ወያኔ በእርዳታ የሚያገኘውን ገንዘብ መመዝበሩን መቀጠሉ ተጋለጠ

ሀፍረት የሌላቸው የወያኔ ዘረኛ ገዢዎች ለሰብአዊ እርዳታ የሚገባውን ከፍተኝ መጠን ያለውን ገንዘብ ንጹሀንን ላማስፈራሪያ፡ ለማሰቃያና ለመግደያ ብሎም ኪሳቸውን ለማዳለቢያ እየተተቀሙበት መሆኑን ሰሞኑን ቤን ራውለንስ የተባሉ የሰብአዊ መብት ታጋይ ለአየር ላንድ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ መግለጻቸውን ዘአይሪሽ ታይምስ የተባለው ጋዜጣ ዘግቡዋል።

ከዚህ ቀደም በሰር ቦብ ጊልዶፍ አስተባባሪነት በከፋ የረሃብ ችግር ለተጠቃው የሰሜኑ የሀገሪቱ ህዝብ ለመርዳት የተዋጣውን ገንዘብ ከተራበው ወገን አፍ በመቀማት የመሳሪያና የነሱ የተንደላቀቀ ኑሮ መምሪያ እንዳደረጉት ከበቂ በላይ በሆነ መረጃ ተደግፎ መቅረቡና በአለም ላይ መነጋገርያ ሆኖ መሰንበቱ የሚታወስ ነው። ይሁን እንጂ በውሸታቸው የሚታወቁት ግፈኞች በዛ አልበቃ ብሎአቸው አሁንም ከተላያዩ የተራድኦ ድርጅቶችና መንግስታት በሰብአዊ እርዳታ ስም የሚገኛውን በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ችግረኞች እንዲደርሳቸው ከማረግ ይልቅ ራሳቸውና ጥቂት ደጋፊዎቻቸው እንደፈለጉ የሚንደላቀቁበት በተረፈው ደግሞ ለተቀረው ህዝብ የተለያዩ የፖለቲካ ደጋፊዎች ናችሁ በሚል የሚሳደዱበት የሚታሰሩበት የሚገደሉበት መሆኑን እኝሁ ግለሰብ ጠቅሰዋል።

አቶ ሮውለንስ አያይዘውም ሀገሪቱ በአለም ከፍተኛ እርዳታ ተቀባይ አገሮች ውስጥ አንዱዋ መሆኑዋንና በአመት ከሁለት ቢሊዮን ኢውሮ በላይ ገንዘብ እንደምታገኘ ገልጸው በተቃራኒው በሀገሪቱ ግን ከፍተኛ ረሃብ የመብት ረገጣና ግድያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መምጣቱ የሚያሳዝን መሆኑን ገልጸዋል። ጉዳዩንም ሁሉም የተራድኦ ድርጅቶችና መንግስታት ከበቂ በላይ መረጃ በተደገፈ መልኩ እንደሚኡያውቁት ተናግረዋል።

ጉዳዩን ሊያስተባብሉ ያልቻሉት የአየርላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶት በአውሮፓ ህብረት በሚቁዋቁዋም አለም አቀፍ ቡድን ሊጠና ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል።