የቱኒዚያ ሕዝባዊ አመፅ ማእበል ሌሎች የአፍሪቃ ሃገራትን እያናወጠ መሆኑ ታወቀ

በቅርብ ጊዜ ቱኒዚያ ዉስጥ ሕዝባዊ አመፅ ከተቀሰቀሰና አመጹም ለቤን አሊ ተገቢዉን ዋጋ ከሰጠ በሁዋላ ተመሳሳይ አመጾች በግብጽ፣ አልጄሪያ፣ የመን ፣ እንዲሁም በዮርዳኖስ መቀጣጠላቸውን በርካታ የዜና አውታሮች በመግለጽ ላይ ይገኛሉ::

ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በግብጽ የተለያዩ ከተማዎች ህዝባዊ አመጽ ተቀስቅሶ አራት ሲቪሎች መሞታቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መቁሰላቸው ታውቁአል፣ ፣ በተመሳሳይ መልኩ 18 የሚሆኑ የግብጽ ወታደሮች ላይ ጉዳት መድረሱ በተለያዩ የዜና አውታሮች ተዘግቦአል፣ ፣ ግብጻዊያን ያደረጉትን የተቃውሞ ሰልፍ ለመበተን የግብጽ ፖሊሶች አስለቃሽ ጪስና ውሃ መጠቀማቸውን የዜና አውታሮቹ አክለው ገልጸዋል:;

ሆስኒ ሙባረክ በቅርቡ በአገራቸው ተደርጎ በነበረው ምርጫ እንደመለስ ዜናዊ 99፡ 6% የመራጭ ድምጽ አገኘሁ አይበሉ እንጂ በከፍተኛ የድምጽ ልዩነት ተቃዋሚዎቻቸውን እንዳሸነፉ ማስነገራቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ህዝባዊ አመጽ እያንቀጠቀጣቸው ባሉት የስሜን አፍሪካ እና የመካከለኛ ምስራቅ አገሮች አንዳቸውም የመለስ ዜናዊ አይነት በዘር ላይ የተመሠረተ የአፓራታይድ አገዛዝ በአገራቸው እንዳልዘረጉ ይታወቃል።

በተመሳሳይ መልኩ አል-ጄሪያዎችም እንደ ቱኒዚያዎች በአደባባይ ሠልፍ ተቃዉሟቸዉን እንደቀጠሉ የዜና አውታሮች እየገለጹ ነው። በአልጀሪያ ሠልፍ-ተቃዉሞ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በሰልፈኛዉና በፀጥታ አስከባሪዎች መካካል በተደረገ ግጭት አርባ-ሁለት ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል። አል-ጄሪያን ለበርካታ አመታት የበጠበጠዉን የርስ በርስ ግጭት፥ ቁርቁስ ያስወገዱ፥ የኢትዮ-ኤርትራን ጨምሮ አፍሪቃ ሐገራትን ጠብ ፥ዉዝግብ ለማግረብ የጣሩ እየተባሉ ሲደነቁ፥ በምዕራቦች ሲወደሱ የነበሩት ፕሬዝዳት ቡተፈሊቃን ህዝባቸው በቁን በቃንዎት እያላቸዉ መሆኑም ታውቁአል።

በሌላም በኩል ይሄው በቱኒዚያ የተቀጣጠለዉ የህዝብ አመጽ በዮርዳኖስ ከሐገሪቱ ዘዉዳዊ አገዛዝ ይልቅ በጠቅላይ ሚንስትሩ በሚመራዉ መንግሥት ላይ ያነጣጠረ ተቃውሞ ተቀስቅሱአል። ንጉስ አብደላሕ የሕዝቡን ብሶትና ቁጣ «አዳምጬያለሁ» ለማለት፥ ጠቅላይ ሚንስትር መንግሥታቸዉ ተቃዉሞዉን ለማቀዝቀዝ የመሠረታዊ ሸቆጦች ዋጋን ለማስቀነስ ቃል ገብተዋል፣ ይሁን እንጂ በዮርዳኖስ የተቀሰቀስው የህዝብ አመጽ ወዴት እንደሚያመራ የታወቀ ነገር የለም።

ከዚሁ ዜና ጋር በተያያዘ የመንም በሕዝባዊ አመፅ እየታመሰች መሆኑአን የዜና አውታሮች በምስል አስደግፈው በመዘገብ ላይ ናቸው።

በተመሳሳይ ዜና እንደፈረንጆች አቆጣጠር ባለፈው ሳምንት ጃንዋሪ 14 ከሥልጣናቸው በህዝባዊ ተቃውሞ የተወገዱትና በአሁኑ ሰዓት በሳውዲ አረቢያ በስደት ላይ የሚገኙት የቱኒዚያው አምባገነን መሪ ቤኒ አሊና ባለቤታቸው በተገኙበት ተይዘው በቅጥጥር ሥር አንዲውሉ የቱኒዚያ ጊዜያዊ መንግሥት በትናንትናው ዕለት አለም አቀፍ የእስር ማዘዣ ማውጣቱ ታውቆአል። ቤን አሊ እና ቤተሰቦቻቸው በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ የ እስር ማዘዣ የወጣባቸው በስልጣን ላይ በነበሩበት አመታት የአገራቸውን ገንዘብ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብና ንብረት በመዝረፋቸው ነው ተብሎአል።

በወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ሥር ላለፉት 20 አመታት በመማቀቅ ላይ የሚገኘው የአገራችን ህዝብ እንደተቀሩት የሰሜን አፍሪካ አገሮች ሆ ብሎ ሊነሳና የመለስ ዜናዊንና ጥቂት ግብር አበሮቹን አገዛዝ ለፍጻሜ ሊያቃርበው ይችላል የሚለው ግምት የብዙ ኢትዮጵያዊያን እየሆነ መምጣቱን ሰሞኑን በተለያዩ የኢትዮጵያዊያን መወያያ መድረኮች ላይ የሚነሱት አስተያየቶች ያመለክታሉ።