ሰሜን ጎንደር ጭልጋ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች የበርካታ አርሶ አደሮች የደረሱ ምርቶች በእሳት ጋየ።

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን በጭልጋ ወረዳ ዋርካየ እና ሰርጢያ በተባሉት ቀበሌ ገበሬ ማኅበራት ውስጥ እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች የበርካታ አርሶ አደሮች የደረሱ ምርቶች በእሳት ጋይተዋል።
የሕወኃት መንግስት የአማራ ሕዝብን የነፃነት እንቅስቃሴ ለማረቅ ይቻለው ዘንድ ተላላኪወቹ በሆኑ የቅማንት ማኀበረሰብ መሪ ነን በሚሉ ኃይሎችን በማደራጀትና በስውር በማስታጠቅ አብሮ በሰላምና በፍፁም መግባባት የኖሩትን ሁለቱ ማኅበረሰቦች አንዱ በሌላው ላይ ትንኮሳን በማስፈፀም የክልሉን ሰላማዊ የዕለት ኑሮ በማተራመስ ላይ ነው።
ዛሬ ሌሊቱን በሁለቱ የወረዳው ገበሬ መንደሮች ውስጥ የተፈፀመው ታጭደው በተከመሩ የሰብል ምርቶች ላይ በመሆኑ የከፋ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው አርሶ አደሮች በምሬት ገልፀዋል።