gains. We have a long way to go and Jawir is a distration. Expect some pundits who will try to redicule Oromos and their genuine strugle for their rightful place in democratic Ethiopia. We have to fight them too!

  5. buffa kkk
    Amaran ye sera mefelegeya arekew ende ? ere serteh bela !
    aMARA Ethiopia negn eyale yemotal enji ,,lenante ye siltan mewetacha ayhonim

    Amara le netsanetu endetagel Mogzet ayfelgim !!
    tint ke abatochu yeweresew ye jegninet wenew ahunim ale !!
    AHUN ADAME PARTY EYEFEBEREKISH KKKKK

    ye Amara netsa awchi honsh ?

    Qetafi !

  6. አቶ ግርማ ካሣ ጃዋርን እንተወው እሺ ኢትዮፒያ ውስጥ የዘር ክልል እና የዘር ፖለቲካ ለምን አስፈለገ? ይህንን ደግሞ ህወሃት እና የኦሮሞ የዘር ልሂቃኖች እንጂ ሊላ ማንም አልፈጠረውም በተዳጋጋቢ እንደሰማነው ለዚህ በዘር የመደራጀት ችግራቸው ሁለቱም ወገኖች የሚያቀርቡት አምሃራ የሚባል ስረአት ለዘመናት ስለገዛና ኢትዮፒያን የአምሃራ ስላደረጋት የሚባል ክስ አለ ይሂ ነው በዋናነት መታየት ያለበት ምክንያቱም ኢትዮፒያን እንደ አገር ከተቀበልን 81 ብሂር ያለባትን አገር በተወሰኑ ዘሮች ስም ጨፍልቀን መግዛት የለብንም ሲጀመር አምሃራ ኢትዮፒያዊ እንጂ አምሃራ የሚባል የአምሃራ መሪት የለውም ኦሮሞም ቢሆን የኦሮሞ መሪት የሚባል የለውም ማህበረሰቦች እንደየ ታሪካቸው ሰፍረዋል ስለዚህ አንዱ ስፍራ የተደበላለቀ ማህበረሰብ ሊገኝ ይችላል አንዱጋ የአንድ ማህበረሰብ ብቻ ሊጋኝ ይችላል ስለዚህ እነዚህ ሁሉ ህዝቦች ግን ኢትዮፒያ መሪት ላይ ናቸው ኦሮሞ በኢትዮፒያ ውስጥ የተለያዩ ቦታዎች ሰፍራል አዎ ግን የሰፈረበት ሁሉ የኦሮሞ ነው ያለው የትኛው ታሪክ ነው? በአዲሱ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተለያዩ ማህበረሰቦች ያሉት እኮ ኦሮሞ ለነዚህ ማህበረሰቦች አገር እንደሰጣቸው ተደርጎ ለምን ይቆጠራል? እነሱም የራሳቸው መሪት ነው ስለዚህ በኦሮሞ ጠቅልሎ መጥራት ነው ትልቅ አደጋ ያለው ኢትዮፒያዊያን ከተባሉ የከሊ መሪት የከሊ አይባሉም ስለዚህ ፍትሃዊነው የአምሃራ መሪት ብሎ በአምሃራ ውስጥ ያሉ ብሂረሰቦችን አምሃራም አይደለም አገሩን መሪቱን የሰጣቸው በአምሃራ ክልል ሊጨፈለቁ የተፈለገበት የፖለቲካ ሂደት ግልጽ መሆን አለበት ዋናው የፋሺት አገዛዝ ከፋፍለህ ግዛው ዝረፈው መጠቀሚያና የዘር ልሂቃኖች በ 21ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮፒያን ህዝብ ወደሃላ 100 አመት ብቻ ሳይሆን ከዛም እያለ ወደሃላ የኢትዮፒያ ህዝቦች የአሰፋፈራቸውን ሁኒታ እራሱ የኢትዮፒያን ታሪክ እንደ አገር መቆም ልናይበት እና እርስ በርስ የሚያጋጨን ሂደት ላይ ነው ያለነው አንድ አገር ሲቆም ያልተጋጨ ማህበረሰብ የለም አምሃራ ለአምሃራ ይጋጫል ኦሮሞም ለኦሮሞ ይጋጫል ትግሪም ሊላውም እንደዛው በዋናነት ግን ኢትዮፒያ እንደማንኛውም አገር ስትቆም አንዱ አንዱን ፈልጎ በፍቅርም ይሁን በሃይል እንደ አገር ቆማለች በታሪካችን ኢትዮፒያ እንደ አሁኑ የፈረሰችበትም ዘመን አለ ከዛም በፊት እንደ አገር ቆማ የተዳደረችበት ታሪክ አለ ኢትዮፒያ ስትፈራርስ መልሰው ለማቆም በዛ ዘመን የነበሩ ህዝቦች የራሳቸው መሰረታዊ ምክንያቶች ስላላቸው እና ህዝቡም ልክ እንደአሁኑ በኢትዮፒያዊነቱ መኖር የሚፈልግ ወይም በየባላባቱ መገዛት የሚፈልግ ታግሎ ኢትዮፒያን መልሰው አቁመዋል ስለዚህ ኢትዮፒያ ውስጥ አምሃርም ሆነ ኦሮሞ እንዲሁም ሊላው ዛሪ ላለው ማንነታችን አሰፋፈራችን ከመሰረታችን ጋር ና ከታሪካችን ጋር በሂደት የመጣንበት መንገድ ነው ስለዚህ ኢትዮፒያ እንደ አገር የብሂር ብሂረሰቦች አገር መሆናን ማመን አለብን:: ለዚች አገር እኮ የጥንት የኦሮሞ አባቶችም ሆኑ አምሃራው ሞቶላታል ትልቃን ኢትዮፒያ ለመቆጣጠር እንጂ ዛሪ የዘር ልሂቃኖች እንደሚሉን በክልል ተቆልፈው ይሂ ክልል የኒብቻ በሚል በንገድ አልመጡም ስለዚህ ይህ ነው ትልቁ ችግር ኦሮሞው አምሃራውስጥም ሊላው ማህበረሰብ ውስጥም ገብቶ በመኖሩ ኢትዮፒያዊ ሆናል አምሃራም እንደዛው ኦሮሞ ሲሰፍር አምሃራ አልተፈጠርም ወይም ሊላው ማህበረሰብ አልተፈጠርም የሚባልበት የ 21ኛው ክፍለዘመን ይዘር ፖለቲከኖች እንደ ስልጣኒ አድርገውም የሚጠቀሙበት ይመስላል ኦሮሚያ ለኦሮሞ ሲባል በምንም ተአምር ተቀባይነት የለውም ወያኒ 100% ይህንን አካሂድ ስልጣን ለመያዝ ተጠቀመበት እንጂ እውነት አምሃራ የኦሮሞን መሪት ወሮ ነጥቆ ቅኝ ግዛት ተገዝቶነው የሚል አስተሳሰብ የለውም ታሪካን ሁሉም ያውቃሉ ይህቺ ሲስተም አምሃራውን እና ኦሮሞውን ወደ ሃላ እየወሰደ ከታሪክ ቅራኒዎች ጋራ እኒ ነበርኩኝ አንተ ነበርክ እየተባለ በመለያየት ቅራኒዎችን ሃላቀር አስተሳሰቦችን ከማራመድ በስተቀር እውነት ላይ የተበሰረተ የአገር ፖለቲካ ለማራመድ አይደለም ስለዚህ በምንም ተአምር ለኢትዮፒያ ህዝብ እንደ አገር ኢትዮፒያን ካየናት የዘር ፖለቲካ አይሰራም:: የሰለጠነ ህዝብ በሃስብ ተሰባስቦ በዲሞክራሲ የምትመራ አገር መፍጠር ብቻነው የሚያዋጣው የዘር ፊዲራሊዝም ሳይሆን ፊዲራሊዝም ኖሮ ከዘር ፊዲራሊዝም ሊላ ስም ቢሰጠው ሁሉንም ያገር ባለቢትነቱን እንዲሰማው ማድረግ ነው ሊላው እንዲ ሲባል ቃንቃችን ባህላችን የሚባል ነገር አለ ለመሆኑ የኢትዮፒያ ህዝብ ቃንቃውና ባህሉ ብቻ ሳይሆን እኮ ዘሩም ለብሩ ሺ ዘመናት የተቀላቀለ ህዝብ ነው ሚሊሊክ ሳይሆኑ ከዛም ከዛም ለብዙ ሺ ዘመናት አብሮ በመፈላለግ የመጣ ሂደት ነው ስለዚህ የአንድ ማህበረሰብ ቃንቃም ባህልም ደግሞ የሚያድገው በክልል የከሊ መሪት እየተባለ ስለተቆለፈ አይደለም ዋናው ባገራችን ያሉ ቃንቃዎች በሙሉ ሃብታችን ናቸው እነዚህ ቃንቃዎች እንዳይጠፉም ሆነ እንዲበለጽጉ ልሂቃኖች የራሳቸውን ምርምር እያደረጉ መስራት ነው ባህሉንም እንደዛው ለኢትዮፒያኖች ኢትዮፒያዊያን መንግስት ካለና ለኢትዮፒያ ህዝቦች ለህልውናቸው የሚሰራ መንግስት ካለ የዚህ ብሂር ይሂ ነገር ቢሰራለት አገራችን ታድጋለች እዚህ ጋ እንዲህ ቢደረግ ላገራችን ይህ ይተቅማል ተብሎ የሚሰራበት በሃሳብ የተለያዩ መልካም አሳቦችን በማቅረብ ነው የግዲታ በዘር መሆን የለበትም ምክንያቱ ያገር ስሚት እንዲኖረን እና ማንኛውም ብሂረሰብ ኢትዮፒያዊ መሆኑን ማመን አለብን :: በተለይ ጃዋርና የጃዋር ዘመዶች ኢትዮፒያዊነትን በአምሃራ እና በትግሪ የተሰየመ አድርገው ይቆጥራሉ ይሂ ደግሞ ምን ያህል የነዚህን ሰዎች ሃላቀር አስተሳሰብ እንጂ አባቶቻቸው እንዲ የሚያስቡ አይመስለኝም ምክንያቱም አንድ ታሪክ አንድ ቦታ ይጀምራል የታወቀነው ስለዚህ ኢትዮፒያ የምትባለው አገር እንደ አዲስ ስትገኝ በአክሱም ተገኘች ማለት አሁን ላለነው ኢትዮፒያኖች በየትኛውም ቦታ ታሪካችን ነው አክሱምን ለማናውቅ እካን ኢትዮፒያ ግን እያደገች ከአክሱም መንግስት ላሊበላ እያለች አቢሲኒያ የሸዋ መንግስት አቁማ ኢትዮፒያ አድጋለች ስለዚህ መጠሪያችን ኢትዮፒያዊያኖች ነን ለምን አምሃሪኛ ቃንቃ አደገ ከሆነ በወቅቱ የነበሩ ልሂቃኖች አሳድገውታል ተናጋሪው አለ ግን ፊደል በመፍጠራቸው እሰየው የሚያስብል እንጂ የኦሮሞ ቃንቃ ከአምሃሪኛ ቃንቃ የበለጠ ወይም ኢትዮፒያ በአምሃራዎች ነው የምትታወቀው ብሎ ፖለቲካ መስራት ከምንም ጋራ አይሂድም ኦሮሞ ለምሳሊ ከደቡብ ተነሳ ቢባል ደቡብ ላይ ተቀምጦ ቀረ ማለት አይደለም ታሪኩ ከዛ ጀምሮ ይሆናል ግን ኢትዮፒያ እከሊ ከዚህ መጣ ከዛ ተነሳ ሳይሆን ኢትዮፒያን እንዲት አገር አድርገው አቆማት ነው ይህንን ስናይ ኦሮሞ እንደ አምሃራ የዘር ስም ነው ዛሪ 25 አመት የተፈተረችውን ኦሮሚያ አምሃሮች መንግስታን አፍርሰው ወደ ኢትዮፒያ ቀላቀሉ ብሎ ማውራት ፖለቲካ አይደለም ኢትዮፒያ ማንም የማይክደው የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ አገር ነች ይህቺ ሃይማኖት በዘመናቸው እያስፋፉ ህዝቦችን አንድ አድርጋለች ለወላሞው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ለ ጉራጊው ሆነ ለራሱም ለኦሮሞ ለአምሃራም በሚሊሊክ ዘምን አይደለም ክርስትናን የተቀበሉት በኢትዮፒያም የ እስልምና ሃይማኖት የራሱ የሆነ ታሪክ እና መስፋፋት አለው ጃዋር አንዲ የ እስልምና ተከታይ ኦሮሞዎች መብት ካልተፈታ የሊላው እስልምና በብት አይፈታም አለ ለምን ሲባል የታሪክ ቅርኝት ስላለው አለን ok! የኢትዮፒያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ከሁሉም ማህበረሰብ ጋር ቅርኝት አላት ግን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሲነሳ የአጺዎች የአምሃራዎች ያለፈ ስረአት እየተባለ ኢትዮፒያዊያንን አሁን ለመከፋፈል የሚደረግበት ፖለቲካ መሰረተ ቢስ ነው በዘመኑ የነበሩ አምሃራዎች አጺዎች ኢትዮፒያን ሲያቆሙ በኢትዮፒያ ኦርቶዶክስ ስር ቢሆን እኮ መብታቸው ነው ያ በዘመኑ የነበረ ስረአት ነው ስለዚህ አጺዎች ስረአት መስርተው ህዝቡን ኦርቶዶክስ እንዲቀበሉ አድርገዋል ተብሎ የየትኛውን ዘመን ክስ ነው አምሃራ ሊከሰስ የሚችለው በዚህ በአጺዎች ዘመን አምሃራ ብቻ ሳይሆን እስከ ሃይለስላሲ ድረስ የተለያዩ አጺዎች አስተናግዳለች ለምሳሊ ንጉስ ጦናን አጺ ናቸው የራሳቸው ታሪክ አላቸው አምሃራ አይደሉም አጺ ዮሃንስ ትግሪ ናቸው, አሲ ሃይለስላሲ ንጹህ አምሃራ አይደሉም ,ሚሊሊክም ቢሆኑ ንጹህ አምሃራ አይደሉም ስለዚህ ኢትዮፒያ በአምሃራ ነው የምትታወቀው እየተባለ እንደው ዘረኝነትን ማሰባሰቢያ ካለንበት ዘመን ጋ ይሂዳል? ጎበዝ እነዚህ ሁሉ አሲዎች ኢትዮፒያዊያኖች ናቸው ስለዚህ የአምሃራ አባቶች በክርስትና ሃይማኖታቸው የታወቁ አጺዎች ነበሩ ኢትዮፒያንም ህዝብ ክርስቲያን ያደረጉ እየተባለ ለሚባለው ለመሆኑ እስልምናን እየታረዱ በግዲታ የተቀበሉ የኢትዮፒያ ህዝቦች ምን እንበላቸው? አምሃራው ክርስቲያን ቢባልም እስልምና የተቀበለውን ታዲያ ከጃዋር ታሪክ ጋር ቅርኝት ካለው ክርስቲያን ኦሮሞ ደግሞ ከአምሃራ ታሪክ ጋር ቅርኝት ቢኖረው ምንድነው ችግሩ ? የጎሳ ፖለቲካ የሃላ ቀሮች አስተሳሰብ ነው በአጠቃላይ አሁን ያሉ የዘር ፖለቲከኞች የፈረጅ አችከሮች በገንዘብ የተገዙ በመሆናቸው ስለአገር ምንም ስሚት የላቸውም ወያኒ ባንዳም እንደዛው ነው ፈረጅ የሚያምነው ጥቁር ለፈርጅ የተገዛ ባሪያ ነው ይህን እንደ ሃይማኖት ያምናሉ ስለዚህ የኛ አባቶች ደግሞ ነጭና ትቁር አንድ መሆናቸውን አሳይተዋቸዋል ከወያኒ ባንዳ በስተቀር ዛሪ ወያኒ ባርነት እንዲት እንደሆነች ስለጥኖ ለዘመናት የቀረበት ባንዳነት ለፈርጅ አሽከርነት እንዲት ኢትዮፒያዊያንን ወደ ባርነት ለመክተት በፈርጅን አምልካ በፈረጅ ሃይል የዘር ልሂቃኖች አሽከሮች በገንዘብ ለወያኒ እንዲገዙ አገር እንዳይሉ ከአገር ይልቅ ገንዘብ ገንዘብ ስለሚያስቡ ነው ሊላ ነገር የለም:: አንድ አባት ያሉት ነገር አለ የደቡብ ሰው ነኝ አሉና የአምሃራ የወያኒን አሽከር እንዲህ አሉት አንተ አታፍርም አምሃራነኝ ስትል እባካችሁ ይሂ ኦሮሞ ጉራጊ አምሃራ እያላቹሁ የምትሉትን አቁሙ ባባቶችህ ክልል ለከብት ነው አሉት ይህ ትክክል ነው ክልል ለከብት ነው:: ቀጥለውም የጎባጣ አሽከር አጎንብሶ ይሂዳል ለምን? ሲባል ጊታውን ለመምሰል አሉ እኚህ አባት ስለሱዳን መሪት መሂድ ተናደው ስለዚህ የዘር ልሂቃን ሁሉ የጎባጣ አሽከሮች ባሪያዎች ናቸው ኢትዮፒያዊነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ከስልጣኒጋ ምንም ግኝኙነት የለውም ከዘመኑጋራም ብንም ግንኙነት የለውም

  7. Jawir is still kids let wait until reached 40 then we talk.
    you see how woyane gave us headache we separated with ethnics and we talked about ethnics please don’t be foolish let’s talk about unity.Ethiopia is for all Ethiopians.

  8. Oromiyaan teenna hin tuqinaa nurraa nuhuu irra jirraa/2. Maaliif waa’een oromiyaa akkanatti isin yaachisaa?.waa’een jawaari fi qeerroo oromoo waan isin galchuu miti.isinis biyya keessan bilisoomsadha irra jiraadha.OROMIYAA irraanfadhaa.

  9. The struggle is to realize sovereign regional state of oromia in Ethiopia. Then using what ever resources we have for our development. And sharing some of them fairly with other ethnic groups. Oromo has never been traveled to tigray to get a piece of land. But a large number of oromoprofessionas working in tigray. The same will true with oromia. Ethiopians can live n work in oromia but that doesn’t mean that they have to own land.

  10. please do not forget Jaware there is no Oromia k/hager it is an imagenery line given by EPRDF

    you have to thank you TPLF

    again do not forget the so called Oromo meret formerly it is not oromo’s land

    it is ocopuied by invasion this land including addis ababa formerly it was oocupied by other people

    please refer the history ‘oromo migration’

    do not forget to thank EPRDF

  11. Do you know professor doctor sociologist mekuria bulcha, uppsala and mandalen universities, sweden?
    This individual is jawar mohamed’s political and ideological teacher or father.
    Mekuria bulcha has written the article or booklet:
    “genocidal violence in the making of nation and state in ethiopia.”
    This article appeared in 1977, then in 2002, 2005 then continuously on gadaa.com, it is the main reference for olf, extreme oromo nationalists.
    You can find in this article all the fabricated lies, fiction like narations including 5 million oromos killed by abbyssinian colonizers without the slightest concrete evidence.
    All the references are pseudoreferences because some are the writer’s own writings, others are olf’s, some others donot confirm bulcha’s claims and the remaing were written by ignorant, disillusioned, ordinary and wizard people without evidences.
    bulcha supports independent oromia state, he confirms : oromo’s struggle is for oromia is for oromo. To struggle for finfine is to struggle for oromia.
    He also has written freedom for oromo from what for what?
    Seemingly this distorted, evil mineded, narrow nationalist, deluded and amarophobic individual is the master mind for all olf’s extremists and terrorists.

  12. Anonymous: “ኢትዮፒያ ውስጥ የዘር ክልል እና የዘር ፖለቲካ ለምን አስፈለገ?” Because it is there! Those of you who try to deny ethnicity are living in a dream world. And the solution you suggest is simply utopia.
    If you want to solve a problem, denying the existence of some unconfortable problems is calling failure upon oneself. Mixing up some historical events and glossing over some fundamental problems may make your suggested solution look good. For a lasting solution, you should undertake a thorough and all encompassing problem analysis. otherwise, “Allebabsew biyaarsuu,…”
    Oromo land belongs to the Oromos. Those of you who argue otherwise, please answer me to whom Oromo land belongs then? To the Wayanee? To Saudis? If Oromoland does not belong to the Oromo, by extension, land in Ethiopia doesnot belong to anyone. So the Wayanee can do as it will. Or the Kenyans or Sudanese can claim it. Because you have Oromo-phobia, you do not think of the consequences of you own arguments!

  13. ኢህአዴግን እግዚአብሄር ይይለት እንጅ ሰው በፈለገው መንገድ ቢተዳደር (በነጻነት)፣ ምንም ችግር አልነበረውም።
    ለምሳሌ በትክክለኛ መንገድ ፌዴራሊዝምን ተግባራዊ ቢያደርግ ኖሮ፣ ህጎችም በግልጽ ዉይይት ከፓርቲ ውክልና ነጻ በሆነ ማለቴ ነው፤ ህዝቡ ራሱ የትኛው ነው አብረን እንድንኖር ጥሩ ሊሆነን የሚችለው ብሎ በቀናነት እንዲወያይ ቢደረግ ኖሮ፤ ጊዜም ሊወስድ ቢችልም ሩብ ምዕተ ዓመት ያህል ጊዜ አይወስድም ነበር ለህዝቡ ቢተውለት ኖሮ።
    ነገር ግን ለወሬ ማዳመቂያ ተጠቀመበት እንጅ ተግባር ላይ አላዋለውም። አንድ ነገር ተሞክሮ ካልሰራ የግድ በዚያ መቀጠል ያለበት አይመስለኝም፤ መሞከር ግን አለበት።
    አሁንም እውን ኢህአዴግ ስለ ኢትዮጵያ የሚያስብ ከሆነ፤ ከርሱ ሌላ ብዙ ለአገራቸው ቀናዒ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በሁሉም ቦታ አሉና፣ ሰከን ብሎ ለማዳመጥ ቢሞክር የተሻለ ነው እላለሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*