“አባ ጳውሎስ” እባኮዎት የምንኩስናዎን ልብስ ያውልቁና አለማዊ ልብስ ይልበሱ

በመጸሃፈ ሲራክ

በዚህ ድርጊት ልባቸው የተሰበረና የቤቱ ቅናት ያቃጠላቸው ሊቀ-ሊቃውንት አለቃ አያሌው ታምሩ ለእውነት በመቆም የሚከተለውን የግዝት ቃል አስተላልፈው ነበር።

“ከዛሬ ጀምሮ በብፁህ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እና ተባባሪ በሆኑት ሊቃነ ጳጳሳት እጅ ቡራኬ እንዳትቀበሉ፡ እንዳትናዘዙ፡ስማቸውን በጸሎተ ቅዳሴ የሚጠሩ አባቶች ቀሳውስት ካህናት ካሉም የአምልኮተ ጣኦት አራማጅ ናቸውና ተጠንቀቁዋቸው፡ ምክር ስጡዋቸው እምቢ ካሉም ተለዩአቸው። በዓል ሲመታቸውም የአሮን የወርቁን መታሰቢያ ሆኖ በቤተክርስቲያን ሊከበር የማይገባው ስለሆነ ጳጳሳት ይህንን ድርጊት አውግዘው ከስልጣናቸው ካላነሱ ምእመናን እንዳትዛዙአቸው፤ ደሙን ባፈሰሰ አምላክና ስም ቤተክርስቲያንን በሚመራና በሚጠብቅ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥያቄዬን አስተላልፋለሁ።