በአዋሳ ገብርኤል ምእመናን በድንጋይ ተፈነከቱ

  • ፖሊስ ሁከተኞቹን ያሬድ አደመን እና ትዝታው ሳሙኤልን ጨምሮ 12 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለ
  • ምእመናን የክልሉ መንግሥት ሐላፊዎች ችግሩን ለመፍታት ባላቸው ሐቀኝነት ላይ የተፈጠረባቸው ጥርጣሬ እየተጠናከረ ነው
  • ‹‹ፓትርያኩ ውሸታም ናቸው፤ ጉባኤያችንን ከመስቀል አደባባይ ወደ ገብርኤል አመጡብን፤ የማንፈልጋቸውን መምህራን አስመደቡብን፤ የጳጳሱን ግቢ በር እናሽጋለን፤ መኪና ወደ ገዳሙ እንዳይገባ እናግዳለን፤ የተላኩብንን መምህራን እስክንመለስ እና የታሰሩብንን እስክናስፈታ ድረስ ጸልዩልን፡፡›› (ዛሬ ጠዋት የእነ ያሬድ አደመ መናጆዎች በደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም ያሰሙት ክስ እና ፉከራ)
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 29/2011፤ ጥር 21/2003 ዓ.ም)፦ ንት ማምሻውን በሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ማሠሪያ ገቢ ለማሰባሰብ በተዘጋጀ ጉባኤ ላይ የሀገረ ስብከቱን ፈቃድ ጥሶ ዐውደ ምሕረቱን በኀይል ለመቆጣጠር በተደረገ ሙከራ ሳቢያ በተቀሰቀሰ ብጥብጥ ምእመናን በድንጋይ የተፈነከቱ ሲሆን ለብጥብጡ መንሥኤ ናቸው የተባሉት የሐዋሳ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ አባ ናትናኤል፣ ያሬድ አደመን፣ ዲያቆን ትዝታው ሳሙኤልን ጨምሮ 12 ሁከት ፈጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

(Read More  . . . . .)