የዓፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር ዓሊ ሴሮ ህወሓትን ኣናትዋን ብሎ ቀልቧን ገፎ ልቧን ኣዝሮ መለሳት።
Amdom Gebreslasie –
ራስዋ የማታደርገውን ነገር ለዓፋር ክልላዊ መንግስት ኣስተዳዳሪ እሷ ኣጋር ብላ የምትጠራው ኣብዴፖ ለዓመታት በሊቀ መንበርነት የመራው ዓሊ ሴሮ ከሊቀ መንበርነቱና ኣስተዳዳሪነቱ ለማንሳት ስትሞክር በኣፍዋ ሽኖባታል።
ጉዳዩ በያዝነው ዓመት ህወሓትና ራሷ ጠፍጥፋ የሰራቻቸው የኢህኣዴግ ኣባል ድርጅቶች ጉባኤዎቻቸው ኣካሂደው ሊቃነ መናብርቶቻቸው “ባለህበት ቀጥል” ብለው እንደጨረሱ የሚታወቅ ነው።
ከሁሉም በላይ በህወሓት ያጋጠመ ክፍፍልና ባለ ኔትወርኩ ኣንጃ ኣሸንፎ ከሃያኛ ወደ ኣንደኛ ተናጥሮ በመምጣት ሊቀመንበር ፣ ሆኖ ቀጥሎም የትግራይ ክልል ኣስተዳዳሪ ሆኖ መቀጠል ኣነጋጋሪ መሆኑ የሚታወቅ ነው።
ህወሓት በቤትዋ ውጥረት ነግሶባት እስካሁን በንትርክ ትገኛለች።
በጉባኤው ታዳሚ ሁኖ የተገኙት ዓፋሮች የህወሓት ኣይረቤ ንትርክ ኣይተው ስቀው፣ ንቀውና ተሰላቀው ተመልሰው ነበር።
የራስዋ ኣሮባ የሰው……… እንደሚባለው ህወሓት እንደለመደችው ዓፋር ክልል ሂዳ “ዓሊ ሴሮ ከድርጅት ሊቀመንበርነትህና ኣስተዳዳሪነትህ ውረድና ምክትልህ ይተካህ” ኣለችው።
ዓሊ ሴሮም “የድርጅት ሊቀ መንበርነት ለምክትሌ ኣሳልፌ የምሰጠው የክልሌ ኣስተዳዳሪነት የማይነካብኝ ከሆነ ብቻ ነው። ኣለበለዚያ የሊቀመንበርና የክልል ኣስተዳዳሪነት ተው የሚል ጥያቄ የሚመጣ ከሆነ ግን ኣልሰማቹም። ይህ ሊቀ መንበርነት ሃላፊነቴ ኣሳልፌ የምሰጠውም ዲሞክራት ስለሆንኩኝና እኔ ከህወሓት መሪዎች የተሻልኩ መሪ ስለሆንኩ ብቻ ነው።”
እውነቱ ነው ዓሊ ሴሮ በእድሜው መሪዎች ሙተው፣ ታመው ስልጣን የለቀቁ እንጂ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የለቀቀ ሰው የለም።
“… በመሰረቱ ህወሓት የራስዋ ክፍፍል(ኣንጃዎች) ሳታስተካክል እኛ ምንም ችግር የሌለን እያለን እጅዋ ኣስገብታ እድትፈተፍት ኣንፈቅድም።…” በማለት ልክዋን ነግሮ ኣባርሯ ታል
በዚህ ምክንያት የዓፋር መስተዳድር ካቢኔ እስካሁን ኣልተዋቀረም።
የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንትም እንዲሁ ወጊድ እያለ የሚያስቸገራቸው ነው እየተባለ ነው።
ዓሊ ሴሮ ግን ወንድ ነው “…ህወሓት የራስዋ ችግር ሳትፈታ ሌሎች ላይ እጆችዋ የምታስገባ ምን በመሆንዋ ነው…” ብሎ ኣሸማቅቆ መለሳት።
እውነቱ ነው ዓሊ ሴሮ የሚመራው ክልል በድርቅ የተጎዳው ህዝቡ ቀለብ ኣቅርቦ ከሞት እየታደገው ነው። የህዝቡ እንስሳትም ሳርና ውሃ ኣቅርቦ የሂወት ኣድን ስራ እየሰራ ይገኛል።
የትግራይዋ ህወሓት በኣንጃዎችዋ መካከል የስልጣን ሽኩቻ እንደቀጠለ ነው።
መስተዳደሩም ድርቁ ለመደበቅ ያለደረበው ብርድ ልብስ፣ ያላጠረው ኣጥር፣ ያለተናገረው የምርት ቁጥር የለም።
እነ ብኣዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴንና ሌሎችም ህወሓት በሌላት ኣቅም እጇ ስታስገባባቸው ልኳ ነግረው ሊመልሷት ይገባል እላለው።
ህወሓት ኣቅም ካላት ህዝቧ በረሃብ እየረገፈ ነውና ትታደገው…!
