አውስትራሊያ ለሀገሯ ዜጎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሰጠች

ከአውስትራሊያ በተሰማው ሰበር ዜና እንደተገለጸው በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የአፍሪቃ ህብረት ስብሰባ ተከትሎ ሽብርተኞች በተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ ክፍሎች ፍንዳታዎች ሊያደርሱ እንደሚችሉ አውስትራሊያ ማስጠንቀቁዋ ታወቀ::

የአውስትራሊያ የውጪ ጉዳዮችና ንግድ ዲፓርትመንት ባወጣው በዚሁ መግለጫው አውስትራሊያዊያን ወደ ምስራቅ አፍሪቃ በተለይም ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲያቆሙ ወይንም እንዲያስቡበት አስጠንቅቁአል::

እንደ ዲፓርትመንቱ መግለጫ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የአፍሪቃ ህብረት ጉባኤ ተከትሎ ባልተገለጹ የአዲስ አበባ ክልሎች ሽብርተኞች ጥቃት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ታማኝ የሆነ መረጃ እንደደረሰው አስታውቁአል:: አያይዞም ወደ ኢትዮጵያ ለመጉአዝ ሃሳብ ያላቸው አውስትራሊያዊያን ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሩአል:;

ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ከኒውዮርክ ፍንዳታ አስቀድሞ የአልኢትሃድ የሽብር ጥቃት ዒላማ የነበረች ሲሆን፤በተለይም ከኒውዮርክ በፊት አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና ሐረር እንዲሁም በ አብዱል መጂድ ሁሴን እና በፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ላይ ከዛም በግዮን፣ በዋቢ ሸበሌ፣ በትግራይ ሆቴል እና በምድር ባቡር ላይ የአልኢትሃድ አሸባሪዎች ጥቃት ዒላማ እንደነበረች ይታወቃል::

ኢትዮጵያ በተለይም በሶማሊያ ላይ ያደረገቺውን ወረራ ተከትሎ ከሽብርተኞች ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል ሲዘገብ መቆየቱና በኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም የወያኔው አምባገነን አገዛዝ በሶማሊያ ላይ የወሰደውን ርምጃ ሲቃወሙ መቆየታቸው አይዘነጋም::