ተቃዋሚዎች ራሳቸውን የሚመለከቱበትን መስታዎት ይስበሩት

ተቃዋሚዎች ራሳቸውን የሚመለከቱበትን መስታዎት ይስበሩት ( Jomanex Kassaye )==================================================
ብዙዎች ይሀ አገዛዝ እየገደለን፣ እያሰደደን፣ እያሰረን፣ አካላችንን እያጎደለ፣ እየዘረፈን፣ መብታችንን ነጥቆ በጭለማ እያኖረ የሚገዛን ከጥንካሬው ሳይሆን ከተቃዋሚ ድክመት ነው በሚለው ይስማማሉ፡፡
ከ10 ዓመታት በፊት የነበረው ተቃዋሚ ጩኸቱ የዲፕሎማቶች መንደር ጎልቶ ይሰማ ነበር፣ ዲሲ ሆኖ አዲስ አበባ ላይ ያሸብር ነበር፤ ዛሬ ነገሮች የተገላቢጦሽ ሆነው ሆድ አደር እና ዘረኛ ካድሬዎች ዲሲ ላይ ያስፈራሩ ደህንነቶች እና ጆሮ ጠቢዎች ተቃዋሚዎችን በስደትም ሆነው ያሸማቅቁ ይዘዋል፡፡
ድምጽ ለማሰማት ተጠራርቶ አዳራሽ የማይበቃው የነበረ ዛሬ የተለመዱ ፊቶች ብቻ የሚከሰቱበት ብዙዎችን ያራቀ ሆኗል፡፡
በፖለቲካችን ብዙ የተጎዱ ብዙ ዋጋ የከፈሉ ዛሬ ላይ ሆነው ሲመለከቱት አገር እናተርፋለን በሚል ሕይወታቸው የተመሰቃቀለ፤ ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉ እየከፈሉም ያሉ አሉ ይኖራሉም…
ነገር ግን ተቃውሞን መምራት እኔ ብቻ ባልኩት እኔ ብቻ በምመራው መንገድ ማለት ለአገዛዙ ጥንካሬ ከመሆን ውጪ የፈጠረው ፋይዳ የለም
አገዛዙን የሚቃወም ስንል ይህ በውስጥም በውጭም ያሉትን ይመለከታል
ተቃዋሚዎች ራሳቸውን የሚመለከቱበትን መስታዎት ይስበሩት ከእውነታው ጋር ይጋፈጡ
አንድነትን የሚያክል ፓርቲ አፈር ድሜ መጋጥ የአመራሮች ድክመት ጭምር እንጂ የአገዛዙ ጥንካሬ ብቻ አይደለም፡፡
ትዕግስቱን ሸራፋ በማለት አንድነትን ማስመለስ አገዛዙንም መገርሰስ ወይም ማስገበር አንችልም!
አይደለም ኢትዮጵያን ሌላም አገር ማንቀጥቀጥ የሚችለው የሥደተኛ አቅም ሲባክን ማየት፣ ተሰላችቶም ለስርዓቱ ሲገብር ማየት ስንሰደድ አንድ ሽንፈት ፣ ወጥተን ይሄን ማየት ሁለተኛ ሽንፈት ነው፡፡ (ሂሳችንን እንዋጥ)
እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው፤
አገዛዙ መንግስትነት የሰጠውን አቅም እና ሃብት ተጠቅሞ ዲፕሎማቲክ ጫናውን መቋቋም ችሏል ቆዳውንም አደንድኗል፤
አገዛዙ በአገር ቤት ራሱን የሃብት፣ የሥራ እና የኅልውና ጉዳይ ምንጭ እሱ ብቻ እንዲሆን አድርጎ ዜጎችን እየገዛ ነው፡፡
…
እስከዛሬ የመጣንበትን የት መድረስም እንደምንፈልግም እናውቃለን፤ ከዜሮ መጀመር ቢመስልም የሄድንበትን ቆም ብሎ ማየት፣ እና መገምገም ፣ አዲስ አካሄድ እና ሁሉን ያካተተ አግላይ ያልሆነ አደረጃጀት አስፈላጊ ከሆነም ያለውን የሚያጠናክር ከውስጥም ከውጪ ያስፈልገናል… አሁን!
ትችት የማትቀበሉ፣ ከእኔ ወዲያ ላሳር የምትሉ ለለውጥ ካልተዘጋጃችሁ በሂደት ብቻችሁን አልያም ራሳችሁን ከገደል ማሚቱዎች ጋር ታገኙታላችሁ፡፡ አገዛዙም ባለበት ቀጥሎ ፡፡
ሌላው ወያኔ አለቀለት ዜና ለፕሮፓጋንዳ አልፎ አልፎ ቢጠቅምም ተቃዋሚዎች አገዛዙን ለመገርሰስ ወይም ለማስገበር የድርሻቸውን እንዲወጡ ከማድረግ ይልቅ ቆመው እንደደመራ እስኪወድቅ እንዲጠብቁ አድርጓል፡፡
በዚህ ያተረፈው አገዛዙ ነው፡፡
‹‹እያወቁ አለቁ›› አንሁን

10 Comments on “ተቃዋሚዎች ራሳቸውን የሚመለከቱበትን መስታዎት ይስበሩት”

  1. ቆንጅት ስጦታው፤ ጥሩ ብለሻል ነገርግን የሚሰማ ጆሮ አለወይ ? አሁንማ በውጭ የምናይው ተቃዋሚ ተብየ እራሱን በሌለ ተግባሩ በወሬ ቱማታ ተወጥሮ ወያኔ ሊወድቅ ሁለት ቀን ቀርቶታል፤ ወያኔን እጁን ልንጨብጠው ነው፤ የወያኔን ፓንት የሚያወልቅ መረጃ አለን በማለትየማይጨበጥ የተስፋ ዳቦ እያገመጠን ነው። ወያኔ ደግሞ አገራችንና ሕዝባች ለማጥፋት ወያኔዊ ስልቱን እየለዋወጥ ዝርፊያና ግድያውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
    ሰሞኑን በተፈጥረው ሕዝባዊ አመፅ ምክንያት ወያኔ ፈርቶልና እንደራደረው ብለው መግለጫ የበተኑ ማፈሪያ ተቃዋሚ መሰል ባንዳውችን እየተመለከትን ነው። ታዲያ ለየትኛው ተቃዋሚ ነው ምክር የምትለግሺው።

    ቸር ይግጠመን ለማንኛውም

  2. ወያኔ እኮ በሁለት የብሄር ነውጦች ተሸንፏል ሽንፈቱን በቀይ ሽብር ደመደመው!!

    ይህን ሢያነቡ ጉጅሌዎቹ በንዴት በቴሥታ ላፕቶፓቸውን እንደሚሠብሩ እርግጠኛ ነኝ።

  3. በየስብሰባዎቹ ላይ የተለመዱ ፊቶች ብቻ ሚሳተፉበት ምክንያት እስቲ እንመርምር እንደኔ የተለመዱና ኣንድ ኣይነት ሃሳቦች ብቻ ስለ ሚስተጋቡ ነው ሁለተኛው ደግሞ የኢትዬጵያና ህዝቦቿ እንድነትና ብሄራዊ ጥቅም ሳይሆን የራሳቸውን የግል ጥቅም ብሎም የብሄር እኩልነትን የማይቀበሉ በጥላቻ የታወሩ ስለ ሆኑ ነው ካገሪቷ እና ህዝቦቿ ጥቅም ይልቅ ኢህኣዴግን ተክተው ስልጣን ስለ መያዝ ብቻ ሚያልሙት ታድያ እንዴት ሊሳካላቸው ይችላል?

  4. ኢትዬጵያውያን ጎደሬዎች እኮ የሡዳንን መሬት ወሥደው እያረሡ ነው
    የጅል አባባል ይህ የመለሥ ኑዛዜን እየተገበሩ ያሉት ፖሥተር ሀይለማሪም ኑዛዜያቸውን ከቻሉ በህዝ ተወካዬች ም.ቤት ያቅርቡልን እባኮ።

  5. yasazenal p m haylamaryam yamenageraw ewnte letyopia naw yamesarawe kale weda akababew hedo lamen kenawarew hezbe gare ayewayayem sudan wasanune eygafu gaberawen bateyet eyadabdebu asfaftew maretun kayazu bahuwala weyane zare maretu yasudan new belo badebabaye eyawera new ewnat weyane malet etyopeyaweyn nan ylalu?yelelaw hager mangest yerasu yalhone maret yezo yane naw belo eytawga eyayen naw enante dagmo yamttykubat geza yematal.

  6. Mnilk yemilen agar guadochachen beTere-woyanie gora keña gar begnbar qedemtnet teselfew woyanien bemanqeTeqeT mitagelut jegnochachn bewoyanie sigedelu ena sitaseru sm anbel, Tere-woyanie tglun aqeTaTlen woyanien bemedmses yetaserutn neTa enawTachew, geday woyaniewochn enbeqelachew eyalnew. Lk new, negeru mereb tekezie endemilew aydelem. SlTan mefelegachn Tru neger new woyanie yabelashewn lemastekakel ena mesel Tfatoch endaydegemu lemasweged mesariyachn new slTan meyaz.

  7. Anchi maneshe ina neaw tekawamiwochin
    yemetetechi politica inde anchi beken
    aser 10 gize igerin meskel ayedelem
    bezu wuta wered alew .

  8. ኧረ ተው የኦሮሞ ወንድሞች የትግል አድማሳችሁን ሰፋ አድርጉት ! ! ! ውያኔ ካመጣው የዘር አጥር ውስጥ መውጣትና ትግሉን ሁሉን ያቀፈ ማድረግ በጣም አጣዳፊ ጉዳይ ነው።ወይ ሁሉም ተቃዋሚዎች ሁሉን አቀፍ መፈክር ይዛችሁ ውጡ ወይም ባላችሁበት እርገጡ።25 ዓመት ባለበት ተረገጠ ! ! ! ወያኔ ያጠረውን የዘር ክልል ማፍረስ ነገ ተብሎ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ! ! ! ! The longer this is delayed, the deeper woyane sinks its poisionous fang on us ! ! !

  9. @Dedebu ,
    Thanks for correctly identifying the evil that has stalled the struggle to free Ethiopians from the grip of Woyane. Race, the very sinster evil that helped Woyane to stay in power is ironically used by the same people who claimed they are the victims of racil discrimination.
    the potent cure for racially motivated supression is noting other than unity! Unfortunately our oromoc brothers are heading on the wrong direction.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*