መሲ የባሎን ዶር አሸናፊ ሆነ :: የፊፋ የ2015 የዓለም ምርጥ 11 ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ይፋ ሆኑ
መሲ የባሎን ዶር አሸናፊ ሆነ
በስዊዘርላንድ ዙሪክ በተካሄደው የሽልማት ስነስርዓት የፊፋ 2015 የባሎን ዶር የዓለም ምርጥ ተጫዋችነት ክብሩን ማግኘት ችሏል። መሲ ይህን ሽልማት ማግኘት የቻለው ተፎካካሪዎቹን ኔይማርን እና ሮናልዶን በመብለጥ ነበር።

Ethio Addis Sport : ፊፋ በየዓመቱ ምርጥ ብቃት በመጫወታ ቦታቸው ምርጥ ብቃት ማሳየት ችለዋል ያላቸውን 11 ተጫዋቾች በመምረጥ ይፋ እንደሚያደርግ ይታወቃል።
በዚሁ መሰረት ፊፋ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2015 ዓ.ም የፊፋ የዓለም 11 ምርጥ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾችን ይፋ አድርጓል።
ተጫዋቾቹም ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ሉካ ሞድሪች፣ ሊዮኔል ሜሲ፣ አንድሬስ ኢንየስታ፣ ዳኒ አልቬስ፣ ማኑኤል ኑየር፣ ማርሴሎ እና ሰርጂዮ ራሞስ ሆነዋል።
የፊፋ 2015 የዓለም ምርጥ የወንዶች እግር ኳ አሰልጣኝ የባርሴሎናው ልዊስ ኢነሪኬ ሆናል።

ምንጭ፦ የፊፋ ድረገፅ
