ግልጽ ደብዳቤ (ፀሐይ አሳታሚና ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ) – (ሊያነቡት የሚገባ)
ክፍሌ ሙላት (የኢነጋማ ፕሬዝዳንት) – በግል
ሲሞላልኝ በሳምንት ካልሆነልኝ ደግሞ በአስራ አምስቱ ሰላምታዬን ካሉበት የማደርሳቸው ወዳጆች አሉኝ። ለአገር ምድሩ ሳይሆን በጣት የሚቆጠሩ። ከእነዚህ መካከል አንዱ የሙያ ባልደረባዬ ኤልያስ ወንድሙ ነው። ትውውቃችን የመንገድ ላይ አይደለም። የኔዎቹ የነፃ ፕሬስ አባላትና የሃገሬ ሰላም ወዳድ ኃይሎች በግፈኞቹ የሕወሃት አባላትና ሹመኞች የሚሰደዱበት የሚታሰሩበት ብሎም የግፍ ፅዋ የሚቃመሱበት በእነዚያ የትግል፣ የፈተናና የፍልምያ ዓመታት የልብ ወዳጅና ለእውነት የቆሙ በመብራት በሚፈለጉበት የወያኔ የግፍ ዘመናት። ዛሬም ይህ ሐቅ ገሃድ ነው።