ሳዑዲ አረቢያ የታሰሩ ኢትዮጵውያን
የሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት ያሰሯቸዉን ኢትዮጵዉያን ክርስቲያኖች እስልምና እንዲቀበሉ ግፊት እያደረጉባቸዉ ነዉ ሲል አንድ የክርስቲያኖች መብት ተማጋች ድርጅት ወቀሰ።እስረኞች ግን ሐይማኖታቸዉን እንዲቀይሩ ተደረገባቸዉ ሥለተባለዉ ተፅዕኖ ያወሱት ነገር የለም
የሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት የሐገሪቱን ሕግና ሥርዓት ጥሰዋል በሚል ወንጀል ያሰሯቸዉን ኢትዮጵዉያን ክርስቲያኖች እስልምና እንዲቀበሉ ግፊት እያደረጉባቸዉ ነዉ ሲል አንድ የክርስቲያኖች መብት ተማጋች ድርጅት ወቀሰ።ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘዉ ዓለም አቀፍ የክስቲያን መብት አስከባሪ የተሰኘዉ ተቋም እስረኞቹ ለማስፈታት የፊታችን ማክሰኞ ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ ሰልፍ ጠርቷል።የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የሐይማኖት ኮሚሽን የተሰኘዉ ድርጅት በበኩሉ ኢትዮጵያዉያኑ እስረኞች አንድም እንዲፈቱ አለያም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ጠይቋል። አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ። ያዳምጡ
የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ያነጋገራቸዉ እስረኞች ግን ሐይማኖታቸዉን እንዲቀይሩ ተደረገባቸዉ ሥለተባለዉ ተፅዕኖና ጫና ያወሱት ነገር የለም።ይሁንና እስረኞቹ የነሱንም ሆነ የሌሎች ኢትዮጵያዉን እስረኞችን ችግር ለማቃለል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሥልጣናት ብዙም አልጣሩም በማለት ይወቅሳሉ።የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካዮች ግን ወቀሳዉን አይቀበሉትም።ዝር ዝሩን እነሆ። ያዳምጡ