ኢትዮጵያዊው ሙስሊም የፍርሀት ድባቡን አሸንፎ ለአራት ዓመታት በትግል ጎዳና ላይ ፀንቷል! (ድምፃችን ይሰማ)
ኢትዮጵያዊው ሙስሊም የፍርሀት ድባቡን አሸንፎ ለአራት ዓመታት በትግል ጎዳና ላይ ፀንቷል!
ረቡእ ታህሳስ 13/2008
አምባገነን ስርዐቶች የህዝቦችን መብት በማክበር፣ ነፃነታቸውን በመጠበቅ፣ ለጥያቄዎቻቸው ምላሽ፣ለችግሮቻቸው መፍትሄ በመስጠት ህዝብን ከጎናቸው ከማድረግ ይልቅ የፍርሀትን ድባብ በመፍጠር ህዝብ አንገቱን ደፍቶና ተሸማቆ በፍርሀት ታፍኖ እንዲኖር ማድረግን ይመርጣሉ፡፡ ይህ የፍርሀት ድባብን የመፍጠሩ የስነ ልቦና ጦርነት ደግሞ በተቀናጀ እና በተጠና መልኩ የሚሰራ ነው፡፡ ራስን አግዝፎ ማቅረብ፣ በፕሮፓጋንዳ እና በሀሰት ውንጀላ ተቃራኒን ወገንን ማሳጣትና ማጠልሸት፣ ደካማ አድርጎ መሳል እና መከፋፈል፣ ከዚያም ሲያልፍ ጉልበት በመጠቀም ‹‹አልችልም›› የሚል ስሜት እንዲፈጠርበት በማድረግ የጭቆና ቀንበር ተሸክሞ እንዲኖር ያደርጋሉ፡፡ ይህ የሁሉም አምባገነኖች ስልት ነው፡፡ በታሪክ ወደኋላ ተመልሰን የአምባገነኖችን አኳኋን ብንቃኘው የስልት እንጂ የይዘት ለውጥ አናገኝበትም፡፡
በቁርዐን በተደጋጋሚ የተወሳው አምባገነኑ ፊርዐውንም የእስራዔልን ልጆች በዚሁ መልኩ የፍርሀት ድባብ ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ ችሎ ነበር፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የእስራዔል ልጆችን ነፃ ለማውጣት ሙሳን ሲልክ ህዝቡ የጭቆናን ቀንበር ተሸክሞ መኖርን ተላምዶት ነበር፡፡ ነብዩላህ ሙሳ (ዐ.ሰ) ይህን የፍርሀት ድባብ በማፈራረስ አምባገነኑን ፊርዐውን መጋፈጥ ሲጀምሩ ግን የእስራዔል ልጆችም ተብትቦ የያዛቸውን የፍርሀት ድር በጣጥሰው ከጎኑ መሰለፍ ችለዋል፡፡ የስኬት ጉዟቸውም የሚጀምረው ከዚሁ ፍርሀትን አሸንፈው ከጭቆና ተቃራኒ በቆሙበት ቅፅበት ነው፡፡
ግፈኞች ሰዎችን የሚያሰቃዩት አካላቸውን ለመጉዳት ሳይሆን ለሰው ልጅ እጅግ ወሳኝ የሆነውን ተስፋ እና ወኔ በመስበር በፍርሀት እንዲኖር ለማድረግ ነው፡፡ ከፍርሀት የተላቀቁና የነጻነት ስሜትን የተላበሱ ሰዎች ለጨቋኞች ሁሉ ራስ ምታት መሆናቸውን አምባገነኖች ሳይቀር በሚገባ ስለሚያውቁት ህዝቡ ተስፋ እንዲቆርጥ እና ወኔ እንዲያጣ፣ ብሎም በፍርሀት ተሸብቦ እንዲኖር በቃልም ሆነ በጉልበት የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ አምባገነኖች የፈጠሩትን የፍርሀት ድባብ በጣጥሶ ‹‹ጭቆናው ይብቃኝ!›› ማለት የጀመረ ህዝብ የትልቁን ስኬት መስረት የሆነውን የመጀመሪያውን ድል ተጎናፅፏል፡፡ የድል መሰረት የሚገነባው የስነ ልቦና ጦርነቶችን ተቋቁሞ፣የፍርሀትን አጥር በመሻገር ሊሰብሩት የፈለጉትን ወኔ አጎልብቶ፣ ልብን በተስፋ ሞልቶ በጽናት መጓዝ በተጀመረበት ቅፅበት ነው፡፡ በትናንሽ እንቅፋቶች ተደናቅፎ ባለመውደቅ ማስፈራያ፣ ዛቻዎች፣ እስራት፣ ስቃይ እና ግድያ የማይፈታው ህዝብ ይዞት የተነሳውን የመብት ጥያቄ ከዳር ለማድረስ የሚያስችለውን የስነ-ልቦና ስንቅ አሟልቷል፡፡
የኢትዮጵያ ሙስሊምም አምባገነኖች በሀገሪቷ ‹‹የፍርሀት ድባብ አስፍነናል›› በማለት በእምነቱ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት አልፈው ‹‹እኛ የመረጥንልህን አስተሳሰብ ነው መከተል ያለብህ›› ማለት ሲጀመሩ ነበር ጥልቅ የሆነ የዲን ፍቅር በወለደው ወኔ የፍርሀት ድባቡን በጣጥሶ አደባባይ በመውጣት ‹‹ሰብዐዊ መብቴን አክብሩ! ከእምነት ተቋሜ ውስጥም እጃችሁን ሰብስቡ!›› ማለት የጀመረው፡፡ ይህ ታሪካዊ ክስተት እስከተከሰተበት ቅፅበት ድረስ ማንም የኢትዮጵያ ሙስሊምን በዚህ መልኩ የጠበቀው አልነበረም፡፡ የመብት ማስከበር ትግሉም በመንግስት ማስፈራሪያና አፈና ብዙ ከመራመድ እንደሚደናቀፍ መንግስትም ሳይቀር በፅኑ ያምን ነበር፡፡ የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፡፡ ፍርሀትን ከጫንቃው ላይ ያስወገደው ህዝብ ከመንግስት በኩል ድምፁን ለማፈን የደረሱበትን በደሎች ሁሉ ለነገው ረጅም ጉዞው እየደለደለ መሸጋገሪያ ድልድይ አድርጎት ይኸው እዚህ ደርሷል፡፡ ላለፉት አራት ዓመታት ባልቀዘቀዘ ወኔ፣ ባልደበዘዘ ብርታት ሲታገል የነበረውም አምባገነኖች የፈጠሩትን የፍርሀት ደብባ ድል ማድረግ በመቻሉ ነው፡፡
ድል የሚጀምረው ከውስጥ ነው፤ ፍርሀትን ታግሉ ከማሸነፍ! ኢትዮጵያዊው ሙስሊምም የፍርሀት ድባቡን አሸንፎ አራት አመት በትግል ጎዳና ላይ ፀንቷል! መብቱ እስኪከበርም አዋጭ በሆኑ የትግል ስልቶች መታገሉን ይቀጥላል! ያለበት ጎዳና የድል ጎዳና ነው… ከአራት ዓመታት በፊት ፍርሀትን አሸንፎ የጀመረው የድል ጎዳና!!!
ብሄራዊ ጭቆናን አንሽከምም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!
Like ☑ Comment ☑ Share ☑

Tert tert cheap propaganda !
LEGIZEW ALTESAKAM !!
WE WILL FIGHT EXTREMISM TO THE DEATH !!!
abjunjira rabumaegna abshira
አይዟችሁ ወያኔ ይደመሠሣል
ነፃ ሀይማኖት
ነፃ ሀገር
ነፃ አሥተሣሠብ ይኖረናል
ሞት ለትግራዩ ወረበላና ዘራፊ ቡድን ወያኔ!!!
ዘረኝነትና መካፋፋል ከሌባው መሪ ጋር አብሮ ተቀብሯል!!!
Lalefut 40 ametat yefenechachehut yibkal ahun
Yialem hizeb bemulu awkoachehoal .
Ye Jawar Mohammed jelewoch
Jimma yakatelutin betekratian
bezihu website be English
Version indetemeleketu
Gabezeachoalehu .
Merry Christmas. !
Abesha ke seraw werew
yikedemal yaltekenage tigle
Wutetun aytacehutal ayenachew
Ser weyane Video iyanesa abrot sizel menim ayeteretrum be Harramaya university lejochu mastebabel bemaychelubet huneta record
tedergewal.
Pls, pls, everyone read the article written by Noah Muse on aigaforum.Com the name of the article” eger sayatsedu yechama sheta ayakomum” I can’t believe what a nice article it is. If they admitted all the mistakes they are making and make improvements that we’ll be great for everyone. Thank you.
በውነቱ ይሄ ድምጻችን ይሰማ የሚባል የአጭበርባሪ ቡድን በዚህ አምድ ላይ እንዲያናፋ መፈቀዱ እጂግ ይገርማል። ጎብዝ እነዚህ እኮ ናቸው በየቦታዉ ቤተክርስትያን እንዲቃጠል ትዛዝ የሚሰጡት ማንን ለማሞኘት ነው? እንዲሀ ትያትራቸውን የሚያውቅ ሰው ሲገኝ ወያኔ ነው ትግሬ ነው የማይሉት የለም። ከወያኔ መንግስት ጋር እጅና ጉዋንት ሆነዉ ነው እስከዛሬ የስሩት የትግሬን መንግስት ስንቃወም የማይሉን አልነበረም ታዲያ ሁለቱ ጩሉሌዎች ሲናቆሩ ዛሬ በዚህ ወጥቶ በዚህ ገብቶ ይሉናል። አላማቸዉ ኢትዮጵያን እስላማዊ ሀገር ለማድረግ ነዉ ይህ ነገር ብዥ ያለባችሁ ወገኖች የእስላሞች ስብሰባ ሀጂ ናጂብ ጁዋር መሀመድን ጋብዘዉ የተናገረውን መስማት ነው። ጎብዝ ክወያኔ ጋር አንድ ናቸው። በሊቢያ ወገኖቻችንን ያሳርደቱም እነሱ ናችው።፡ሊቢያ እንዴት ሁኖ ነው ኢትጵያዊ ኦርቶዶክስ የሚለየው?።፡ባጠቃላይ የነሱ ድምጽ ቢቻል የሚዳፈን እንጅ መሰማት ያለበት አይደለም።አላማቸውእስላማዊ አለም ለመፍጠር ነው የገንዘብ ችግር የለም ሳውዲ አለላቸዉ።
በአማራውና በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የቀይ ሽብሩን ንፍሮ ያሥቀቀለው ወያኔ መቃብሩ እንደተቆፈረለት ማወቅ ይኖርበታል።