የቀድሞው መንግሥት ባለሥልጣናት ከገና በፊት ሊፈቱ ይችላሉ
(በታምሩ ጽጌና በዘካሪያስ ስንታየሁ፤ ሪፖርተር ጋዜጣ፤ Sunday, 19 December 2010 12:31 ):-
በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰው በሞት፣ በእድሜ ልክና በዓመታት እስር እንዲቀጡ የተወሰነባቸው የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለገና ሊፈቱ እንደሚችሉ ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ በወቅቱ የፈጸሙትን የተለያዩ ወንጀሎችን በማመን እግዚአብሔርን፣ ሕዝብንና መንግሥትን ይቅርታ እንዲጠይቁ ከሁለት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ላሉት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ በወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስና በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሃይማኖት መሪዎች እንዲለምኑላቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፤ የሃይማኖት መሪዎቹ መንግሥትን፣ ተጎጂዎችንና የተጎጂ ቤተሰቦችን በማነጋገር ይሁንታ በማግኘታቸው ሳይፈቱ እንደማይቀሩ ምንጮቹ ያላቸውን ግምት ተናግረዋል፡፡
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)
