ኢትዮጵያ ውስጥ የዋጋ ንረቱ እያሻቀበ ነው ፤የባንክ ሥራ ግን አዋጪ ሆኗል፤ መንግሥት ከ1ቢሊዮን ብር ሰብስቧል
(ኢትዮ እማማ)
ኢትዮጵያ ውስጥ የዋጋ ንረቱ በአሁኑ ወቅት ከመጠን በላይ እያሻቀበ ቢሄድም የባንክ ሥራ ግን አዋጪ ሆኗል፤ በኢትዮጵያ መንግሥት የሚረዱ የግልና የመንግሥት ባንኮች ትርፋማ ሆነዋል ።መንግሥት ከ1ቢሊዮን ብር በላይ ተርፍ ሰብስቧል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ለመጪዎቹ አምስት አመታት እንዳቀደ ቢናገርም ከውጨ የሚገቡ ምርቶች ና በአገር ውስጥ የሚገኙ የሸቀጣ ሸቀጦች እጥረት ለዋጋ ንረቱ ማሻቀበ እንደምክንያት አድርጎ ያቀረባል። የሀገሪቱ መንግሥትም ይህንን የዋጋ ንረት ከማርገብ ይልቅ ዝምታን በመምረጡ በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የኅብረተሰባችን ክፍል ኑሮን መቋቋም አቅቶት በችግር እየተጠበሰ የገኛል።
ይሁንና የኢትዮጵያ መንግሥት በርካታ የሚደጉማቸው የግል ባንኮችን በብዛት እንዲከፈቱ በማድረግ ከባንኮች 1ቢሊዮን 458 ሚሊዮን ብር ወይንም 88.2 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በ2009/10 ማለትም ከጁላይ 8, 2009 እስከ ጁላይ 7, 2010 ከግልና ከመንግሥት ባንኮች የተጣራ የታክስ ትርፍ አግኝቷል።
የግል ባንኮች ትርፍ 39 በመቶ በ2009/10 እድገት ያሳየ ሲሆን አሥሩ የግል ባንኮች 162 ሚሊዮን ብር በ2009/10 የትርፍ ጭማሪ በማሳየት 580 ሚሊዮን ብር ወይንም በወቅቱ ምንዛሬ ወደ 35 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር አካባቢ ትርፍ አግኝተዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 840 ሚሊዮን ብር ወይንም 50.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ክፍያ ፈፅሞ በ2009/10 ላይ 46 ሚሊዮን ብር ካለፈው በተሻለ ከፍተኛ ትርፍ ለማግኘት ችሏል።
ለ24000 የሀገሪቱ ዜጎች የስራ እድል መከፈቱና አሥሩ የግሉ ባንኮች 13000 ሠራተኞችን ቀጥረው እንደሚያሰሩ ተጠቁሟል።በቀጣዩ አመትም የኢትዮጵያ መንግሥት የሚደግፋቸው አባይ፣ ደቡብ ግሎባል፣አዋሳ፣እናትና ኖአ ባንክ የተሰኙ አዲስ የግል ባንኮች እንደሚከፈቱ ታውቋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለበፊቶቹም ሆኑ አዲስ ለሚከፈቱት ለግል ተብዬ ባንኮች ገንዘብ ያበድራቸዋል፣ገንዘብ ያስቀምጥላቸዋል።
እንደ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች አገላለፅ ከሆነ የሀገሪቱ መንግሥት በገበያው ውስጥ የሚንቀሳቀሰውን የገንዘብ መጠን ግምት ውስጥ ባልከተተ መልኩ ስለሚያንቀሳቅስ በተለይም የሀገሪቱ ባለስልጣናት መንግስት የበጀት ጉድለት ሲያጋጥመው ብቻ ሳይሆን እንዳሻቸው እንዲወጣ ስለሚያዙ እንዲሁም ለንግድ ለተቋቋሙት ባንኮች ከካዝናው እያወጣ በትህዛዝ ጭምር በብድር መልክ እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ የሚሰጠው ገንዘብ በአብዛኛው ገቢ ስለማይሆን ይህም በገንዘብ ፖሊሲው ጭምር ሳቢያ የዋጋ ንረቱ በአሁኑ ወቅት ከመጠን በላይ እንዲያሻቅብ አድርጎታል ባይ ናችው።