ዘቢዳር ቢራ አክሲዮን ማኀበር 150 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ በነፃ ተሰጠው

–    ንብ ባንክና ኢንሹራንስ የ20 ሚሊዮን ብር አክሲዮኖች ገዙ

የአገሪቱን የቢራ ገበያ ለመቀላቀል ካለፈው መጋቢት 2003 ዓ.ም. ጀምሮ የአክሲዮን ሽያጭ እያደረገ ያለው ዘቢዳር ቢራ አክሲዮን ማኅበር፣ ለፋብሪካ ግንባታ የሚሆነውን 150 ሺሕ ካሬ ሜትር በነፃ ሲያገኝ፣ ለፋብሪካው ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አኑሯል፡፡