የአሜሪካው አለም አቀፍ የሃይማኖት ኮሚሽን በሙስሊሙ ማህበረሰብ ኮሚቴዎች ላይ መፈረዱን በማወገዝ መግለጫ አወጣ
የአሜሪካው አለም አቀፍ የሃይማኖት ኮሚሽን በሙስሊሙ ማህበረሰብ ኮሚቴዎች ላይ መፈረዱን በማወገዝ መግለጫ አወጣ
ቢቢኤን፤-ሀምሌ 30/2007
የአሜሪካ አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን የ18 የሙስሊሙ ኮሚቴ ጥፋተኛ ተብሎ መፈረዱን በጽኑ መቃወሙን አስታውቀ፡፡ አወዛጋቢው በሆነው የጸረ-ሽብር ህጉ መከሰሳቸው ያወሳው የሃይማኖት ኮሚሽኑ ጥፋተኛ የተባሉት ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት አስባችሃል በመባል መከሰሳቸውን ጠቅሶ ክሱ ና ጥፋተኛ መባለቸው ትክክል አለመሆኑን በማስገንዘብ በእቸኳይ እንዲፈቱ አሳስብዋል፡፡
”እነዚህ ግለሰቦች በሰላማዊ መንገድ ለሃይማኖት ነጻነት የሚታገሉ ነበር” ያሉት የአሜሪካው አለም አቀፍ የሃይማኖት ኮሚሽን ሊቀንበር የሆኑት ዶክተር ሮበርት ጆርጅ ናቸው፡፡
ችሎቱ የሚያመልከተው የኢትዪጲያ መንግስት በሰላማዊ መንገድ ቅሬታ የሚያሰሙበትን ግሰቦች ወይም ቡድኖች ዝም ለማሰኘት እንደሚጠቀመበት ነው ዶከተር ሮበርት ገልጽዋል፡፡
በሃምሌ 27 የተፈረደባቸው 18 አራቱ 22 አመታት መፈረዳቸውን ገልጾ 18 ፤15፤ 7 አመታት የተፈረደባቸው እንዳሉ ጠቅሶ ኮሚሽኑ ከነዚህ መካከል የሙስሊሙ ኮሚቴ አባላት እንዳሉበት ገልጽዋል፡፡ ኮሚቴዎቹ የህዝብን ጥያቄ ይዘው ከመንግስት ጋር ሲወያይ መቆየታቸውን በሁላም መታሰራቸውን አውስትዋል፡፡ ከኮሚቴዎቹ በተጨማሪ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ሌሎችም እንዳሉበት ኮሚሽኑ በመግለጫው ጠቅስዋል፡፡
የአሜሪካው አለም አቀፍ የሃይማኖት ኮሚሽን የአሜሪካ መንግስት በግልጽ ይህን ኢ-ፍትሃዊ ፍርድ ውሳኔ በግልጽ በአደባባይ እንዲያወግዝ ጠይቅዋል፡፡ መግለጫው በውስጡ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣም በስፋት ጠቅስዋል፡፡ ፖሊስ በንጹኃኖች ላይ አስለቃሽ ጋዝ ና ጥይት ተኩሰው እንደነበር አጋልጥዋል፡፡
አለም አቀፍ የሃይማኖት ኮሚሽኑ ኢትዪጲያ በሄደበት ጊዜ ከተከሳሾቹ ጠበቆቹ ጋር መገናኘታቸውን እና ጠበቆቹ በታሳሪዎቹ ላይ ቶርቸር መፈጸሙን እና የደረሰውን ነገር መጥቀሳቸውን ገልጽዋል፡፡
በያዝነው አመት የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጠቅላይ ሚኒስት ሃይለማርያም ደሳለኝ የታሳሪዎቹን አያያዝና የተፈጸመውን ቶርቸር በማስመልከት ማጣራት እንዲደረግ ጠይቆ እንደነበር ኮሚሽኑ በመግለጫው ገልጽዋል፡፡ ቢቢኤን የኮሚሽኑን መግለጫ አስመልክቶ በአርብ ፕሮግራማችን የምናቀርብ ይሆንና ኮሚሽኑ ያወጣው መግለጫ ሊንክ ከስር ተቀምጥዋል፡፡