ከጎሣ ልዩነት ወደሃይማኖት ልዩነት? ያዋጣል?
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
ሃይማኖት ተከታዮች ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበር፤ አብዛኛዎቹ ተሳታፊዎች ይዘውት የነበረው መፈክር፡ ‹‹እስልምና በቋንቋ ወይም በጎሣ አይከፋፈልም!›› የሚል ነበር፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአንዋር መስጊድ ውስጥ ብዙ ሰዎች ተገደሉ፣ ያንን አልፈን ወደሌላ ምዕራፍ የተሸጋገርን መስሎኝ ነበር፤ ነገር ግን አዲስ ክስተት እይተፈጠረ ይመስላል፤ ሰሞኑን በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መሀል ወይም በእነሱ ላይ አዲስና አንዳንዶቹ የማይቀበሉት ጥቃት የተፈጸመባቸው ይመስላል፤ በጋዜጦች ላይ አንዳንድ ስሞታዎችን በተደጋጋሚ አንብቤአለሁ፤ በሚወጡትና እኔ ባየኋቸው ጽሑፎች የተጣራና ግልጽ የሆነ ነገር ባለማግኘቴ ወደኢንተርኔት ገብቼ ‹‹አህባሽ›› ስለተባለው የእስልምና ዓይነት ለማወቅ ሞክሬ ያገኘሁት፡-