ለወገን እንደ (መንግስት?) ቀድሞ መድረስ ሲገባ ዜጎችንና ችግሮችን መካድ ሕሊናዊ ድክመትን ያሳያል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)
===Thousands of people in need of emergency food assistance is rising ===
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በሃገራችን በአማራ ክልል በወሎ እንዲሁም በሐረር አከባቢ እና የአፋር አከባቢዎች ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ የደረሰውን የተፈጥሮ መዛባት/የዝናብ እጥረት የፈጠረውን ድርቅ በተመለከተ በማህበራዊ ድህረገጾች እና በኢትዮጵያውያን የመገናኛ አውታሮች በተለያየ መልኩ ዘገባዎች ቭድዮዎች እና ምስሎች (ለበለጠ መረጃ Mereja) በይፋ ተለቀው አለምን እያዳረሱ በሚገኙበት በዚህ ወቅት ላይ ድርቁን የፈጠረው የተፈጥሮ ሂደት/የዝናብ እጥረት መሆኑ እየታወቀ በስልጣን ላይ የተቀመጠው የወያኔ ጁንታ በራስ አለመተማመኑን የሚያሳዩ የተለመዱ ሃሰቶችን እየነዛ ይገኛል::
ይህን የዝናብ እጥረት የፈጠረውን ድርቅ ያስከተለው ችግር ዜጎች በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ባሉበት እና እርዳታ በሚያስፈልጋቸው በዚህ አስከፊ ወቅት ላይ ለዜጎች ሕመም እና ችግር መድረስ የሚገባው መንግስት(ካለ?)ሆኖ እያለ በሃገራችን በስልጣን ላይ ያለው አሸባሪ መንግስት ግን ይህንን የተፈጥሮ አደጋ ለመደበቅ በመውተርተር የድርቅ አደጋና የምግብ እጥረት ስጋት የለም በማለት በሃሰት ለሚዲያዎች መናገሩ ምን ያህል በራሳቸው የማይተማመኑ ባለስልጣናት ሕዝብን እንመራለን በሚል የሃሰት ዲስኩር ወንበራቸው ላይ እንደተኮፈሱ ሲያሳይ በሌላ በኩል ደግሞ በአየር ፀባይ ለውጥ (ኤሊኖ)የፈጠረው የተፈጥሮ መዛባት መሆኑን ሊነግሩን ሲሹ ለምን ይህ ከታወቀ ባየር ትንበያ እና ጥናት ሂደት ቅድመ ጥንቃቄ አልተወሰደም ተብለው ሲጠየቁ በድጋሚ አደባባይ ያገጠጠው ገበናቸውን ይዘው ሚስታቸው አጭር ቀሚስ ስር ለመደበቅ ሲሽቀዳደሙ ይታያሉ::
ሕዝብን ማስተዳደር ማለት ቅድሚያ ለሕዝብ መስጠት መሆኑ በቀላሉ የሚታወቅ ጉዳይ ነው::በየቀኑ በአፋር ክልል ከ100 በላይ እየሞቱ አርብቶ አደሩን ለከብቶችህ እንቅስቃሴ በደረሰኝ ሊቀረጥብህ ነው እዚህ ክፈል እዚያ ተንገላታ አልመረጥከኝም ወዘተ ከማለት ቀድሞ ለሕዝብ መስራት ምን እንደሆነ ከሌሎች ግንዛቤ መቅሰም አሊያም ስልጣኑን ለሚያስተዳድር ስርአት ላለው ዜጋ አስረክቦ መውረድ ግድ የሚልበት ውቅት ላይ መሆኑን ልታውቁ ይገባል::ባለፉት ሁለት ወራት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተከሰተው የዝናብ እጥረት ድርቅ እንደፈጠረ እየታወቀ የወያኔ ግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ፤ የዝናብ እጥረት ቢኖርም የድርቅ አደጋና የምግብ እጥረት ስጋት የለም ማለት ያሳፍራል፡፡ከሌሎች ክልሎች በተለየ በአፋር ክልል ግን ሁኔታው ተባብሷል፡፡ በየቀኑ እስከ 100 የሚደርሱ ከብቶች በመኖና በውሃ እጥረት እየሞቱ ሲሆን የአፋር ክልልን አቋርጠው ወደ ጅቡቲ ወደብ ከሚጓዙ ሹፌሮች በመንገድ ዳርና ዳር በርካታ በጎችና ፍየሎች ሞተው እንደሚታዩ መስክረዋል::
የጉዳዩ አሳሳቢነት የጀመረው ክሰኔ 2006 ከአመት በፊት መሆኑ ሲታወቅ ይህ ሪፖርት የቀረበለት የወያኔው ጁንታ ግን ፈጣን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የራሱን የፖለቲካ ፍጆታ ሲያሳድድ የሕዝብን ጥያቄ እና የአከባቢውን ሪፖርት ችላ በማለት በሃሰት ላይ የተመሰረተ መረጃ በመስጠት የህዝብን ሕልውና ለአደጋ አጋልጦ ሰጥቷል::የተፈጥሮ አደጋ ፈታኝ መሆኑን ያመኑት የወያኔ ጁንታ አሾክሻኪዎች እስካሁን ድረስ በፍጹም ሊቆጣጠሩት ባለመቻላቸው በየአከባቢው እንሰሳት እየሞቱ ዜጎች ከቀያቸው እየተሰደዱ ይገኛሉ::መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ብልሃቶች እና ዘዴዎች ከቅድመ ጥንቃቄ ጀምሮ እስከ እርዳታ ማሰባሰብ የመሳሰሉት ስራዎች መተግበር ሲገባቸው ለወገን እንደ መንግስት ቀድሞ መድረስ ሲገባ ዜጎችንና የደረሱ ችግሮችን መካድ ሕሊናዊ ድክመትን ያሳያል::የህዝብን ችግር ለመደበቅ መሞከር እና አቅጣጫ ለማስቀየር መሮጥ የወያኔ ባለስልጣናት በራሳቸው እንደማይተማመኑ እና በሃሰት እንደተሞሉ ያሳያል::በራሱ የሚተማመን መንግስት ለዜጎቹ ከቅድሚያ ጥንቃቄ ጀምሮ እስከ መስዋእትነት የሚደርሱ ተግባራትን ይከውናል::ሕሊናዊ ድክመት የተጠናወታቸው በራስ መተማመን የከዳቸው ወያኔዎች ስልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክቡ ይጠበቅባቸዋል:: #ምንሊክሳልሳዊ
