በሚሌ ወረዳ በድርቅ ምክንያት በረሀብ የተጎዱ ወገኖቻችን በስቃይ ላይ ይገኛሉ::

Minilik Salsawi – በአፋር ክልል እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልል የደረሰው ድርቅ ተስፋፍቶ የቀጠለ ሲሆን እነዚሕ በምስሉ የምትመለከቷቸው በሚሌ ወረዳ በድርቅ ምክንያት አንስሳቶቻቸዉ አልቀው የሚሌ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት እና የወረዳዉ አደጋ መከላከል የወያኔ ጁንታ አገዛዝን ትእዛዝ ሳይጠብቅ ከየጫካዉ የሠበሰባቸዉ በረሀብ የተጎዱ ወገኖቻችን ናቸዉ።

በመሆኑም አሁን በሚሌ ጤና ጣቢያ ጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ ሲሆን እየተደረገላቸዉ ያለዉ ድጋፍ እጅግ አናሣ ነዉ የወያኔ መንግስት ፊቱን እስካሁን ወደ ተጎዱ ወገኖች ለማዞር ፍቃደኛ ሳይሆን በመቅረት ያለውን ከባድ የድርቅ አደጋ በማስተባበል ላይ ይገኛል::ወገኖች እያለቁ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ሲያስፈሊግ በጥናት ላይ ነን በማለት በሕዝብ እልቂት እያላገጠ ይገኛል::በአሁን ወቅት ወያኔ ለመደበቅ የሚሞክረው ድርቅ ከ1977 ከደረሰው በላይ አስከፊ ነው ሲሉ አከባቢውን ያዩ ኢትዮጵያውያን እየመሰከሩ ነው::

Minilik Salsawi's photo.