ማነው? አንዷለምንና አጋሮቹንየሚገርፋቸው?የሚያስገርፋቸው? ወያኔ ወይስ እኛ?

የጐንቻው

ገሃዱ እውነታ አንዷለምንና አጋሮቹን አሳልፈን ለግርፋት፤ ለውርደት፤ ለስቃይ፤ ‘ለቁም-ሞት’ የዳረግናቸው በለየለት ጠላት (ወያኔ) እናሳብ እንጅ፤ በደለኞች እኛ ቁጥራችን ያስደመመን ብዛታችን እንደ ሃይቅ ያሰጠመን፤ ግነነታችን ያንቀጠቀጠን፤ አንድነታችን ያናወጠን፤‘ [እኛ ከሰማንያ ሚሊዮን በላይ የምንሆን ኢትዮጵያውያን]፤ ነን።