ኢሕአዴግን ወደ መቃብር ለማውረድ ለትግሉ መቀጣጠል የእያንዳንዳችን ሚና በጽናት ይጠበቅብናል።
ኢሕአዴግን ወደ መቃብር ለማውረድ ለትግሉ መቀጣጠል የእያንዳንዳችን ሚና በጽናት ይጠበቅብናል።
#Ethiopia #EPRDF #EthiopianOppositionparties #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) :- ከሕወሓት/ኢሕአዴግ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የጠበቃችሁ፤ ከሕወሓት/ኢሕአዴግ ሥልጣን መጋራት የፈለጋችሁ፤ ከሕወሓት/ኢሕአዴግ የእምነት፣ የፕሬስና የሃሳብ ነጻነት የጓጓችሁ፤ ‘ከሕወሓት/ኢሕአዴግ ጋር ተስማምቶ መሥራት ይቻላል’ የምትሉ፤ ተስፋ ቁረጡ። እንኳን አብሮ ለመሥራት ለመወዳደር እድል የማይሰጥ ፈሪ ድርጅት መሆኑን በይፋ አረጋግጧል።
ከሕወሓት/ኢሕአዴግ ጋር አንድ ነገር ብቻ ነው የሚቻለው፤ ከሕወሓት/ኢሕአዴግ በታች ሆኖ መሥራት። ጫማ እየላሱ ‘ጌታዬ!’ ማለት። ያንን የሚመርጥ የፖለቲካ ድርጅት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደፈለገ መንቀሳቀስና መሥራት ይችላል። ጥሩ ቢሮ ይሰጠዋል። ግዙፍ ባጀት ይመደብለታል። ዓመታዊ ጉባዔውን ሼራተን መደገስ ይችላል። በየምክንያቱ ቤተመንግሥት መግባት መብቱ ይሆናል። የመገናኛ ብዙሃን ችግር አይገጥመውም። እስር፣ ዛቻና ወከባ ሕልም ሆነው ይቀሩለታል። ‘ባሪያ የተቃዋሚ ድርጅት’ እየተባለም ይወደሳል።በምንም ተአምር አትታለሉ፤ ኢሕአዴግ በምንም ሁኔታ ሥልጣኑን አሳልፎ ለማንም አይሰጥም። ከተለያዩ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የፈለገ ዓይነት ስምምንነት ቢያደርግ፣ ሥልጣኑን ያጋራል ማለት አይደለም። ቁራሽ ሥልጣን ጠብቃችሁ ከሆነ ዳግም ተሞኝታችኋል። በዚህ አጋጣሚ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር በሽብር የታወቀው ሕወሓት ከወደቀ የብአዴን እና ኦሕዴድ በህይወት መኖር ያበቃለታል።
ሕወሓት/ኢሕአዴግ ሃብትና ሥልጣን አያጋራም። ሁሌም የበላይ ሆኖ ሌሎችን መምራትና መቆጣጠር ብቻ ነው የሚፈልገው። ሌሎቹ እሱን እንዲያጅቡት ነው እቅዱ። ለሚቀጥሉት ብዙ ዓመታትም ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ለመታየት የሚያስችለውን እርምጃ ሁሉ ከመውሰድ አይመለስም። ሕወሓት/ኢሕአዴግ ገንዘብ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ዘራፊዎች የሚሰበስበው፣ ከትላልቅ ሃገራት የጸጥታ ድርጅቶች ጋር የሚሰራው፣ ከአለም አቀፍ አሸብር እና ወንጀለኛ ድርጅቶች ጋር በጋራ የሚንቀሳቀሰው ፣ ሰላማዊ ዜጎችን እያፈሰ በአሸባርነት የሚወነጅለው ፣ ገንዘብ እየረጨ በየመንደሩ የራሱን ሚሊዮነር የሚቀፈቅፈውና ሰራዊቱን የሚያንጸው ለሃገር ብሎ አይደለም። ለአንድ ግልጽ ዓላማ ነው፤ ሥልጣኑን ላለማጋራት፤ ሥልጣን አጠገብ ማንንም ላለማድረስ! …..ያ መታመን ያለበት እውነት ነው። ስለዚህ ሕወሓት/ኢሕአደግን ወደ ከርሰ መቃብር ለመክተት በሙሉ ሃይል ተባብሮ በመታገል የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት ማረጋገጥ የእያንዳንዳችን ሃላፊነት እና ድርሻ መሆኑን መገንዘብ ግደታችን ነው። ሕወሓት/ኢሕአደግን ወደ መቃብር ለማውረድ ለትግሉ መቀጣጠል የእያንዳንዳችን ሚና በጽናት ይጠበቅብናል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!! #ምንሊክሳልሳዊ

Arehin bereh laay yemitara
ወያኔ እኮ አልቅሠው ቀብረዋታል በሙት መንፈሥ የሚንገዳገዱትንም ቻይና የቆፈረችላቸው በርካታ ጉድጎድ አሉን እንደ አደረጃጅታቸው ይቀበራሉ።
@ Gellila
ጓዶችህ እንዲህ ይላሉ ወያኔ ሀጠራው!!!
©
“ሕወሓት/ኢሕአደግን ወደ ከርሰ መቃብር ለመክተት በሙሉ ሃይል ተባብሮ በመታገል
የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት ማረጋገጥ የእያንዳንዳችን ሃላፊነት እና ድርሻ መሆኑን መገንዘብ ግደታችን ነው”
የማይካድ ሀቅ!!!
**********************************************************
Le Aheya maan teyit
Yecheresal leinante dula neaw
medanitachueh .
ከፊታችን ገዝፎ የሚታየው ብቸኛ አማራጭም ይኸው ነው ፣ወያኔን ለመጣል በሁለገብ ትግሉ ውስጥ በንቃት መሳተፍ ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም፣ ወያኔን ለመታገልም የግድ በረሃ መግባት ለያስፈልግ ይችላል ሁላችንም በሞያችንና ባለንበት አካባቢ በህቡእ እየተደራጀን ከውስጥ ወያኔን በማስጨነቅ ለውጪው ትግል ድጋፍ መስጠት እንችላለን።
@Gadissa
ኦህዴድ ሢከፋው እንዲህ ይላችሀል ወያኔ ሀጠራው!!!
Woyanee’s ultimate goal: secession by re-drawing the border (taking as much as they want from the Ethiopian side, and port of Assab from Eritrea)
Strategy: loot Ethiopia and build Abay Tigray, create an ever ending hostility between Amhara and Oromo so that they don’t unit, destabilize Eritrea through Afar to claim port of Assab, Rule by absolute might by monopolizing power and wealth, Destroy Amhara’s capacity to revive, pretend to be a “developmental State” to buy time.
destination: hell, as they have never seen it before!
Chelemaw rezeme
You guys are sellout I
Know you. Your master yehie
Hodam banda Birhanu mistun
tillo ye Eritrean shermutochin iyebeda gizewn
yasalefal.