የአደንዛዥ ዕፆች ሱስ

የዛሬው የወጣቶች ዝግጅት በአደንዛዥ እፅች ላይ ነው ያተኮረው። ባለሙያዎች እንደሚገምቱት እስከ 15 ከመቶ የሚሆነው የኢራን ህብረተሰብ የአደንዛዥ እፅ ሱሰኛ ነው። እንደ ኦፒየም እና ሐሺሽ የመሳሰሉት አደንዛዥ ዕፆች በአገሪቷ ይወሰዳሉ። ጉዳቱ የነዚህ እፆች ያህል አይሁን እንጂ በኢትዮጵያም በተለይ የጫት ሱሰኛ ከፍተኛ ነው።