ዳኞች አዳማ ስልጠና ላይ ናቸው በሚል ሰበብ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ለጥቅምት 5 ለ38ኛ ጊዜ ተቀጠሩ::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ፍትሕን ከሚደፈጥጡ የወያኔ ባለስልጣናት የሚሰጠውን ውስኔ ለማንበብ የምን ስልጠና ያስፈልጋል የሚል ጥያቄ ያስከተለው የዞን ዘጠን ጦማርያን የዛሬው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ጉዳይ የካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ዳኞች ስልጠና ላይ ናቸው በሚል ሰበብ ጦማርያኑን ማጉላላት ቀጥሏል::ከታሰሩ 531 ቀናትን ያስቆጠሩት ለ37 ጊዜ በወያኔው የፖለቲካ ፍርድ ቤት የሚጉላሉት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ክሳቸው ፖለቲካዊ መሆኑ ከጅምሩ የሚታወቅ ሲሆን በቂ መረጃ ያልቀረበባቸው በመሆኑ ወያኔ አጣብቂኝ ውስጥ ስለከተተው ፍትህን በአደባባይ ገድሎ እየቀበራት ይገኛል::

ጉዳዩ ዳኞች አዳማ ስልጠና ላይ ስለሆኑ መዝገቡ ለጥቅምት 5/2008 ዓ·ም ተቀጥሯል። ይህም ለጦማሪያኑ በማረሚያ ቤት ተነግሯቸዋል።ለዳኞች የሚሰጠው ስልጠና ሃገሪቷን ላለፉት አመታቶች ያሽመደመደው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስልጠና ዜጎች በፍትህ ላይ ያላቸውን እምነት ከባለፈው የበለጠ የሞተውን ደግሞ ይገለዋል ተብሎ ይጠበቃል::በኢትዮጵያ የሞተው ፍትህ የዜጎችን ይመኖር ሕልውና ከማደፍረሱ ሌላ ያለው አገዛ አለመረጋጋቱን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል::የዞን ዘጠኝ ጦማርያም ምንም ማስረጃ ይሁን አጥጋቢ ክስ ሳይቀርብባቸው ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለጹ ብቻ የደነበረው ወያኔ እያንገላታቸው ይገኛል::

Minilik Salsawi's photo.

4 Comments on “ዳኞች አዳማ ስልጠና ላይ ናቸው በሚል ሰበብ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ለጥቅምት 5 ለ38ኛ ጊዜ ተቀጠሩ::”

  1. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    የባለገ ማነው እኔ ወይስ ውድ እናቶቻችንን የሚሰድብ?አስተውል የምትሳደበው ያንተንም እናት ነው:ኢትዮጵያዊ እናቶችን ነው ብቻ ዌቡን በአልባሌ ስድብ አትበክለው:ስድብህን ሌላ በማይነካ,ቀይረው

  2. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    ወንድሜ ሀሳብን በሀሳብ እንጂ በስድብ አታድርገው:መሳደቡ ላንተ የእግር እሳት ይሆንብሀል:”መፅሀፉም ተሳዳቢ አትሁን” ይላል!

  3. እየተሳደበ ያለው ማን ነው ? እኔ ውይንስ repetitive nonsense እየለቀለለቀ ይኽነን site እያቆሸሸ ያለው ነው?
    For all i know this ግTም was recited back in the 70s in the five doors kasanchis azmari bet.Now this sick man is using ይኽነን ግጥም to pollute this site.Well I clearly understand your idea.I apologize to you decent fellow Ethiopians,but the only way a shitty person can understand is only when you communicate with him the same shitty way he is communicating.Now having said that this looser is a burger eating pest who knows nothing but post repetitive nonuse just to annoy us and i promise i am not going to take his shit just quietly.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*