የሱዳንና ደቡብ ሱዳን ያለመጠቃቃት ውል

ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በአፍሪቃ ሕብረት አማካይነት አዲስ አበባ ላይ ባካሄዱት ድርድር እርስበርስ ያለመጠቃቃት ውል ተፈራረሙ። ውሉን የተፈራረሙት የሱዳን የጸጥታ ሃላፊ ሞሐመድ አታና የደቡብ ሱዳኑ አቻቸው ቶማስ ዱዝ ሲሆኑ ውሉን ያፈራረሙት ዋነኛው አደራዳሪ የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ታቦ እምቤኪ ናቸው።