ሕዝብን በፍቅር እንጂ በኃይል ማንበርከክ አይቻልም – ግርማ ካሳ
ሕዝብን በፍቅር እንጂ በኃይል ማንበርከክ አይቻልም – ግርማ ካሳ
ሁልጊዜ እንደምናደረገው ብሄራዊ እርቅን፣ ሰላምን እንሰብካለን። እስከአሁን ሰሚ አላገኘንም። ቢሆንም ለአገርና ለህዝብ ይበጃል የምንለዉን የሰላም ጥሪ እየደጋገምን፣ ሰሚ ኖረም አልኖረም እንጻፋለን። እንናገራለን። የጥበብና የማስተዋል መንፈስ ይለቀቅልን ዘንድ፣ በተለይም ሌላውን ጋኔን የሚሉ ግን ነርሱ ጋኔን የሰፈረባቸው መሪዎች ልቦና እንዲሰጣቸው፣ በኣጠቃላይ አገራችን ወደ ደም መፋሰስና ረብሻ እንዳትሄድም እንጸልያለን። ነገሮች በመክረራቸው ማንም አይጠቀምም፤ ምናልባት እንደ ግብጽና ሻእቢያ ያሉት ካልሆኑ።
አዲስ አድማስ እንደዘገበው ወደ 18 ሚሊዮን ሕዝብ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል። እንደ ህዝብ እንደ ኣገር ትልቅ ችግር ላይ ነው ያለነው። በኦሮሚያና በጎንደር የተነሳው ቀዉስ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ነው የመጣው። ችግሩ ስር የሰደደ እንደሆነ ራሳቸው ስልጣን ላይ ያሉት ያውቁታል። በአሁኑ ጊዜ ለነርሱም ፣ ለሕዝቡ ለሁላችንም የሚያስፈለገው ሰላማና መረጋጋት ነው። “ነገሮች ይስተካከላሉ “ ብሎ ቃል በመግባት ሰላምና መረጋጋት የሚመጣ አይደለም። ይቅርታ ይደረግልኝና አገዛዙ ቃል የሚገባዉን እንኳን እኛ፣ እነ ሪፖርተርም አይምኑትም። ሰላምና መረጋጋት በጠመንጃና በጉልበት የሚመጣም አይደለም። ሰላምና መረጋጋት የሚመጣው መተማመን ባለበት የፖለቲካ መፍትሄ ነው።
በመሆኑም ከዚህ በፊት እንደጻፍኩት ደግሜ እጽፋለሁ። የሕወሃት/ኢሕአዴግ አመራሮች በርጋታ ቁጭ ብለው ይምከሩ። ሕዝቡም ሆነ ማንም ኢትዮጵያዊ እነርሱ ላይ በግለሰብ ደረጃ ጸብ የለውም። ጸቡ በዘረጉት የአፈና ስርዓት ላይ ነው። በቅርቡ በሜዲያ ላይ ይፋ እንዳደረጉት፣ ሥር የሰደደ የመልካም አስተዳደር ችግር አለባቸው። የአምስት ዓመት እቅድ ብለው ያወጡት እንደሚጠበቀው ተግባራዊ አልሆነም። ሌላ የአምስት አመት እቅድ አውጥተዋል። ይሄን አዲስ ፕላን ያለ ህዝብ ተሳትፎ ዉጤት እንደማያመጣም ራሳቸው ደጋግመው ተናግረዋል::
እንግዲህ ሕዝብን ያስቆጣው፣ ራሳቸውም ያመኑበትን የፍትህ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራታይዜሽን ችግር በተጨባጭ ለመፍታት ቁርጠኝነት ማሳየት አለባቸው። የፖለቲካ መፍትሄ መፈለግ አለባቸው። የፖለቲካ መፍትሄ ማለት ደግሞ ህዝብን ከጎን ማሰለፍ መቻል ማለት ነው። በኦሮሚያና በጎንደር የተነሳው ህዝብ ነው። እነርሱ እንደሚሉት ኦነጎች ወይንም ግንቦት ሰባቶች አይደሉም። ይሄንን ሕዝብ ላይ ጦርነት ከማወጅ፣ ሕዝቡን ማዳመጥ ያስፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን ምክሮች እለግሳለሁ፡
1. በጎንደር እና በኦሮሚያ በሕዝቡ ላይ የተሰማራው ጦር ወደ ካምፑ እንዲመለስ ትእዛዝ መሰጠት አለበት
2. የሕሊና እስረኞች በሙሉ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ መፈታት አለባቸው፡
3. ገዢዎች ለብሄራዊ እርቅ ዝግጁ እንደሆኑ በመገልጽ አገር ቤት ካሉ በዋናነት ከሰማያዊ፣ መድረክ፣ ኤዴፓና መኢአድ ጋር፣ እንዲሁም በእሥር ቤት ካሉና በተራ ቁጥር 2 መሰረት ከሚፈቱ እንደ አንዱዋለም አራጌ፣ ሃብታሙ አያሌው ካሉ አንጋፋ የፖለቲክ መሪዎች ጋር በአስቸኳይ በመነጋገር፣ አዲስ ምርጫ መደረግ የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለባቸው። ሕገ መንግስቱ ጠ/ሚኒስትሩ አዲስ ምርጫ መጥራት እንደሚችል ይደነግጋል። ካለኝ መረጃ የጠቀስኳቸው ደርጅቶች ሁሉ ቁጭ ብለው የጋራ መፍትሄ ይገኝ ዘንድ፣ ሰላምና መረጋጋት ይመጣ ዘንድ ለመወያየት ዝግጁ ናቸው። አላስተዋሉትም እንጂ ከማንም በላይ እነዚህ ደርጅቶች ናቸው አገር በማረጋጋቱ አንጻር ሊረዷቸው የሚችሉት።
4. ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ከኢሕአዴግ እና ከተቃዋሚዎች የተወጣጣ የአንድነት መንግስት ወይንም የሽግግር መንግስት መቋቋም አለበት። ይህ መንግስት ዋና አጀንዳው አገሪቷ ተርጋግታ በሰለም እንድትቀጥል ማድረግ ሲሆን፣ መጪው ምርጫ ሰላማዊና ፍትሃዊ የሚሆንበት ሁኔታ ያመቻቻል። የተጀመሩትም የልማት እንቅስቃሴዎችን ያስቀጥላል።
ኢሕአዴጎች ባለፈው ምርጫ 100% አሸንፈናል ብለዋል። ስለዚህ ዳግም ምርጫ ሊያስፈራቸው አይገባም። ለአገር ደህንነትና ሰላም ሲባል ወደዚህ አቋም መምጣት ካልቻልይ በራሳቸው ላይ እባብ እንደመጠምጠም ነው።
የተለያዩ ባለስልጣናት ሜዲያ ላይ እያስወጡ መግለጫ መስጠት መፍትሄ አይደለም። ቶሎ ተነጋግረው ፣ ነገሮች ሳይባባሱ ለአገር፣ ለህዝብ፣ ለትዉልድ የሚጠቅመዉን የብሄራዊ እርቅ አጀንዳ ያስቀድሙ። ህዝብን በፍቅር እንጂ በኃይል ማንበርከከ አይቻልም። ከሕዝብ ጋር ተስማምተው እስካልሄዱ ድረስ፣ ህዝብን እስካላከበሩ የሚሻሻል ነገር አይኖርም። አወድዳደቃችው እጅግ በጣም የከፋ ነው የሚሆነው።
የሕዝብ ጥያቄ ደግሞ፣ አንዳንድ አክራሪዎች እንደሚሉት የዘር ጥያቄ አይደለም። የዴሞክራሲ፣ የሰላም፣ የፍትህ፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ነው። እነርሱም ራሳቸው ቆመንለታል፤ ታግለንለታል የሚሉት ጥያቄ ነው።
ይሄን ስጽፍ አንዳንዶች ግርማ ካሳ በአቋራጭ ስልጣን ፈልጎ ነው የሚሉ ደካሞች ይኖራሉ። በተለይም አፍቃሪ ሕወሃቶች። የምንም የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ማሀበር አባል እንዳልሆንኩ ይታወቅልኝ። በአሜሪካን አገር ቤተሰብ ያለኝ፣ በጣም ጥሩ ኑሮ የምኖር፣ መብቴ ተጠብቆ፣ እነ ኦባማን በነጻነት እየተቸው፣ ያለ ፍርህት፣ ቀና ብዬ የምኖር ሰው ነኝ። የምጽፈው ቢያንስ እኔ በአሜሪካን አገር መጥቼ ያገኙሁት መብት፣ በአገሬ ያለው ወገኔ እንዲያገኝ፣ በሶሪያ ያየነው በኢትዮጵያ እንዳይደገም ነው።

good job.
History has shown us time and time again regimes like the current regime in Ethiopia will not give up power through negotiations. They have to be cornered to even talk with oppositions much less giving up power. The govenment officials themselves indicated on several occasions that some one has to overthrow them just like they overthrew the Degue. Unfortunately, some people have to die to librate the rest.
አቶ ግረማ ካሳ ያቀርቡት ሐሳብ በጣም ጥሩ ነው። እንዳሉት ወያኔ ስምቶ ከተጠቀመበት ነገር ግን መስማት ካልቻለ በሕዝባችን አመፅ ጆሮው ይቆረጣል ከዚህ ጋር በተያያዘ መንገድ ሌላ መዘዝም ማስከተሉ አይቀርም ስለዚህ እርሰወ እየደጋገሙ ማሰማተወን የግድ ያደርገዋል እንደሚያውቁት የውስጥ አዋቂ ምክር በዚህ ወቅት ለወያኔ ያስፈልገዋልና።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
ሞት ለባንዳው ወያኔ !!
አቶ ግርማ ለምንድን ነው ጊዜህን የምታጠፋው ? ? እንዴ ! ! ዝም ብለህ ጊዜ ስላገኘህ ትፅፋለህ ? ? እነዚህ ሰዎች የሰባዊ ተፈጥሮ የላቸውም።ከዚህ በፊት እንደዝሁ ፅፈህ ነግሬህ ነበር፥አዋቂ ሰው አንዳንድ ጊዜ አያውቅም ብየ።ጥሩ ኑሮ የምትኖር ከሆነ እባክህ ሕይወታቸውን ሰውተው ነፃ ሊያወጡን የደም ግብር እየከፈሉ ያሉትን በምትችለው አቅምህ እርዳ።እኔ በምችለው እያድችረግሁ ያለሁት ይኽንን ነው። እነዝህ ሰዎች በደላችው ምድር ከምትችለው በላይ ሆኖዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ እማ ይቅር ብሏቸው ነበርኮ።
http://i1.wp.com/ecadforum.com/Amharic/wp-content/uploads/2015/12/Ethiopian-Border-Affairs-Committee.jpg?resize=300%2C160&adf855
የሰሞኑ ጭገት ያሥነሱት አሉ አንዱ ጀግና
ጠንቋይ
ባለዛር
አጋንት አይ ሚኒስትር
ሰውን መናቅ ይብቃቸው!
የኦሮሞውም ሆነ የዐማራው ሕዝብ ፕሬዚዳቶች ስልጣናቸውን ይልቀቁ መፍትሔው እሱ ብቻ ነው
ሳተናው አሊ
የፈለገ ኢንተለጅንሥ ቢኖር የህዝብ ፍላጎትን ማቆም አይቻልም!!!
ሞት ለወያኔ!!!
********************************************
Ante demo besint yetegzaeh nehe ?
simeh ke komatawochu yimeslal .
Shintam siltan besetut min yiseral
kuchi bilo yal yelele yfetera tarik
mawrat inji min tawkalachueh ?
Ato Girma you are inosent person you did not know these peoples. There agenda will not allow them to implement yor advice.
Any way let us see.
komatawochu ማለት ምን ማለት ነው፡
wanaw neger ethiopiyan yefelege ke 3000shi amet befit yezer tyaki sayanesa kll saynorew andu kandu tedebelalko andun yandu haymanot werso mengst mesrto yenore hzb ager yakakame hzb yeteleyayu tarikoch bealem lay yasmezegebe ager ethiopiya yetebalechw bekeld aydelem zari yhi ye oromo merit bemebal ychohal yhi yeamhara dnber bemebal ychohal wededachum telachum abatochachu yhchin ager lemastebek dar dberan lemasfat kalhone lemeshetm hone ante yezizer slhonk yante ager aydelem kankayin slematnager agerh aydelm blew yetenesubet tarikna yegezubet zemen yelem be 21Naw kfle zemen seltnenal kalachu kankachn be ethiopiya mdr ydabr yale lelilawm mahbereseb yastemr mknyatum ageru yegaranewna yekeli yekeli atbelu yezer lhikanochm zer aschersachu zer bemasdat lezerochachn ager ena neSanet enametalen blachu atalmu yh weyani slewedeke bcha sayhon hak new ahun betera betera yebanda erzraz ye italiyan ashker planun yzo letaliyann kucht eyemeleselet new yegobenana + yemililik zeroch yeshewa ager hzboch kaltefu tgri megzatna menor aychlm ylal ye italiyan fashishisht le hwehat yasrekebew sistem lemn ? abatochachn tarikachewn slemiyawku endenate bezer altekefafelum meseretachewn yawkalu ye hwehatna +ye Oneg wtet meseret yelilew liba siserk ysmamana sikafel ytal wtet new tglu le oromo merit sayhon Nesanet le ethiopiya hzb yhun
ይቀጥላል………….
Yekir yibelacew Yemiserutin
Ayawkum ena
አቶ ግርማ ቢያረገኝ ነገሮችን በቅጡ ሳልረዳ ጊዜ ስላለኝ ብቻ አልጽፍም።የራስህን ጽሁፎች እራስህ አንብብና ተረዳቸው።ኢህአዲግ በምርጫ ብቻ ነው እያልክ ስትሰብክ አልነበረም?የኦሮሞ ወንድሞቻችንን ትግል አቃለህ ስትጽፍ አልነበረም?ሌሎችም አሉ ላስታውስህ ብዬ ነው።
Wetet yelem enj qiTama binor bewetetu eyarask tmegeb neber endetebalew new ye grma hasab. Grma yaqerebew hasab tru new, gn bewoyanie teqebaynetu 10% new. Ye etiopian hzb megdel le woyanie yekurat ena yedesta mnch new, Telat awrien endemegdel new yemiqoTrew. Zuriyaw chelema sihonbet beleqe saat lidemeses Tqit siqerew bcha manabat woyanie ye grman hasab yqebelal. Ya demo leña yemoten woyanie lederdr megabez aymokerm. Masweged new bcheña mrchachn.
Wetet yelem enj qiTama binor bewetetu eyarask tmegeb neber endetebalew new ye grma hasab. Grma yaqerebew hasab tru new, gn bewoyanie teqebaynetu 10% new. Ye etiopian hzb megdel le woyanie yekurat ena yedesta mnch new, Telat awrien endemegdel new yemiqoTrew. Zuriyaw chelema sihonbet baleqe saat lidemeses Tqit siqerew bcha manalbat woyanie ye grman hasab yqebelal. Ya demo leña yemoten woyanie ledrdr megabez aymokerm. Masweged new bcheña mrchachn.