የኦሮሞ ወጣቶችን ተቃውሞ በመጠቀም ገዢው መንግስት የኦሮሞን ሕዝብ ከሌላው ሕዝብ ለማጋጨት የሚያደርገውን ሴራ ሕዝቡ በንቃት እንዲመለከት ተጠየቀ
የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች እስከ
ሰው ህይወት ማለፍን ያስተከተለ ተቃውሞ በመካሄድ ላይ መሆኑን ተክትሎ ገዢው መንግስት
የተማሪዎቹን ጥያቄ የሃገር አንድነትን ከመበታተን ጋር በማያያዝ በብሔር ለመከፋፈል
የሚያደርገውን ሴራ ሕዝቡ በንቃት እንዲከታተለው ተጠየቀ::
በተለያዩ የሶሻል ሚዲያዎች ላይ በተለይም የኦሮሞ ሕዝብ ደጋፊና ተቆርቋሪ በመምሰል ሰሞኑን
ተማሪዎቹ እያደረጉ ያሉትን ተቃውሞ በመደግፍ ሌላውን ብሔር የመሳደብ እና የማጥላላት ዘመቻ
መጀመሩን ተከትሎ ይህን የሚያደርጉት መንግስት ያሰማራቸው ካድሬዎች በመሆናቸው ሕዝቡ
በንቃት እንዲከታተለው ተጠይቋል::
ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ እነዚሁ መንግስት ያሰማራቸው
የሶሻል ሚዲያ ካድሬዎች ጥያቄው ወደ ሌላ ብሄር ጥላቻ እንዲሸጋገር በማደረግ ከፍተኛ ሥራ ላይ
እንደተሰማሩ የታወቀ ሲሆን ይህም እንዲደረግ የተወሰነበት ምክንያት የኦሮሞ ተማሪዎች ጥያቄ
የማስተር ፕላን ጥያቄ ሳይሆን የሌላ ብሄረሰብ ጥላቻ እንደሆነ ተደርጎ እንዲወሰድ ነው ተብሏል::
መንግስት የራሱን ካድሬዎች በማሰማራት በኦሮሞ ተወላጆች ስም ሆን ብሎ ሌላውን ብሄረሰብ
በመሳደብ የተማሪዎቹን ጥያቄ ለማፈን የሚያደርገው ጥረት ከዚህ ቀደምም የተሞከረ እንደነበር
ያስታወሱት የፖለቲካ ተንታኞች ባለፈው ዓመት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ የአማራ
ተወላጅ ንብረት የሆነ ቤትን በማቃጠል እነዚሁ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች እንዳቃጠሉት
በማስመሰል ለፕሮፓጋንዳና ለብሔር ግጭት የሚጋብዝ ሴራ ቢጠነሰስም ሕዝቡ የገዢው መንግስት
ሴራ መሆኑን በመረዳት ማክሸፉ ይታወሳል::
በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልሎች ተማሪዎቹ ሰላማዊ ጥያቄ ሲያቀርቡ በመሃላቸው መንግስት
ያሰማራቸው ካድሬዎች ሕዝቡ ጋር በመመሳሰል ሌላውን ብሄር የሚሳደቡ መልዕክቶችን አብረው
እንዲናገሩ በማድረግ ሴራ ላይም የተሰማሩ እንዳሉ የጠቆሙት ተንታኞች ተማሪዎቹ ከእንደዚህ
ያሉ ተኩላዎች መጠቀሚያ ሳይሆኑ በሰላማዊ መንገድ ሌላውን ሳይነኩ ጥያቄያቸውን አጠናክረው
እንዲቀጥሎ የፖለቲካ ተንታኞች ምክራቸውን ይለግሳሉ::
ከኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መስሪያ ቤት በሶሻል ሚድያዎች በተለይም በፌስቡክ በኦሮሞ ተወላጆች
ስም ህዝብን ከሕዝብ የሚያቃቅሩ መልዕክተኞች የተሰማሩ መሆኑን የሚጠቁሙት ምንጮች እነዚህ
ሰዎች የሚያስተላልፏቸውንና ብሄርን ከብሄር ሊያጋጩ የሚችሉ መል ዕክቶችን በንቃት
እንዲከታተሏቸው ተጠይቋል።”
ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com
ወያኔ እርስ በርስ ለማጋጨት የማይፈነቅለዉ ድንጋይ የለም
ኦሮሞ ኦሮሞነቱ ለማስከበር፤አማራ አማራነቱ ለማስከበር፡ በኢቲዮጲያዊነት ማመን አለበት ያሉት የቀድሞዉ ጠቅላይሚኒስቴራችን የተናገሩት ያላመነ አለ እንዴ?
እርሥ በእርሥ ሆናን ግን ወያኔን እናሥወግዳለን ሀገርና ብሄርን ለይተን እንወቅ ይህን የዘረኝነት ፊሽካ የሚነፋት ወያኔዎች ናቸው ዛሬ አላያችሁም እንዴ ፈንጂ ነቅለው መሥኪድ ላይ ሢጥሉ ብዙ አይተናል ብዙ ከሣሽና ምሥክር አሁን ለታየሁ ወላፈን እንኳ ሆኖ ለመቅረብ በዝግጅት ላይ ነው እርሥ በርሡ ተዋልዶ እየኖረ ያለን ህዝብ ወያኔ አይገነጥለውም።
ሞት ለወያኔ
ኢትዬጵያ የሁላችንም ናት አይዞን ይህን ባንዳ ብቻ በርትተን ተባብረን እናሥወግድ የብሄር ማናለብኝነት ረገጣ አገዛዝ ከወያኔ በሃላ ያበቃል።
ወያኔ ሀጠራው ሀቱ !!!
ይህን ታክቲክ በምርጫ 97 ተሞክሮ የነበረ የሌባው መለሥ ዜናዊ እቅድና ትግበራ ነው
ሞት ለወያኔ!!!
Abo egna oromom amaram tigrayim and nan, hulum bewayane tatakam yelam tagoji enji, betiopia tatakam wayanena kadire naw,
memar kalebache yezer lhikanoch memar alebachew eni leoromo hzb new yemtagelew weyanin chaka eyale ewedew neber eyalu tekawami meslew ahunm weyani yametalachewn yezer kll yzew lemenges weym leferej beterachew habt lemesht kalhone yezer poletika sijemerm meseret yelilew bewsht beri welede tarik hzbnnkemeleyayet ena kefaflo kemaschfchef mannetn kemasatat agern kemasatat lila neger yelewm ethiopiya andnat hzbocha and nachew zeru tedebelalko meleyam yelachum yezer lhikanoch weyanin yebanda erzraz lemetal ke ethiopiya gar metarek alebachu le ethiopiyawinetachn entagelalen kalalachu ahunm weyanin edmi endemtchmru edemtarazmu atterateru yezer poletika metfat alebet oromona amhara weym guragi ….behasab poletika mesrat enji endit new tadiya yand ager hzboch yezer poletika fukkr yhi yehala keroch astesaseb new wededachum telachum ethiopiya eko ende ager yekomechw bemililik zemn aydelem tarikan batkebelum alem yawekew new slezih hzboch le bzu shi zemen abrew norewal ynoralum endeye tarikachew ethiopiyan ethiopiya endthon adrgewatl yhi weroN new stl antem wereh new blo endemilh atterater slezi be 21Naw kflezemen zer kotera egzir ykr ybelen amin belu gedayun yebanda erzraz ena ashkerochun yatfaln wegenochachnn egziabhir kegonu yadrgln
oromo ,amara,..all are humanbeing. We should organize to abolish tplf and its sons as soon as possible.
አሉ እንጅ በጓዳማ ቋጥኝ ሲተክሉ ነበር
This is the best time to unite. Against woyane
Andenet hayel new! Tiglachen ketayenet yalew mehon alebet. (there must be robust strugle against woyane!!!) Woyane ena hod ader kadrewochun enaswogedachew…. We need change!!