ከአዲስ አበባ የመጡት የኦርቶዶክስ አባቶች የሽምግልና ቃላቸውን ማፍረሳቸው ተገለጸ

የሽምግልና ጉባኤው ላደረገው ጥረት ሊመሰገን ይገባልብጹእ ወቅዱስ አቡነ መልከ ጸዲቅ

ቤተ ክርስቲያኗ ለ4 ተከፍላለችሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ

በህገ መንፈሳዊ መሰረት በፓትርያርክ ላይ ሌላ አይሾምም ከተሾመም ለመጀመሪያው ይጸናልመላከገነት ገዛኸኝ

Ethiopia Zare (ሰኞ የካቲት 19 ቀን 2004 ዓ.ም. February 26, 2012)፦ በህጋዊው እና በብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ በሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስና በአዲስ አበባ ተቀማጭነቱን ያደረገው በአቡነ ጳውሎስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ መሀከል ከሳምንት በላይ የፈጀው በአሜሪካዋ ግዛት አሪዞና ድርድር ለለቀጣይ ውይይት ለሀምሌ የተቀጠረ ቢሆንም የአዲስ አበባ ተደራዳሪዎች የሽምግልና ቃላቸውን ማፍረሳቸው ተዘገበ።