የወያኔው ዘረኛ አገዛዝ ዘር በማጥፋት ተግባር ላይ ያነጣጠረ ወንጀል መፈጸሙን ቀጥሉአል
በአማራ ክልል የደባርቅ ወረዳ ነዋሪዎች ለተላላፊ በሽታዎች ማጥፊያ ተብሎ መድሃኒት በግዴታ እንደተሰጣቸውና ይህም መድሃኒት ላልታወቀ ሌላ በሽታ እየዳረጋቸው መሆኑን መናገራቸውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ዘገበ::
ኢሳት በዘገባው የደባርቅ ነዋሪዎች እንደገለጹት የወረዳ የጤና ባለሙያዎች በየቀበሌዎቹ እየዞሩ የሰጡት መድሃኒት ነፍሰ ጡሮችን እያስወረደና ቀደም ብሎ የተለያዩ በሽታዎች ያሉባቸውን ሰዎች ላልታወቀ ሌላ በሽታ እንዲጋለጡ ያደረጋቸው መሆኑን ገልጹአል::
ለደባርቅ ነዋሪዎች መድሃኒቱ የተሰጠው ባካባቢው ያሉ ተላላፊ በሽታዎችን በማስወገድ ለጉብኝት የሚሄዱ ቱሪስቶችን ጤንነት ለመጠበቅ ነው መባሉን ኢሳት የዘገበ ሲሆን፣ ፣ የአካባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት ግን በዚህ ምንነቱ ያልታወቀ መድሃኒት የሞቱ ሰዎች ሳይኖሩ እንደማይቀሩ አክሎ ገልጹአል::
ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በዘር ላይ ያነጣጠር ጅምላ ግድያን ቀደም ብሎ ወደ ስልጣን ወምበር ከተቆናጠጠ ጀምሮ ሲፈጽም እንደቆየ የተለያዩ የመረጃ ምንጮች መዘገባቸው አይዘነጋም::