እናቴ፣መንግስቷ እና መሬቷ
አቤ ቶኪቻው
ወዳጄ እንዴት ሰነበቱልኝ… እውነቱን ለመናገር በየሳምንቱ ለሀገሬ አንድ ለእናቱ የሆነችው ፍትህ ጋዜጣ ላይ በየሳምንቱ ብከሰት ደስታዬ ወደር አልነበረውም። ነገር ግን ጋዜጣዋ የምትውለው “አርብ አርብ ይሸበራል እየሩሳሌም” በተባለበት አርብ ቀን በመሆኑ የኔ ነገር ደግሞ በተለይ ከዚህ ከስደት በኋላ አንዳንዴ የምፅፋቸው ፅሁፎች “ፆም የነካካቸው” እየሆኑብኝ የጦም ሀገር ለሆነችው ኢትዮጵያዬ አልሆን እያለኝ ስተወው፤ ስተወው ቆይቼ በዛሬው አርብ ግን በተቻለኝ አቅም ጦም ያልነካካው ጨዋታ ይዤ አዲሳባ ብቅ ብዬ ነበር።