“ከምስራቅ ወደ ሰሜን”? (በዮናስ በላይ)

“ስብ ት ለአብ…”፣ ሰሙኑ ምን ያልተከሰተ ነገር አለ? የህወሓት 37ኛው የልደት በዓል በሚከበርበት፣ ፈላስፋው ዘርአያዕቆብ ባስታወስንበት ድንቅ የፍልስፍና ቀን ማግስት ስብ ት ለአብ ገብረ እግዚአብሔር አጋፋሪ እንዳሻውን ተከተላቸው። በሰማእታቱ ቀን መሆኑ ነው። የቀድሞው የግብርና ምኒስትር ጓድ ተፈራ ዋልዋም ከርቸሌ ጎብኝተው እንደወጡ ሰማን። በዚህ ቢያሳልፈው ጥሩ ነበር። ነገር ግን አልሆነም። የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ከህዝቡ ጋር ሳይመክር ከምስራቅ ወደ ሰሜን አፈ ሙዙ በማዞር ላይ እንደሆነ ተሰማ። አቶ መለስም ሆኑ አቶ ኢሳያስ ግን እስከአሁን ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ ትንፍሽ አላሉም። ፓርላማውም ምንም አላለ፣ ሚድያውም እንደዛው። ለነገሩ በእነዚህ በሳንባቸው በማይተነፍሱ ተቋማት ላይ ለምን እጃችን እንቀስራለን? “አህያውን ፈርተው ዳውላውን!” ይሉታል እንዲህ አይደል ታድያ?


ምርጫ 2002፣ “አንድ ለአምስት” በሚለው ልበወለድ መፅሓፍ ሳይሆን የኢህአዴግ የ “ዴሞክራሲ” ቀመር በ99% አሽንፈው ፓርላማውን እብስ አድርገው “አባ ጠቅል!” በተባሉበት ማግስት ትልቅ ስጋት አደረባቸው። አዲስ አበባ ዳግም ወደ አመፅ እንዳትገባ። እናም ቀድመው “ድምፃችን ይከበር!” ባይ በመሆን ነገሩን አስቀየሱት። ነገር ግን ከዓረብ ገራት ወዲያውኑ አዲስ የለውጥ ንፋስ ነፈሰ። እናም ያ ሁሉ ልፋት የውሃ ሽታ ሊሆንባቸው ሆነ። ይሁን እንጂ አስበው አስበው ሁለት ካርድ መዘዙ። አንደኛው ከኢሳያስ ጋር “ፍቅር እንደገና” ሳይሆን ጦርነትን መድገም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የፍጥጫ ይዘት ያለውን አባይን መገደብ ነበር። አባይን ያላየ ሄዶ ማየት ይችላል፣ ይሉታል በዚህ ጊዜ ነው።


አቶ መለስም አቶ ኢሳያስ ላይ የቀሰሩትን እጃቸው በረድ በማድረግ ትንሽ የማይባል ህዝብ ታሪካዊ ዳራውን ብቻ አይቶ ቀልቡ እንደተሳበ፣ አብዛኛው ደግሞ “ሆድ ይፍ ው” እንዲሉ አበው እያወቀ እንዳለወቀ በመሆን “ልማት ይቅደም!” በማለት የመንፈስ ልእናውን ሲያስመሰክር በማየታቸው በዚህኛው ካርድ ገፉበት። ሆኖም የለውጥ አየሩ ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ዳግም ተቃረበ፣ እናም ወደ ውጭ ከማየት ወደ ውስጥ በመመለስ የመ መርያውን ካርድ ይዘቱ ሳይለቅ፣ “በሻዕብያ መንግስት ተላላኪነት…የልማታችን ፀር…” እያሉ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች በማሰር እሳቱን ወደ ፍምነት ቀየሩት። ገሬ፣ እንደ ድሮው “እኔ ልቅደም፣ እኔ” በሚሉ ሳይሆን፣ “መምሃሪን አይግበርካ መምሃሪን አየስእንካ!” ከሚለው አባባል አንዷን ጫፍ ብቻ በመምዘዝ አስበልተው ገሸሽ በሚሉ ፖለቲከኞች የተሞላች ሁናለች እና ንፋሱ አቅጣጫውን ቀይሮ መንፈሱን ቀጠለ። የአዲሳቤ ቅስምም እምሽክ አለ።


ከአውሮፓው የአየር መዛባት ተያይዞ ነው መሰለኝ ያ የአረቡ የለውጥ ንፋስ ለ‘ሳልሳይ’ ጊዜ እያንዣበበ ያለው። በዚህም ድ ው በእለት ጉርሻ እጦትና ከመኖርያው መፈናቀል፣ ብታሙም በአዲሱ የመሬት አዋጅ፣ እንዲሁም በአጠቃላይ ቁርጠኛና ቀኛ የነፃነት መሪ በማጣት የበሸቀ ህዝብ ራሱን በራሱ እንዳይነሳባቸው፤ ከውስጥም ያለውን የስልጣን ሽኩቻ ለማስተንፈስ ሲሉ አዲስ ጉዞ የ መሩ ይመስላል። ጉዞ ወደ ሁለተኛው ካርድ፣ እንደገና…


በ90ዎቹ፣ የኢሳያስ መንግስት የኢትዮጵያ ድንበር እንደሚደፍር ከስድስት ወር በፊት በከፊል የህወሓት አባላት ለኢህአዴግ መሪዎች የቀረበውን ሪፖርት ሳናነሳ፣ የ ገር ሽማግሌዎች፣ “አረ ልታስጨርሱን ነው!” ብለው የጮሁበት ጊዜ ስናይ ጆሮ የሰጣቸው እንዳልነበር እናስታውሳለን። የተፈራውን እንደሆነም የእነ አቶ መለስ መልስ፣ “የያዙት መሬት 20፣ 30 ዓመት ከእነሱ ጋር ይቆይና ወደ መካከለኛው ገቢ ያላቸው ገራት ተርታ ስንሰለፍ እንመልሰዋለን!” በማለት ስላቅ መቱ። በውስጣቸው ነገር እየከረረ ሲመጣም፣ “በቃ! ሌሎች ፓርቲዎች አያገባቸውም ህወሓትና ሻዕብያ በፓርቲ ደረጃ ተወያይተው ነገሩን ይፍቱት!” ነበር ያሉት። የማታ ማታ፣ በስንት ሙጉት ጉዳዩ ወደ ፓርላማ ቀረበና፣ “የሰላም በሩ እንዲከፈት እናንኳኳ ከሌለ ግን ሰብረን ሙያ እንስራ” ብሎ ወሰነ። ይሁን እንጂ የህዝብ ውሳኔ ላለማክበር አሁንም ኢህአዴግ አንገራገረ። በመሆኑም በሁለት ልብ ተከፍሎ ወደ ጦርነት የገባ ህዝብ ደሙ በከንቱ ፈሰሰ። በዛ በኩል እንኳን፣ “ባደመ ሄደች ማለት ፀሃይ በምስራቅ ትጠልቃለች ማለት ነው!” ያሉትን እውን እንደሆነ ማስመሰከር ችለዋል። ምንም ትርፍ ያልተገኘበት ደምና አጥንት የተከፈለው ከወዲህ ነው።


በዚህ ጉዳይ ላይ፣ ጆን አቢንክ “The Eritrean-Ethiopian border conflict” በሚለው ጥናታዊ ስራቸው ላይ፣ “የሁለቱም እቡይነት እና አምባገነነት እንዲሁም የመወሰን ብቃት ማነስና ግንኙነታቸው ግልፅ ስምምነት ላይ የተሞረከዘ ባለመሆኑ የተወለደ ትርጉም የለሽ ጦርነት” ብለው ይገልፁታል፡- “in focusing too much on the whereabouts of Badme in the final border demarcation exercise, it is easy to lose sight of the real issues of the war, which to most observers was quit senseless. These issues were a combination of personal arrogance of two regimes(and leaders) with authoritarian tendencies, political indecisiveness(especially on the part of Ethiopia), and the lack of clear-cut, statesman-like agreements the mutual politico-economie relations of the two new states after 1991, when the two leaders came to power with a momentum of hope and promise.”


አቶ መለስ በተመሳሳይ መልኩ “የአንድ ገር ሉአላዊነት ማክበር” የሚል የይስሙላ መር ቸው ጥሰው ወደ ሶማሊያ ለመዝመት የቤት ስራቸውን ከጨረሱ ብኃላ፣ ለወጉ ወደ ፓርላማ መጥተው አማክሩን አሉ። ዳሩ ግን የተለየ ሳብ ያቀረቡ የቤቱ አባላት “በ ገር ህልውና የቆሙ ጋሬጣዎች” በማድረግ ኮነንዋቸው። ሆኖም ‘ኩኑናን’ ጩ ታቸው የቁራ ጩ ት አልነበረምና፣ ያሉትን ከ ቅ የራቀ እንዳልነበረ በዓለም አቀፍ ሚድያዎች ተመለከትን። አቶ መለስ፣ ድጋሜ ወደ ሶማሊያ ሲዘምቱ ግን የእግር ኮቴያቸውን እንኳን ሳያሰሙ ነበር። እናም እንደ የሌላ አገር ዜጋ ነገርየውን ፍፃሜ ካገኘ ብኃላ ሰማን። አሁንም የሆነው ይህ ነው።


ይህ አገር የማን ነው? በ ገራዊ ጉዳይስ መወሰን ያለበት ማን ነው? አቶ መለስ፣ ክብርት ወ ልእልት ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ አዜብ(ወ እጨጌ፣ ልጨምርበት እንዴ? ዶ/ርስ?) እና ነራል ሳሞራ ብቻ ናቸውን? የመሬቱ (የሊዝ አዋጁስ) ይሁን፣ በዚህ የሉአላዊነት ጉዳይ ግን ምንም እንኳን “በ99 በመቶ የተመረጡት” የፓርላማ አባላት ቢንቋቸውም እነዛ “አናሳ ድምፅ ያላቸው” ህዝቦች ለማክበር ሲሉ ግን ከአማራጭ ይሎች ጋር መምከር ይገባዎት ነበር። ወይስ ይህንን ጦርነት ለመከወን በህዝቡ የተቀመጠቦ ቅድመ ሁኔታዎች (ለምሳሌ፡- የአሰብ ጉዳይ እንዲሁም ከስልጣንዎ መውረድ የመሳሰሉትን) ለማሟላት ስላልፈለጉ ይሆን? ወይስ ስለ ጦርነቱ አላማ፣ ትርፍና ኪሳራ እንዳይጠየቁ ሰግተው ነው “በሰላሕታ” የተጠጉት?


የኤርትራ ተቃዋሚዎች ለማደራ ት የሚደረግ ጦርነት ቢሆንስ እኛ ማወቅ አይገባንም!? አቶ ኢሳያስን ለማስበርገግ አሊያም “በአፋር ለፈፀሙት ጥፋት” ተመጣጣይ እርምጃ ለመውሰድስ ቢሆን መምከር የለብንም!? አረ መገለል ገደለን!


የኛ፣ የ ገርዎ ባርያዎች ጉዳይስ ደህና፣ ይህንን ውጥንዎ ግን በድርጅትዎ ሆነ በሰራዊቶ ንፋስ ሳይሰገባቦት ይቀራል ብለው ነው? የባድመን አይነት የዜጋው ደም በከንቱ ፈሶ ማየት የማይፈልግ እሳት የላሰ ግና የመከላከያ ሰራዊት የለም ብለው ነው? ይህንን ሲሆን ሌሎችስ ይሁን፣ ብአዴን ግን ሰምተዋልን? ለነገሩ በእንደዚህ አይነት ጊዜ አቶ መለስ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉ።


አቶ ተፈራ ዋልዋ የኢሳያስ መንግስት በ90ዎቹ እንደወረረን መ መርያ “መዋጋት አለብን!” ከሚሉት ጎራ ነበሩ፣ እንድያውም ይለኛ አቀንቃኝ:: ከተኮረኮሙ በኋላ ግን ወዲያው እጥፍ አሉና “መዋጋት የለብንም!” ባይ ሁነው ቁጭ። አቶ መለስ እንዲህ እያደረጉ ስንቱን ከሰውነት አውጠተዋል? የሆኖ ሆኖ፣ ከውስጥ ያለውንስ ፀሃያችን እስከሚወጣ ድረስ እንሸከመዋለን የውጭውን (የሉአላዊነት) ግን የ ገሬን ልእልናና ክብርን የማያጎድፍ እንዲሆን እማፀኖት አለሁ! “ተስፋ ማድረግ ሰው መሆን አይደል፣ ተስፋ አልቆረጥኩም።”- ኦሮማይ።


ኢትዮጵያዊነትና ታላቋ ኢትዮጵያ ለዘለአለም!