ወሊሶ አንድ የስምንት አመት ልጅ ጨምሮ ስምንት ሰዎች ተገደሉ:: የለውጥ ጥያቄው ቀጥሏል::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) = በወሊሶ ከተማ ተማሪው ገበሬው እና አጠቃላይ ነዋሪው ለለውጥ ባነሳው ተቃውሞ አንድ የስምንት አመት ልጅን ጨምሮ 8 ሰዎች መገደላቸውን የወሊሶ ነዋሪዎች ተናግረዋል::ከትላንትና ጀምሮ ብወሊሶ በተደረገው ተቃውሞ በከተማው ያለውን አስተዳደር ከማፍረስ ጀምሮ እስከ እስር ቤት ሰብሮ በግፍ የታሰሩ ንጹሃንን እስከማስለቀቅ ድረስ የተሳካ ስራ በሕዝቡ ተሰርቷል::ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን የአጋዚ ወታደሮችን የጫኑ ሰባት ከባድ መኪናዎች ወደ ቦታው ቢያመሩም በህዝቡ በተወሰደው የመንገድ መዝጋት እና የተቃውሞ መበርታት ወደ ከተማው መግባት አልቻሉም::

ይህ የሕዝብ ብሶት የወለደው ተቃውሞ ማንም የፖለቲካ ድርጅት ያልወልደው መሆኑ ሕዝቡ በጋራ እና በአንድነት ቆሞ በማሳየት ሃያልነቱን አስመስክሮበታል::ሕዝቡ ለአምባገነን እንደማይተኛ በተግባር አሳይቷል::በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚያደርሱ መንገዶች መዘጋታቸው የታወቀ ሲሆን እስካሁን አለመከፈታቸው ታውቋል::ተማሪዎችና አርሶ አደሮች ወደ ከተሞች የሚወስዱትን ዋና ዋና መንገዶች በትላልቅ ድንጋዮችና ግንዶች ዘጋግተዋል። የፌደራል ፖሊሶችና የወያኔ አጋዚ ቅልብ ወታደሮች እንደልባቸው ለመንቀሳቀስ ተቸግረዋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

11 Comments on “ወሊሶ አንድ የስምንት አመት ልጅ ጨምሮ ስምንት ሰዎች ተገደሉ:: የለውጥ ጥያቄው ቀጥሏል::”

  1. ወገን ሆይ በአሁኑ ሠአት በፊንፊኔ የኮሚኒቲ ፖሊሥ በሚል ሥልት የቤተሠብን መረጃ እያሠባሠቡ ከመሀላችሁ አንድ የፖሊሥ አባል ምረጡ እያሉ ህዝቡን እያሸበሩ ይገኛሉ።

  2. The above picture is form BURKINAFASO uprising
    don’t trust it’s the Shabian’s slaves who posts
    this fake picture . down with Gim7 long live
    WOYANAY !!!

  3. Brave Amara nationals stood shoulder to shoulder with Oromo protestors on December 10, 2015 in Washington D.C., Minnesota and other States. This is a sign of solidarity that we are NOT divided, but a united force to get rid of Tigre dictatorship- our common enemy.

    All Ethiopians – UNITE!

  4. የራሱን እግር ቆርጦ ጥሎ ከመጣ ሰው ምን ደግ ነገር ጠብቃችሁ ነበር……ጅሎች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*